ክፍል 3
የመሲሑ እና የተከታዮቹ ዘመን
በወረቀት የሚታተመው
ይህ ክፍል የመቶ ዓመት ጊዜን የሚሸፍን ነው። መነሻችን አካባቢ ማርያም ስለተባለች ትሑት አይሁዳዊት ድንግል እናነባለን፤ ይሖዋ ፍጹም ላልሆኑ የሰው ልጆች ከሰጣቸው ተልእኮዎች ሁሉ ከባዱን በአደራ ተቀብላለች። ማሳረጊያችን የሚሆነው ደግሞ በኢየሱስ ዘንድ ተወዳጅ የሆነው ሐዋርያው ዮሐንስ ነው። እግረ መንገዳችንን እንደ መጥምቁ ዮሐንስ፣ ሐዋርያው ጴጥሮስ፣ መግደላዊቷ ማርያም፣ እስጢፋኖስና ሐዋርያው ጳውሎስ ያሉ ድንቅ የድፍረት ምሳሌዎችን እንመለከታለን። ልዩ ልዩ ፈተናዎችን በድፍረት ተጋፍጠዋል፤ አንዳንዶቹ የሚኖሩበት ማኅበረሰብ በጥቅሉ መሲሑን አልቀበልም ባለበት ወቅት ስለ እሱ አውጀዋል፤ ስደት እያለም ፈለጉን ተከትለዋል፤ እንዲሁም ተቃውሞንና ጥላቻን ተጋፍጠው ኢየሱስ ያወጀውን ምሥራች ሰብከዋል።