የመጽሐፍ ቅዱስ ባለታሪክ
ምናሔ—መንፈሳዊ ነገሮችን አስቀድም
ምናሔ በመጀመሪያው መቶ ዘመን በአንጾኪያ ባለው ጉባኤ ውስጥ አመራር ከሚሰጡ ወንድሞች መካከል አንዱ ነበር። ምናሔ “የአውራጃ ገዢ ከሆነው ከሄሮድስ ጋር [ተምሯል]።” (ሥራ 13:1) ስለዚህ ምናሔ የተማረ ሰው ነበር፤ ያደገውም በሀብታም ቤተሰብ ውስጥ ሊሆን ይችላል።
ምናሔ እንዲህ ያለ አስተዳደግ ቢኖረውም ራሱን ለይሖዋ ለመወሰንና ጉባኤውን ለመርዳት መርጧል። የትምህርት ደረጃውንና ከባለሥልጣናት ጋር ያለውን ትውውቅ የራሱን ጥቅም ለማራመድ አልተጠቀመበትም። ከዚህ ይልቅ ወንድሞቹን አገልግሏል።
ከምናሔ ታሪክ እንደምንማረው፣ ሀብትና ክብር ከማግኘት የበለጠ ትልቅ ቦታ ሊሰጠው የሚገባው የይሖዋ አገልግሎት ነው። እንደ ምናሔ ሁሉ እኛም ከዓለማዊ ግብ የበለጠ ለመንፈሳዊ እንቅስቃሴዎች ቅድሚያ ልንሰጥ ይገባል። (ማቴ. 6:33) በተጨማሪም ትምህርት ጠቃሚ ቢሆንም “ይበልጥ አስፈላጊ የሆኑትን ነገሮች” እናስቀድማለን፤ እንዲሁም በሕይወታችን ውስጥ ያሉ ሌሎች እንቅስቃሴዎች አምልኳችንን እንዳያስተጓጉሉብን እንጠነቀቃለን።—ፊልጵ. 1:9, 10