ጥቅምት 12 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
ጥቅምት 12 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 135 እና ጸሎት
የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
bt ምዕ. 25 ከአን. 14-21 (30 ደቂቃ)
ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 1 ዜና መዋዕል 5-7 (8 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ 1 ዜና መዋዕል 6:48-60 (3 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ ክህደት ምንድን ነው?—የቃላት መፍቻ፣ nwt ገጽ 1641 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ ኤሊሁ—ጭብጥ፦ ጥበብ በሚንጸባረቅበት መንገድ ምክር መስጠት—w06 8/15 ገጽ 28 አን. 14 እስከ ገጽ 29 አን. 17 (5 ደቂቃ)
የአገልግሎት ስብሰባ፦
የወሩ ጭብጥ፦ “ሥር ሰዳችሁ” እና “በእምነት ጸንታችሁ” ኑሩ።—ቆላ. 2:6, 7
10 ደቂቃ፦ “ሥር ሰዳችሁ” እና “በእምነት ጸንታችሁ” ኑሩ። በወሩ ጭብጥ ላይ ተመሥርቶ የሚቀርብ ንግግር። ‘ሥር መስደድና በእምነት ጸንቶ መኖር’ ሲባል ምን ማለት ነው?’ ይህንንስ ተግባራዊ ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው? (የሰኔ 1, 1998 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 10-12 ተመልከት።) ቆላስይስ 2:6, 7ን፣ ዕብራውያን 6:1ንና ይሁዳ 20, 21ን አንብብና እንዴት ተግባራዊ ማድረግ እንደሚቻል አብራራ። በዚህ ወር በአገልግሎት ስብሰባ ላይ የሚቀርቡትን አንዳንድ ክፍሎች በአጭሩ ከልስ፤ እንዲሁም ከወሩ ጭብጥ ጋር ያላቸውን ተያያዥነት ግለጽ።
20 ደቂቃ፦ “በአገልግሎት ረገድ ክህሎታችንን ማዳበር—የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻችን ጥሩ የጥናት ልማድ እንዲያዳብሩ ማሠልጠን።” በውይይት የሚቀርብ። ተሞክሮ ያለው አንድ አስፋፊ ለመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቱ በመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት በመጠቀም ለመጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥያቄዎች እንዴት መልስ መስጠት እንደሚችል ሲያስረዳው የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
መዝሙር 116 እና ጸሎት