የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • wcg ምዕ. 41 ገጽ 188-191
  • “በአምላክ ፊት ጻድቃን ነበሩ”

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • “በአምላክ ፊት ጻድቃን ነበሩ”
  • በድፍረት ከአምላክ ጋር ሂድ
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ጠለቅ ብለህ መርምር
  • ምን እንደሚያስተምርህ አስብ
  • በትልቁ ነገር ላይ አሰላስል
  • እውቀትህን አስፋ
  • ኤልሳቤጥ ልጅ ወለደች
    ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
  • ያለ ነቀፋ በመመላለሳቸው ተክሰዋል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1994
  • መንገድ የሚያዘጋጅ ሰው ተወለደ
    ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
  • መንገድ ጠራጊው ተወለደ
    እስከ ዛሬ ከኖሩት ሁሉ የሚበልጠው ታላቅ ሰው
ለተጨማሪ መረጃ
በድፍረት ከአምላክ ጋር ሂድ
wcg ምዕ. 41 ገጽ 188-191

41 ዘካርያስ እና ኤልሳቤጥ

“በአምላክ ፊት ጻድቃን ነበሩ”

በወረቀት የሚታተመው
በወረቀት የሚታተመው

ይህ ቀን ለዘካርያስ ልዩ ቀን ነው። ዛሬ የሚያከናውነው አገልግሎት እንዲሁ በዋዛ የሚገኝ አይደለም፤ ምናልባትም በሕይወት ዘመኑ አንድ ጊዜ ብቻ የሚያገኘው ልዩ መብት ነው። ዘካርያስ የአሮን ዘር ከሆኑ እጅግ ብዙ ካህናት አንዱ ነው፤ በዚህ ዕለት ተራው ደርሶ ቤተ መቅደሱ ውስጥ በሚገኘው የወርቅ መሠዊያ ላይ ዕጣን ሊያጨስ ነው። እሱም ሆነ ውድ ባለቤቱ ኤልሳቤጥ ይህን ቀን በጉጉት ሲጠብቁት እንደቆዩ ምንም ጥርጥር የለውም።

ዘካርያስና ኤልሳቤጥ ለብዙ ዓመታት በትዳር ሲኖሩ የተለያዩ በረከቶች አግኝተዋል፤ ቢጓጉለትም እስከ አሁን ያላገኙት አንድ በረከት ግን አለ። ይህም ልጅ ወልዶ መሳም ነው። ይህ በዚያ ዘመን የነበሩ የአምላክ ሕዝቦች ትልቅ ቦታ የሚሰጡት ጉዳይ ነበር። ዘካርያስና ኤልሳቤጥ አሁን ‘ዕድሜያቸው ገፍቷል።’ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚናገረው እነዚህ ባልና ሚስት “በአምላክ ፊት ጻድቃን ነበሩ።” ስለዚህ ወደ አምላክ መጸለያቸውን ቀጠሉ፤ ሁኔታቸው ተስፋ ያለው ባይመስልም አምላክ እንደሚሰማቸው እርግጠኞች ነበሩ።

ሕዝቡ ሁሉ ደጅ ላይ ሆኖ እየጸለየ ሳለ ዘካርያስ ወደ ቤተ መቅደሱ ገባ። ከእሱ በቀር ማንም በሌለበት በዚያ ክፍል ውስጥ በድንገት በዕጣን መሠዊያው አጠገብ የይሖዋ መልአክ ተገለጠለት! አምላክ ጸሎቱን እንደሰማለትና ኤልሳቤጥ ወንድ ልጅ እንድትወልድለት እንደሚያደርግ መልአኩ ለዘካርያስ ነገረው። የልጁ ስም ዮሐንስ ይሆናል። አድጎ ትልቅ ሰው ሲሆን ‘የኤልያስ መንፈስና ኃይል’ ይኖረዋል። ሕዝቡ ወደ ይሖዋ እንዲመለሱ ልባቸውን በማዘጋጀት ታላቅ ሥራ ያከናውናል።

ነገሩን ማመን የከበደው ዘካርያስ፣ የተባለው ነገር መፈጸሙን በምን እርግጠኛ እንደሚሆን ጠየቀ። መልአኩም “እኔ በአምላክ አጠገብ በፊቱ የምቆመው ገብርኤል ነኝ” በማለት አረመው። ዘካርያስ እንዲህ ያለውን ኃያል የይሖዋ አገልጋይ የሚጠራጠርበት ምክንያት አልነበረውም። አምላክ ቃል የገባው ነገር እስኪፈጸም ድረስ መናገር እንደሚሳነው ገብርኤል ነገረው። በመሆኑም ዘካርያስ ከቤተ መቅደሱ ሲወጣ፣ ስለተፈጠረው ነገር በምልክት ከማሳየት ውጭ መናገር አልቻለም።

ልጅ መውለድ እንቢ ያላቸው አንድ ባልና ሚስት በስተ እርጅናቸው ሕይወት የሚቀይር መልእክት ከሰማይ መጣላቸው

ዘካርያስ የተፈጠረውን ነገር በሆነ መንገድ ለኤልሳቤጥ አስረድቷት መሆን አለበት። “ከተወሰኑ ቀናት በኋላ” ፀነሰች። ለአምስት ወር ያህል ከቤት ሳትወጣ ቆየች፤ በስድስተኛው ወር ላይ ግን አንዲት ዘመዷ ልትጠይቃት ከናዝሬት መጣች። ይህች ዘመዷ የሄሊ ልጅ የሆነችው ማርያም ነች። ማርያም ቤት እንደገባች በኤልሳቤጥ ማህፀን ውስጥ ያለው ፅንስ በደስታ ዘለለ። ኤልሳቤጥም በመንፈስ ቅዱስ ተሞልታ ማርያምን “የጌታዬ እናት” ብላ ጠራቻት። ማርያም በኋላ ላይ መሲሕ የሚሆነውን ልጅ እንደፀነሰች ኤልሳቤጥ አውቃለች። ሆኖም በዚህ አልቀናችም፤ ከዚህ ይልቅ ወጣቷን ከፊቷ ለሚጠብቃት ኃላፊነት አደፋፈረቻት።

በመጨረሻ ኤልሳቤጥ ወለደች። የደስታዋ ተካፋይ ለመሆን የተሰበሰቡት ጎረቤቶቿና ዘመዶቿ ሕፃኑ በአባቱ ስም እንዲጠራ ጫና ሊያደርጉባት ሞከሩ። ኤልሳቤጥ ግን ገብርኤል ለባሏ “[ስሙን] ዮሐንስ ትለዋለህ” እንዳለው ታውቅ ነበር። ስለዚህ በሐሳባቸው አልተስማማችም። “አይሆንም! ዮሐንስ ይባል” አለቻቸው። ምላሿ ስላላስደሰታቸው ዘካርያስን አማከሩት። አሁንም መናገር የማይችለው ዘካርያስ “ስሙ ዮሐንስ ነው” ብሎ ጽላት ላይ ጻፈ። በዚያው ቅጽበት የመናገር ችሎታው ተመለሰለት።

ዘካርያስ ጽላት ላይ እየጻፈ ነው፤ ኤልሳቤጥ ሕፃኑን አቅፋ አጠገቡ ተቀምጣለች። ጎረቤቶቻቸውና ዘመዶቻቸው ዘካርያስን ከብበው በትኩረት እየተመለከቱት ነው።

ከዚያም ዘካርያስ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ ትንቢት መናገር ጀመረ። ተስፋን፣ መዳንን እንዲሁም መለኮታዊ ምሕረትን የሚያበስር መልእክት በመንፈስ ተገፋፍቶ ተናገረ። ልጁ ዮሐንስ ‘መንገዱን ለማዘጋጀት ቀድሞ በይሖዋ ፊት እንደሚሄድ’ ተነበየ። የሆነውም ይህ ነው። መጥምቁ ዮሐንስ ሕዝቡ ስለ አምላክ መንግሥት የሚገልጸውን የኢየሱስ መልእክት እንዲቀበሉ ልባቸውን በማዘጋጀት የመሲሑ መንገድ ጠራጊ ሆነ።

መሲሑ ሲገለጥ አምላክ፣ የማያምኑና ተቃዋሚ የሆኑ ሰዎችን በሚይዝበት መንገድ ላይ ትልቅ ለውጥ ይደረጋል። ቀደም ባሉት ዘመናት ብዙ የአምላክ አገልጋዮች የጦር መሣሪያ አንስተው የይሖዋን ጠላቶች በመፋለም ድፍረት አሳይተዋል። አሁን ግን የይሖዋ አገልጋዮች በአዲስ ዘመን መባቻ ላይ ናቸው፤ ከዚህ በኋላ ይሖዋ ጦር እንዲማዘዙ አይጠይቃቸውም። ሆኖም አሁንም ድፍረት ማሳየት ያስፈልጋቸዋል። መሲሑን የተቀበሉ ሁሉ ልክ እንደ ዘካርያስ እና ኤልሳቤጥ የመናገር ስጦታቸውን ተጠቅመው ይሖዋ አምላክን ያወድሱታል እንዲሁም ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የሚናገረውን ምሥራች ያውጃሉ።

ታሪኩን ከመጽሐፍ ቅዱስ አንብብ፦

  • ሉቃስ 1:5-25, 36-45, 57-80

ለውይይት፦

ዘካርያስ እና ኤልሳቤጥ ድፍረት ያሳዩት በየትኞቹ መንገዶች ነው?

ጠለቅ ብለህ መርምር

  1. 1. ዘካርያስ እና ኤልሳቤጥ ፍጹማን ባይሆኑም መጽሐፍ ቅዱስ “ያለነቀፋ ይኖሩ ነበር” የሚለው ለምንድን ነው? (ሉቃስ 1:6፤ it “እንከን የለሽነት” አን. 2-wcgr)

  1. 2. መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ገብርኤል ምን ይነግረናል? (it “ገብርኤል” አን. 2-3-wcgr) ሀ

ሥዕሎች፦ 1. መልአኩ ገብርኤል ሰማይ ላይ ቆሞ ቀና ብሎ እያየ ነው። 2. ለዳንኤል መልእክት ሲያደርስ። 3. ለዘካርያስ መልእክት ሲያደርስ። 4. ለማርያም መልእክት ሲያደርስ።

ሥዕል ሀ

ሥዕል ሀ

  1. 3. ዘካርያስ ለልጁ ዮሐንስ ብሎ ስም እንዲያወጣለት ገብርኤል ነግሮት ነበር። ዮሐንስ ምን ማለት ነው? (it “ዮሐንስ” አን. 1-wcgr)

  2. 4. ዘካርያስ መናገርም መስማትም ተስኖት ነበር? (w08 3/15 30 አን. 6)

ምን እንደሚያስተምርህ አስብ

  • በዘካርያስ ዘመን አይሁዳውያን ረቢዎች አንድ ሰው ሚስቱ ልጅ ካልወለደችለት ሊፈታት እንደሚችል ያስተምሩ ነበር። ታዲያ ባሎች ለትዳር ጓደኛ እስከ መጨረሻው ታማኝ መሆንን በተመለከተ ከዘካርያስ ምን ይማራሉ? ለ

    ሥዕሎች፦ ለበርካታ ዓመታት ከሚስቱ ጎን በታማኝነት የጸና ባል። 1. በሠርጋቸው ቀን ከባለቤቱ ጋር። 2. ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ገለልተኛ በሆነ አካባቢ አብረው ሲያገለግሉ። 3. በአሁኑ ወቅት በጋሪ ምሥክርነት አብረው ሲካፈሉ። ባልየው ታማሚ ከሆነችው ሚስቱ አጠገብ ቆሟል፤ እጁን ትከሻዋ ላይ ጣል አድርጓል። ሚስትየው በሞተር በሚሠራ ተሽከርካሪ ወንበር ላይ የተቀመጠች ሲሆን የምትተነፍሰው በኦክስጅን ታንክ እገዛ ነው።

    ሥዕል ለ

  • ኤልሳቤጥ ከጎረቤቶቿና ከዘመዶቿ ጫና ቢደርስባትም የባሏን መመሪያ በታማኝነት ደግፋለች። (ሉቃስ 1:58-61) ሚስቶች ከእሷ ምን ይማራሉ?

  • የዘካርያስን እና የኤልሳቤጥን የድፍረት ምሳሌ በየትኞቹ መንገዶች መኮረጅ ትችላለህ?

በትልቁ ነገር ላይ አሰላስል

  • ይህ ታሪክ ስለ ይሖዋ ምን ያስተምረኛል?

  • ይህ ታሪክ ከይሖዋ ዓላማ ጋር ያለው ግንኙነት ምንድን ነው?

  • ዘካርያስ እና ኤልሳቤጥ ምድራዊ ትንሣኤ ካገኙ ምን ልጠይቃቸው እፈልጋለሁ?a

እውቀትህን አስፋ

ዘካርያስ አንደበቱ ሲፈታ እና የመናገር ችሎታውን ተጠቅሞ አምላክን ሲያወድስ ተመልከት።

“ስሙ ዮሐንስ ነው” (6:59)

ማርያም ኤልሳቤጥን ልትጠይቅ እንደሄደች የሚገልጸው ታሪክ ከይሖዋ ብርታት ማግኘት ስለምንችልበት መንገድ ምን ያስተምረናል?

“‘ያጠነክራችኋል’—እንዴት?’” (w23.10 14-15 አን. 10-14)

a ዘካርያስና ኤልሳቤጥ የሞቱት በ33 ዓ.ም. ከዋለው ጴንጤቆስጤ በፊት ከሆነ ከሞት የሚነሱት ምድር ላይ ነው።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2026)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2026 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ