የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mrt ርዕስ 134
  • ጠብ መፍትሔ አይሆንም

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ጠብ መፍትሔ አይሆንም
  • ተጨማሪ ርዕሰ ጉዳዮች
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ኢየሱስ ምን አስተምሯል?
  • ኢየሱስ ከዚህ በፊት ምን አድርጓል? ወደፊትስ ምን ያደርጋል?
  • “ጠላቶቻችሁን ውደዱ” ሲባል ምን ማለት ነው?
    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • ዓለም በሙሉ ሰላም ይሆናል
    ተጨማሪ ርዕሰ ጉዳዮች
  • ወርቃማው ሕግ ምንድን ነው?
    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • መልካም ማድረጋችሁን ቀጥሉ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
ለተጨማሪ መረጃ
ተጨማሪ ርዕሰ ጉዳዮች
mrt ርዕስ 134
ኢየሱስ ወንዶችን፣ ሴቶችንና ልጆችን ሲያስተምር።

ከኢየሱስ ተማሩ

ጠብ መፍትሔ አይሆንም

አሁን አሁን ሰዎች የሆነ ችግር ሲያጋጥማቸው ወይም ከሆነ ሰው ጋር መግባባት ሲያቅታቸው ወዲያው የሚሄዱት ወደ ጠብ ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ ያስተማረውም ሆነ በሕይወቱ ያሳየው ነገር ግን ከዚህ ፈጽሞ ተቃራኒ ነው። እስቲ ያስተማራቸውንና ያደረጋቸውን አንዳንድ ነገሮች እንደ ምሳሌ እንመልከት።

ኢየሱስ ምን አስተምሯል?

ኢየሱስ በስፋት በሚታወቅ አንድ ስብከቱ ላይ ቁጣ፣ ጠበኝነትና ዓመፅ ለችግሮች መፍትሔ እንደማይሆኑ አስተምሯል። ከሰጣቸው ምክሮች መካከል አንዳንዶቹን እስቲ እንመልከት፦

  • “ሰዎች እንዲያደርጉላችሁ የምትፈልጉትን ነገር ሁሉ እናንተም አድርጉላቸው።” (ማቴዎስ 7:12፤ ሉቃስ 6:31) ይህ ምክር ወርቃማው ሕግa ተብሎም ይጠራል። መቼም ማናችንም ብንሆን ሌሎች ሥርዓት በጎደለው መንገድ እንዲያነጋግሩን ወይም መጥፎ ነገር እንዲያደርጉብን አንፈልግም፤ ታዲያ እኛስ አለመግባባት በሚያጋጥመን ጊዜም ጭምር ለሁሉም ሰው አክብሮትና ደግነት ማሳየት አይኖርብንም? ኢየሱስ የመከረን እንዲህ እንድናደርግ ነው።

  • “ቀኝ ጉንጭህን በጥፊ ለሚመታህ ሌላኛውን ደግሞ አዙርለት።” (ማቴዎስ 5:38, 39፤ ሉቃስ 6:29) ኢየሱስ እንዲህ ሲል በሞኝነት ራሳችንን ለጥቃት ማጋለጥ እንዳለብን ማስተማሩ አይደለም። ከዚህ ይልቅ አጸፋ መመለስ ተገቢ ነው የሚለውን አመለካከት ማረሙ ነበር፤ በወቅቱ የነበሩ አንዳንድ የሃይማኖት መሪዎችም አጸፋ መመለስ ምንም ችግር እንደሌለው ያስተምሩ የነበረ ይመስላል። ኢየሱስ ግን ተከታዮቹ እንዲህ ሊያደርጉ እንደማይገባ፣ ይልቁንም የሚያበሳጭ ነገር ሲያጋጥማቸው ችግሩን በእርጋታ ለመፍታት መሞከር እንዳለባቸው አስተምሯል።b

  • “ጠላቶቻችሁን ውደዱ።” (ማቴዎስ 5:43, 44፤ ሉቃስ 6:27) ኢየሱስ ለሚጠሉን ወይም መጥፎ ነገር ለሚያደርጉብን ሰዎች ጭምር ደግ መሆን እንዳለብን አስተምሯል። እርግጥ እንዲህ ሲባል፣ የሚያሳዩት መጥፎ ምግባር ትክክል ነው ብለን እናስባለን ማለት አይደለም።c ሆኖም ለሚጠሉን ሰዎች ደግነት ማሳየታችን ቁጣቸው እንዲበርድ፣ አልፎ ተርፎም እነሱም በምላሹ ደግነት እንዲያሳዩን ሊያነሳሳቸው ይችላል።

ኢየሱስ ከዚህ በፊት ምን አድርጓል? ወደፊትስ ምን ያደርጋል?

ኢየሱስ ጠብ ችግሮችን ለመፍታት እንደማይረዳ አስተምሯል፤ እሱ ራሱም ቢሆን ያስተማረውን ነገር ተግባራዊ አድርጎታል። በታሰረበት ምሽት ከተከታዮቹ መካከል አንዱ እሱን ከጥቃት ለመከላከል ሲል የኃይል እርምጃ ወስዶ ነበር፤ በዚህ ጊዜ ኢየሱስ “ሰይፍህን ወደ ሰገባው መልስ፤ ሰይፍ የሚመዙ ሁሉ በሰይፍ ይጠፋሉ” ብሎታል። (ማቴዎስ 26:52) ኢየሱስ በደል የፈጸሙበትን ሰዎች ይቅር ብሏቸዋል፤ እንዲያውም ጸልዮላቸዋል! በዚህ መንገድ ጠላቶቹን እንደሚወድ አሳይቷል።—ሉቃስ 23:33, 34፤ 1 ጴጥሮስ 2:23

መጽሐፍ ቅዱስ የሰላም መስፍን የሆነው ኢየሱስ በቅርቡ ማንኛውንም ግጭት እንደሚያስወግድ ቃል ገብቷል። (ኢሳይያስ 9:6, 7) ወደፊት ስለሚመጣው አስደሳች ጊዜ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት “ጦርነት እና ግጭት የሚቀረው እንዴት ነው?” የሚለውን ርዕስ አንብብ።

a ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት “ወርቃማው ሕግ ምንድን ነው?” የሚለውን ርዕስ አንብብ

b ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት “‘ዓይን ስለ ዓይን’ ሲባል ምን ማለት ነው?” የሚለውን ርዕስ አንብብ

c ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት “‘ጠላቶቻችሁን ውደዱ’ ሲባል ምን ማለት ነው?” የሚለውን ርዕስ አንብብ

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2026)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2026 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ