የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mrt ርዕስ 136
  • ለአምላክ ጊዜ ስጥ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ለአምላክ ጊዜ ስጥ
  • ተጨማሪ ርዕሰ ጉዳዮች
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ኢየሱስ ምን አስተምሯል?
  • “መንፈሳዊ ነገሮችን የተጠሙ ደስተኞች ናቸው።”—ማቴዎስ 5:3
    “መንፈሳዊ ነገሮችን የተጠሙ ደስተኞች ናቸው።”—ማቴዎስ 5:3
  • ደስታ ስለሚገኝበት መንገድ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2010
  • መንፈሳዊ ፍላጎትህን ማርካት ትችላለህ
    ንቁ!—2009
  • እውነተኛ ደስታ ማግኘት ትችላላችሁ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2022
ለተጨማሪ መረጃ
ተጨማሪ ርዕሰ ጉዳዮች
mrt ርዕስ 136
በተለያዩ የዓለም ክፍሎች መጽሐፍ ቅዱስን እያነበቡ፣ የጥናት ፕሮግራም እያወጡ እና እየጸለዩ ያሉ ወጣቶች።

ከኢየሱስ ተማሩ

ለአምላክ ጊዜ ስጥ

ለአምላክ ጊዜ ስትሰጥ ሕይወትህ ይሻሻላል። በውስጥህ ያለው መንፈሳዊ ጥማትም ይረካል። ኢየሱስ ስለዚህ ርዕሰ ጉዳይ ምን እንዳስተማረ ተመልከት።

ኢየሱስ ምን አስተምሯል?

“መንፈሳዊ ነገሮችን የተጠሙ ደስተኞች ናቸው።”—ማቴዎስ 5:3

  • ‘ወደዚህ ምድር የመጣነው ለምንድን ነው? መከራችን የበዛው ለምንድን ነው? ሰው ሲሞት ምን ይሆናል?’ እነዚህ የሁላችንም ጥያቄዎች ናቸው። ደስተኛ መሆናችን የተመካው ለእነዚህ ጥያቄዎች በምናገኘው አርኪ መልስ ላይ ነው።

“ሰው ከይሖዋa አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በምግብ ብቻ አይኖርም።”—ማቴዎስ 4:4

  • የሰው ልጅ በሕይወት ለመኖር ምግብ እንደሚያስፈልገው ሁሉ መንፈሳዊ ምግብም ያስፈልገዋል። የኢየሱስ ሐሳብ እንደሚጠቁመው መንፈሳዊ ረሃባችንን ለማስታገሥ አዘውትረን የአምላክን እርዳታ መፈለግ አለብን።

“ቃልህ እውነት ነው።”—ዮሐንስ 17:17

  • መንፈሳዊ ፍላጎታችንን እንድናረካ አምላክ እኛን የሚያግዝበት ዋነኛው መንገድ ቃሉ ማለትም መጽሐፍ ቅዱስ እንደሆነ ኢየሱስ ጠቁሞናል።

አንተስ ዘላቂ ደስታ ማግኘት ትፈልጋለህ? ለአምላክ ጊዜ እንድትሰጥና መንፈሳዊ ጥማትህን እንድታረካ እናበረታታሃለን። ይህን ለማድረግ የሚያግዙ ነገሮችን አዘጋጅተንልሃል፤ ለምን አትሞክራቸውም?

  • መጽሐፍ ቅዱስን በነፃ አንብብ።

  • በግል በሚመደብልህ አስተማሪ አማካኝነት አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ ኮርሳችንን በነፃ ተማር።

a ይሖዋ የአምላክ ስም ነው። (መዝሙር 83:18) “ይሖዋ ማን ነው?” የሚለውን ርዕስ ተመልከት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2026)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2026 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ