ሚያዝያ
ሐሙስ፣ ሚያዝያ 1
እውነተኛ ወዳጅ ምንጊዜም አፍቃሪ ነው።—ምሳሌ 17:17
መቄዶንያ ውስጥ የምትገኘው የተሰሎንቄ ክርስቲያን የሆነው አርስጥሮኮስ ለሐዋርያው ጳውሎስ ታማኝ ወዳጅ መሆኑን አሳይቷል። ስለ አርስጥሮኮስ የሚናገር ሐሳብ ለመጀመሪያ ጊዜ የምናገኘው ጳውሎስ በሦስተኛው ሚስዮናዊ ጉዞው ወቅት ኤፌሶንን እንደጎበኘ በሚገልጸው ዘገባ ላይ ነው። በወቅቱ ከጳውሎስ ጋር የነበረው አርስጥሮኮስ በቁጣ በተሞሉ ሰዎች እጅ ወደቀ። (ሥራ 19:29) በኋላ ላይ አርስጥሮኮስ ሲለቀቅ፣ አደጋ ወደሌለበት ቦታ ከመሸሽ ይልቅ በታማኝነት ከጳውሎስ ጋር ቆይቷል። ከተወሰኑ ወራት በኋላ ግሪክ ውስጥ ተቃዋሚዎች ጳውሎስን ለመግደል ሴራ እየጠነሰሱ በነበረበት ጊዜም እንኳ አርስጥሮኮስ ከጎኑ አልተለየም። (ሥራ 20:2-4) በ58 ዓ.ም. ገደማ ጳውሎስ እስረኛ ሆኖ ወደ ሮም በተወሰደበት ወቅት አርስጥሮኮስ ረጅሙን መንገድ አብሮት ተጉዟል፤ ጳውሎስ በጉዞው ላይ የመርከብ አደጋ በገጠመው ወቅት አርስጥሮኮስ አብሮት ነበር። (ሥራ 27:1, 2, 41) ሮም ከደረሱ በኋላም ለተወሰነ ጊዜ ያህል ከጳውሎስ ጋር ታስሮ የነበረ ይመስላል። (ቆላ. 4:10) በእርግጥም ጳውሎስ እንዲህ ባለው ታማኝ አጋሩ መበረታታቱና መጽናናቱ አያስገርምም! እንደ አርስጥሮኮስ ሁሉ እኛም በደህናው ጊዜ ብቻ ሳይሆን ‘በመከራ ቀንም’ ከወንድሞቻችንና ከእህቶቻችን ጎን በመቆም ታማኝ ወዳጅ ልንሆናቸው እንችላለን። w20.01 9 አን. 4-5
ዓርብ፣ ሚያዝያ 2
በመጀመሪያው ትንሣኤ ተካፋይ የሆኑ ሁሉ ደስተኞችና ቅዱሳን ናቸው።—ራእይ 20:6
በመንፈስ ቅዱስ የተቀባ ክርስቲያን ይህን ውድ መብት ለማግኘት እንደማይበቃ ይሰማው ይሆናል። ይሁንና ይሖዋ እንደመረጠው ለቅጽበትም እንኳ አይጠራጠርም። ስለ ወደፊት ተስፋው ሲያስብ ልቡ በደስታና በአድናቆት ይሞላል። (1 ጴጥ. 1:3, 4) ይህ ሲባል ግን ቅቡዓኑ መሞት ይፈልጋሉ ማለት ነው? ሐዋርያው ጳውሎስ ለዚህ ጥያቄ መልስ ሰጥቶናል። የቅቡዓንን ሥጋዊ አካል ከድንኳን ጋር በማነጻጸር እንዲህ ብሏል፦ “እንዲያውም በዚህ ድንኳን ውስጥ ያለነው እኛ ከባድ ሸክም ተጭኖን እንቃትታለን፤ ምክንያቱም ዘላለማዊው ሕይወት ሟች የሆነውን አካል እንዲተካ ይህን ድንኳን ማውለቅ ሳይሆን ሰማያዊውን መኖሪያ መልበስ እንፈልጋለን።” (2 ቆሮ. 5:4) እነዚህ ክርስቲያኖች ይሄኛው ሕይወት ስለሰለቻቸው ቶሎ እንዲያከትም ይፈልጋሉ ማለት አይደለም። እንዲያውም በሕይወታቸው የሚደሰቱ ከመሆኑም ሌላ እያንዳንዱን ቀን ከቤተሰባቸውና ከወዳጆቻቸው ጋር በይሖዋ አገልግሎት ማሳለፍ ይፈልጋሉ። ያም ሆኖ በየትኛውም እንቅስቃሴ ሲካፈሉ፣ ወደፊት የሚጠብቃቸው አስደናቂ ተስፋ ከአእምሯቸው አይጠፋም።—1 ቆሮ. 15:53፤ 2 ጴጥ. 1:4፤ 1 ዮሐ. 3:2, 3፤ w20.01 23 አን. 12-13
ቅዳሜ፣ ሚያዝያ 3
ይሖዋ የሚወዳቸውን ይገሥጻል።—ዕብ. 12:6
አፍቃሪው አባታችን እኛን ለማሠልጠን ሲል አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ ተግሣጽ ይሰጠናል። ይህን የሚያደርገው በተለያዩ መንገዶች ነው። ለምሳሌ ያህል፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የምናነበው ነገር ወይም በስብሰባዎች ላይ የምናዳምጠው ትምህርት ማስተካከያ እንደሚያስፈልገን ሊጠቁመን ይችላል። አሊያም ደግሞ ሽማግሌዎች የሚያስፈልገንን እርዳታ ሊሰጡን ይችላሉ። ይሖዋ ተግሣጽ የሚሰጥበት መንገድ ምንም ይሁን ምን፣ ምንጊዜም ይህን የሚያደርገው በፍቅር ተነሳስቶ ነው። (ኤር. 30:11) ይሖዋ መከራ ሲያጋጥመን እንድንጸና ይረዳናል። አፍቃሪ የሆነ ሰብዓዊ አባት ልጆቹ ችግር ሲገጥማቸው እንደሚደግፋቸው ሁሉ ሰማያዊው አባታችንም መከራ ሲያጋጥመን ይረዳናል። መንፈሳዊ ጉዳት እንዳይደርስብን በቅዱስ መንፈሱ አማካኝነት ይጠብቀናል። (ሉቃስ 11:13) ተስፋ በምንቆርጥበት ወይም በምንጨነቅበት ጊዜም ይሖዋ ከአሉታዊ ስሜቶች ጥበቃ ያደርግልናል። ለምሳሌ፣ አስደናቂ የሆነ ተስፋ ሰጥቶናል። ይህ ተስፋ አስቸጋሪ ሁኔታዎችን በጽናት እንድንቋቋም ይረዳናል። እስቲ አስበው፦ አፍቃሪው አባታችን ሊያስተካክለው የማይችለው ምንም ዓይነት ጉዳት ሊደርስብን አይችልም። የሚያጋጥመን ማንኛውም ችግር ጊዜያዊ ነው፤ ይሖዋ የሚያመጣው በረከት ግን ዘላለማዊ ነው።—2 ቆሮ. 4:16-18፤ w20.02 5 አን. 14-15
እሁድ፣ ሚያዝያ 4
በውስጣችን ያደረው መንፈስ በቅናት ሁልጊዜ ይመኛል።—ያዕ. 4:5
ምቀኝነትን ለማስወገድ በምናደርገው ጥረት ሊሳካልን ይችላል! የዮሴፍን ወንድሞች ታሪክ እንመልከት። በዮሴፍ ላይ በደል ከፈጸሙ ከዓመታት በኋላ ግብፅ ውስጥ አገኙት። ዮሴፍ ማንነቱን ለወንድሞቹ ከመግለጡ በፊት፣ ባሕርያቸው ተለውጦ እንደሆነ ለማየት ፈተናቸው። ምግብ እንዲቀርብ ካደረገ በኋላ ለታናሽ ወንድማቸው ለቢንያም ከእነሱ እጅግ የላቀ ድርሻ እንዲሰጠው አዘዘ። (ዘፍ. 43:33, 34) ያም ቢሆን ወንድሞቹ ቢንያምን እንደተመቀኙት የሚጠቁም ነገር የለም። እንዲያውም ለወንድማቸውና ለአባታቸው ለያዕቆብ ከልብ እንደሚያስቡ አሳይተዋል። (ዘፍ. 44:30-34) የዮሴፍ ወንድሞች ምቀኝነትን ማስወገድ ስለቻሉ የቤተሰቡ ሰላም ተመልሷል። (ዘፍ. 45:4, 15) እኛም በተመሳሳይ የምቀኝነት ዝንባሌን ከውስጣችን ነቅለን የምናስወግድ ከሆነ የቤተሰባችንንም ሆነ የጉባኤያችንን ሰላም መጠበቅ እንችላለን። ይሖዋ ምቀኝነትን እንድንዋጋ እና ሰላም እንዲሰፍን ለማድረግ እንድንጥር ይፈልጋል። ትሑት፣ ባለን የምንረካና አመስጋኝ ከሆንን ምቀኝነት ቦታ አያገኝም። w20.02 19 አን. 17-18
ሰኞ፣ ሚያዝያ 5
ይሖዋ ድምፄን፣ እርዳታ ለማግኘት የማቀርበውን ልመና ስለሚሰማ እወደዋለሁ።—መዝ. 116:1
ለይሖዋ ፍቅር ምላሽ መስጠት የምትችልበት አንዱ መንገድ እሱን በጸሎት ማነጋገር ነው። የሚያሳስብህን ነገር ስትነግረው እንዲሁም ስላደረገልህ ነገር ሁሉ ስታመሰግነው ለአምላክ ያለህ ፍቅር ያድጋል። ለጸሎትህ ምላሽ የሚሰጥበትን መንገድ ስትመለከት ደግሞ በመካከላችሁ ያለው ወዳጅነት ይጠናከራል። ስሜትህን እንደሚረዳልህ እርግጠኛ መሆን ትጀምራለህ። ይሁንና ወደ ይሖዋ ይበልጥ መቅረብ ከፈለግክ አንተም የእሱን አስተሳሰብ ልትረዳ ይገባል። እንዲሁም ከአንተ ምን እንደሚጠብቅ ማወቅ ይኖርብሃል። ይህን ማወቅ የምትችልበት ብቸኛው መንገድ ቃሉን መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናት ነው። እንግዲያው ለመጽሐፍ ቅዱስ አድናቆት አዳብር። ስለ ይሖዋና ለአንተ ስላለው ዓላማ እውነቱን መማር የምትችለው ከመጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ነው። መጽሐፍ ቅዱስን በየዕለቱ በማንበብ፣ ለጥናትህ በመዘጋጀት እንዲሁም የተማርከውን ነገር በሥራ ላይ በማዋል ለመጽሐፍ ቅዱስ አድናቆት እንዳለህ ማሳየት ትችላለህ። (መዝ. 119:97, 99፤ ዮሐ. 17:17) መጽሐፍ ቅዱስን በግልህ የምታነብበት ፕሮግራም አለህ? ፕሮግራምህን ጠብቀህ በየዕለቱ መጽሐፍ ቅዱስን ታነብባለህ? w20.03 5 አን. 8-9
ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 6
ከሚያገኛቸው ሰዎች ጋር ይወያይ ጀመር።—ሥራ 17:17
ብዙ መራመድ የሚከብድህ ከሆነ፣ ሰው በሚበዛበት ቦታ ተቀምጠህ ለአላፊ አግዳሚው መስበክ ትችል ይሆናል። አሊያም መደበኛ ባልሆነ መንገድ፣ በደብዳቤ ወይም በስልክ መመሥከር ትችላለህ። ከባድ የአቅም ገደብ ያለባቸው በርካታ አስፋፊዎች በእነዚህ ተጨማሪ የአገልግሎት ዘርፎች በመካፈል ከፍተኛ ደስታና እርካታ ማግኘት ችለዋል። የጤና እክል ቢኖርብህም አገልግሎትህን በተሟላ ሁኔታ መፈጸም ትችላለህ። ጳውሎስ “ኃይልን በሚሰጠኝ በእሱ አማካኝነት ለሁሉም ነገር የሚሆን ብርታት አለኝ” ብሏል። (ፊልጵ. 4:13) ጳውሎስ ከሚስዮናዊ ጉዞዎቹ በአንዱ ላይ የጤና እክል ባጋጠመው ጊዜ ይህ ኃይል አስፈልጎት ነበር። በገላትያ ላሉ ክርስቲያኖች “ለመጀመሪያ ጊዜ ለእናንተ ምሥራቹን ለመስበክ አጋጣሚ ያገኘሁት በመታመሜ የተነሳ [ነበር]” ብሏቸዋል። (ገላ. 4:13) አንተም ያለብህ የጤና እክል ለሐኪሞች፣ ለነርሶችና ለሚንከባከቡህ ሰዎች ምሥራቹን የምትሰብክበት አጋጣሚ ሊከፍትልህ ይችላል። እነዚህ ሰዎች አብዛኛውን ጊዜ ሥራ ቦታ ስለሚውሉ አስፋፊዎች ከቤት ወደ ቤት ሲያገለግሉ አያገኟቸውም። w19.04 4-5 አን. 10-11
ረቡዕ፣ ሚያዝያ 7
የክርስቶስ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርት በመሆን ለአምላክ ያደሩ ሆነው መኖር የሚፈልጉ ሁሉ ስደት ይደርስባቸዋል።—2 ጢሞ. 3:12
በ2018 መንፈሳዊ እንቅስቃሴያችን ሙሉ በሙሉ በታገደባቸው አሊያም በሥራችን ላይ አንዳንድ ገደቦች በተጣሉባቸው አገሮች ውስጥ የሚኖሩ ከ223,000 የሚበልጡ የምሥራቹ አስፋፊዎች ነበሩ። ይህ መሆኑ አያስገርመንም። እውነተኛ ክርስቲያኖች ስደት እንደሚደርስባቸው ይጠብቃሉ። የምንኖረው የትም ይሁን የት፣ ባለሥልጣናት ለአፍቃሪው አምላካችን ለይሖዋ በምናቀርበው አምልኮ ላይ ሳናስበው በድንገት እገዳ ሊጥሉ ይችላሉ። መንግሥት በአምልኳችን ላይ እገዳ ቢጥል ‘የአምላክን በረከት አጥተናል’ የሚል የተሳሳተ መደምደሚያ ላይ እንደርስ ይሆናል። ይሁን እንጂ ስደት ይሖዋ እንዳዘነብን የሚያሳይ ነገር እንዳልሆነ እናስታውስ። ሐዋርያው ጳውሎስን እንደ ምሳሌ እንውሰድ። ጳውሎስ የአምላክን ሞገስ ያገኘ ሰው እንደሆነ ጥያቄ የለውም። በክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍት ውስጥ ያሉ 14 ደብዳቤዎችን የመጻፍ መብት ያገኘ ከመሆኑም ሌላ ለአሕዛብ የተላከ ሐዋርያ ነበር። ያም ቢሆን ከባድ ስደት ደርሶበት ነበር። (2 ቆሮ. 11:23-27) ሐዋርያው ጳውሎስ ካጋጠመው ነገር እንደምንማረው ይሖዋ፣ ታማኝ አገልጋዮቹ ስደት እንዲደርስባቸው ይፈቅዳል። w19.07 8 አን. 1, 3
ሐሙስ፣ ሚያዝያ 8
የምንታገለው . . . በሰማያዊ ስፍራ ካሉ ከክፉ መንፈሳዊ ኃይሎች ጋር ነው።—ኤፌ. 6:12
ይሖዋ ለአገልጋዮቹ በጥልቅ እንደሚያስብ ከሚያሳይባቸው መንገዶች መካከል አንዱ ጠላቶቻቸውን እንዲቃወሙ የሚረዳቸው መሆኑ ነው። ቀንደኛ ጠላቶቻችን ደግሞ ሰይጣንና አጋንንቱ ናቸው። ይሖዋ እነዚህን ጠላቶች በተመለከተ ያስጠነቀቀን ከመሆኑም ሌላ እነሱን ለመቋቋም እርዳታ እየሰጠን ነው። (ኤፌ. 6:10-13) የይሖዋን እርዳታ የምንቀበልና ሙሉ በሙሉ በእሱ የምንታመን ከሆነ ዲያብሎስን በመቃወም ረገድ ሊሳካልን ይችላል። እኛም ልክ እንደ ሐዋርያው ጳውሎስ “አምላክ ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ሊቃወመን ይችላል?” ብለን በልበ ሙሉነት መናገር እንችላለን። (ሮም 8:31) እውነተኛ ክርስቲያኖች እንደመሆናችን መጠን ስለ ሰይጣንና ስለ አጋንንቱ ለማወቅ አንጓጓም። በዋነኝነት ትኩረት የምናደርገው ስለ ይሖዋ በመማርና እሱን በማገልገል ላይ ነው። (መዝ. 25:5) ያም ቢሆን ሰይጣን ስለሚያደርጋቸው ነገሮች መሠረታዊ እውቀት ማግኘታችን አስፈላጊ ነው። ለምን? እንዲህ ያለው እውቀት በሰይጣን እንዳንታለል ስለሚረዳን ነው።—2 ቆሮ. 2:11 ግርጌ፤ w19.04 20 አን. 1-2
ዓርብ፣ ሚያዝያ 9
ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ፣ ለመናገር የዘገየ . . . መሆን አለበት።—ያዕ. 1:19
አንድ ሰው ያስጨነቀውን ነገር በሚነግረን ጊዜ ጥሩ አድማጮች ነን? ሌሎችን ማዳመጥ ሲባል ምንም ነገር ሳንናገር ዓይን ዓይናቸውን ከማየት ያለፈ ነገር ይጠይቃል። ሌሎችን በምናዳምጥበት ጊዜ፣ አዘኔታና ርኅራኄ ማሳየት እንችላለን። አንዳንድ ጊዜ፣ አሳቢነት የሚንጸባረቅባቸው ጥቂት የተመረጡ ቃላትን መናገራችን ብቻ ስሜታችንን ሊገልጽ ይችላል። ለምሳሌ እንዲህ ልትሉ ትችላላችሁ፦ “የደረሰብህ ነገር በጣም ያሳዝናል!” ምናልባትም በጭንቀት የተዋጠው ወንድማችሁ የተናገረውን ነገር እንደተረዳችሁለት ለማረጋገጥ አንድ ወይም ሁለት ጥያቄዎችን ልትጠይቁት ትችላላችሁ። ለምሳሌ “ምን ማለትህ እንደሆነ ልታስረዳኝ ትችላለህ?” አሊያም “እንዲህ ስትል እኔ የገባኝ እንደዚህ ነው። በትክክል ተረድቼሃለሁ?” በማለት ልትጠይቁት ትችላላችሁ። እንዲህ ያሉት ፍቅር የሚንጸባረቅባቸው አገላለጾች ግለሰቡ በጥሞና እያዳመጣችሁት እንዳላችሁና ስሜቱን መረዳት እንደምትፈልጉ እንዲገነዘብ ሊያደርጉት ይችላሉ። (1 ቆሮ. 13:4, 7) ሆኖም ምንጊዜም ‘ለመናገር የዘገያችሁ’ መሆን እንዳለባችሁ አስታውሱ። ግለሰቡ ሲናገር አቋርጣችሁ ምክር ለመስጠት ወይም አመለካከቱን ለማስተካከል አትሞክሩ። እንዲሁም ትዕግሥተኞች ሁኑ! የመፍትሔ ሐሳብ ለማቅረብ ከመሞከር ይልቅ አዘኔታና ርኅራኄ ለማሳየት ጥረት እናደርጋለን።—1 ጴጥ. 3:8፤ w19.05 17-18 አን. 15-17
ቅዳሜ፣ ሚያዝያ 10
ባሎች ሆይ፣ ክርስቶስ ጉባኤውን እንደወደደና ራሱን ለጉባኤው አሳልፎ እንደሰጠ ሁሉ እናንተም ሚስቶቻችሁን መውደዳችሁን ቀጥሉ።—ኤፌ. 5:25
“ክርስቶስ ጉባኤውን እንደወደደ” ሁሉ በቤተሰብ ውስጥ ባሎችም ሚስቶቻቸውን መውደድ ይኖርባቸዋል። (ኤፌ. 5:28, 29) አንድ ባል ከራሱ ይልቅ የሚስቱን ፍላጎት በማስቀደም ልክ እንደ ኢየሱስ፣ ከራስ ወዳድነት ነፃ የሆነ ፍቅር ማሳየት አለበት። አንዳንድ ወንዶች እንዲህ ዓይነት ፍቅር ማሳየት ይከብዳቸው ይሆናል፤ ለዚህ አንዱ ምክንያት፣ ባደጉበት ማኅበረሰብ ውስጥ ሌሎችን በፍቅርና በአክብሮት መያዝ ስላልተለመደ ሊሆን ይችላል። እነዚህ ሰዎች እንዲህ ያለውን መጥፎ ባሕርይ ማስወገድ ከባድ ሊሆንባቸው ቢችልም የክርስቶስን ሕግ መታዘዝ ከፈለጉ ይህን ለውጥ ለማድረግ ፈቃደኞች መሆን አለባቸው። ከራስ ወዳድነት ነፃ የሆነ ፍቅር የሚያሳይ ባል የሚስቱን አክብሮት ያተርፋል። ልጆቹን ከልቡ የሚወድ አባት፣ በንግግሩም ሆነ በድርጊቱ በልጆቹ ላይ በደል አይፈጽምም። (ኤፌ. 4:31) ከዚህ ይልቅ ፍቅሩንና አድናቆቱን በመግለጽ ልጆቹ የደህንነትና የመረጋጋት ስሜት እንዲሰማቸው ያደርጋል። እንዲህ ያለው አባት የልጆቹን ፍቅርና አመኔታ ያተርፋል። w19.05 6 አን. 21
እሁድ፣ ሚያዝያ 11
ይሖዋ አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል፤ በያዕቆብ ቤትም ላይ ለዘላለም ንጉሥ ሆኖ ይገዛል።—ሉቃስ 1:32, 33
ማርያም ገብርኤል የተናገራቸውን እነዚህን ቃላት ስትሰማ ምን ስሜት አድሮባት ሊሆን ይችላል? ገብርኤል ከተናገረው ሐሳብ በመነሳት ኢየሱስ ንጉሥ ሄሮድስን ወይም ከእሱ በኋላ በእስራኤል ላይ ከሚነግሡት ገዢዎች መካከል አንዱን ተክቶ እንደሚነግሥ አስባ ይሆን? ኢየሱስ ንጉሥ ከሆነ ማርያም የንጉሥ እናት የመሆን ክብር የምታገኝ ከመሆኑም ሌላ ከቤተሰቧ ጋር በቤተ መንግሥት ውስጥ ትኖራለች ማለት ነው። ሆኖም ማርያም በመንግሥቱ ውስጥ ለየት ያለ ቦታ እንዲሰጣት እንደጠየቀች የሚገልጽ ዘገባ አናገኝም። በእርግጥም ማርያም በጣም ትሑት ሴት ነበረች! የአምላክን ቃልም ሆነ ክርስቲያናዊ ጽሑፎቻችንን የምናጠናበት ዋነኛ ዓላማ ወደ ይሖዋ ይበልጥ መቅረብ እንደሆነ እናስታውስ። በተጨማሪም በአምላክ ፊት ‘ምን እንደምንመስል’ በትክክል ማወቅና እሱን ለማስደሰት የትኞቹን ለውጦች ማድረግ እንዳለብን መረዳት እንፈልጋለን። (ያዕ. 1:22-25፤ 4:8) እንግዲያው ምንጊዜም ማጥናት ከመጀመራችን በፊት ይሖዋ መንፈሱን እንዲሰጠን መጸለያችን አስፈላጊ ነው። ይሖዋ ከምናጠናው ነገር ሙሉ ተጠቃሚ መሆንና እሱ በሚያየን መንገድ ራሳችንን ማየት እንድንችል ይረዳን ዘንድ ልንለምነው ይገባል። w19.05 31 አን. 18-19
ሰኞ፣ ሚያዝያ 12
ብዙ ጭንቀት [አለብኝ]።—1 ሳሙ. 1:15
አንዳንድ ጊዜ በርካታ ችግሮች ይደራረቡብናል። እስቲ አንዳንዶች ያጋጠሟቸውን ሁኔታዎች እንመልከት። ጆን የተባለ ወንድም መልቲፕል ስክለሮሲስ የሚባል ሕመም አለበት፤ በዚያ ላይ ደግሞ ለ19 ዓመታት አብራው የኖረችው የትዳር ጓደኛው ጥላው ሄደች፤ ይህ ሁኔታ ስሜቱን በጣም ጎድቶት ነበር። ከዚያም ሁለት ሴቶች ልጆቹ ይሖዋን ማገልገላቸውን አቆሙ። ቦብ እና ሊንዳ የተባሉት ባልና ሚስት ያጋጠሟቸው ችግሮች ደግሞ ከዚህ ይለያሉ። ሁለቱም ከሥራቸው ተፈናቀሉ፤ በኋላ ላይ ደግሞ ቤታቸውን ለመልቀቅ ተገደዱ። ይህም እንዳይበቃ፣ ሊንዳ ለሕይወት አስጊ የሆነ የልብ በሽታ እንዳለባት ተነገራት፤ ከዚህም ሌላ በሽታ የመከላከል አቅሟን የሚያዳክም የጤና እክል አጋጠማት። ፈጣሪያችንና አፍቃሪው አባታችን ይሖዋ፣ የሚያስጨንቅ ሁኔታ ሲያጋጥመን የሚሰማንን ስሜት እንደሚረዳልን መተማመን እንችላለን። ደግሞም ይሖዋ የሚያጋጥሙንን ችግሮች መቋቋም እንድንችል ሊረዳን ይፈልጋል። (ፊልጵ. 4:6, 7) የይሖዋ አገልጋዮች በጽናት ስለተወጧቸው ችግሮች የሚገልጹ በርከት ያሉ ዘገባዎችን በአምላክ ቃል ውስጥ እናገኛለን። በተጨማሪም የአምላክ አገልጋዮች ያጋጠማቸውን አስጨናቂ ሁኔታ እንዲቋቋሙ ይሖዋ የረዳቸው እንዴት እንደሆነ በቃሉ ውስጥ ሰፍሯል። w19.06 14 አን. 2-3
ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 13
እውነተኛ ወዳጅ ምንጊዜም አፍቃሪ ነው፤ ደግሞም ለመከራ ቀን የተወለደ ወንድም ነው።—ምሳሌ 17:17
በተለያየ ምክንያት የትዳር ጓደኛቸውን ላጡ ሰዎች በትናንሽ ነገሮች ደግነት ስናሳይ፣ እንደምንወዳቸው እናረጋግጥላቸዋለን። እነዚህ ሰዎች ከመቼውም ጊዜ ይበልጥ ጥሩ ወዳጆች ያስፈልጓቸዋል። ታዲያ ወዳጅ ልትሆኗቸው የምትችሉት እንዴት ነው? ቀለል ያለ ምግብ ሠርታችሁ ቤታችሁ ልትጋብዟቸው ትችላላችሁ። አብረዋችሁ እንዲዝናኑ ወይም ከእናንተ ጋር አገልግሎት እንዲወጡ ልትጠይቋቸው ትችሉ ይሆናል። አሊያም ደግሞ በቤተሰብ አምልኮ ፕሮግራማችሁ ላይ እንዲገኙ አልፎ አልፎ ጋብዟቸው። እንዲህ ስታደርጉ “ልባቸው ለተሰበረ ቅርብ” እንዲሁም ‘ለመበለቶች ጠባቂ’ የሆነውን የይሖዋን ልብ ደስ ታሰኛላችሁ። (መዝ. 34:18፤ 68:5) የአምላክ መንግሥት በቅርቡ ምድርን መግዛት ሲጀምር “የሚያስጨንቁ ነገሮች [ሁሉ] ይረሳሉ።” “የቀድሞዎቹ ነገሮች አይታሰቡም፤ ወደ ልብም አይገቡም” የተባለለትን ጊዜ መምጣት በጉጉት እንጠባበቃለን። (ኢሳ. 65:16, 17) ያ ጊዜ እስኪመጣ ግን እርስ በርስ መደጋገፋችንን እና የመንፈሳዊ ቤተሰባችንን አባላት በሙሉ እንደምንወዳቸው በቃልም ሆነ በተግባር ማሳየታችንን እንቀጥል።—1 ጴጥ. 3:8፤ w19.06 25 አን. 18-19
ረቡዕ፣ ሚያዝያ 14
ይሖዋ ረዳቴ ነው፤ አልፈራም።—ዕብ. 13:6
ከበርካታ ዓመታት በፊት በመጠበቂያ ግንብ ላይ “በፈተና ወቅት በአምላክ ይበልጥ የሚታመነው፣ አምላክን በሚገባ የሚያውቀው ሰው ነው” የሚል ሐሳብ ወጥቶ ነበር። ይህ በእርግጥም እውነት ነው! ስደት ሲደርስብን መጽናት ከፈለግን ይሖዋን መውደድና በእሱ ሙሉ በሙሉ መታመን ይኖርብናል። (ማቴ. 22:36-38፤ ያዕ. 5:11) ወደ ይሖዋ ይበልጥ የመቅረብ ግብ ይዛችሁ መጽሐፍ ቅዱስን በየዕለቱ አንብቡ። (ያዕ. 4:8) መጽሐፍ ቅዱስን ስታነቡ፣ የይሖዋን ፍቅር በሚያንጸባርቁት ባሕርያቱ ላይ ትኩረት አድርጉ። ይሖዋ የተናገራቸው ወይም ያደረጋቸው ነገሮች ፍቅሩን የሚያሳዩት እንዴት እንደሆነ አስተውሉ። (ዘፀ. 34:6) ፍቅር አግኝተው የማያውቁ አንዳንድ ሰዎች፣ አምላክ እንደሚወዳቸው መቀበል ይከብዳቸው ይሆናል። አንተም እንዲህ የሚሰማህ ከሆነ የይሖዋን ምሕረትና ደግነት ያየኸው በየትኞቹ መንገዶች እንደሆነ በየዕለቱ በዝርዝር ጻፍ። (መዝ. 78:38, 39፤ ሮም 8:32) ስለ ራሳችሁ ሕይወት ስታስቡ እንዲሁም ከአምላክ ቃል ባነበባችሁት ነገር ላይ ስታሰላስሉ ይሖዋ ያደረገላችሁን ብዙ ነገሮች መዘርዘር ትችላላችሁ። ይሖዋ ላደረገላችሁ ነገሮች ያላችሁ አድናቆት እየጨመረ ሲሄድ ከእሱ ጋር ያላችሁ ዝምድናም ይበልጥ ይጠናከራል።—መዝ. 116:1, 2፤ w19.07 2-3 አን. 4-5
ሐሙስ፣ ሚያዝያ 15
ጸንታችሁ የቆማችሁት በራሳችሁ እምነት ስለሆነ እኛ ለደስታችሁ ከእናንተ ጋር የምንሠራ ነን እንጂ በእምነታችሁ ላይ የምናዝ አይደለንም።—2 ቆሮ. 1:24
ይሖዋ ለሌሎች የግል ውሳኔ የማድረግ ሥልጣን አልሰጠንም። አላስፈላጊ ደንቦችን የሚያወጣ ሰው ወንድሙን ከአደጋ እየጠበቀ ሳይሆን በወንድሙ እምነት ላይ እያዘዘ ነው። ሰይጣን ዲያብሎስ በይሖዋ ታማኝ አገልጋዮች ላይ ስደት ለማድረስ የሚያደርገውን ጥረት አያቆምም። (1 ጴጥ. 5:8፤ ራእይ 2:10) ሰይጣንና ወኪሎቹ ለይሖዋ በምናቀርበው አምልኮ ላይ እገዳ ለመጣል መሞከራቸውን ይቀጥላሉ። ያም ቢሆን በፍርሃት የምንርድበት ምንም ምክንያት የለም! (ዘዳ. 7:21) ይሖዋ ከእኛ ጋር ነው፤ ሥራችን ቢታገድም እንኳ እኛን መደገፉን ይቀጥላል። (2 ዜና 32:7, 8) በመጀመሪያው መቶ ዘመን የነበሩት ወንድሞቻችን በዘመኑ ለነበሩት ባለሥልጣናት እንዲህ ብለዋቸው ነበር፦ “አምላክን ከመስማት ይልቅ እናንተን መስማት በአምላክ ፊት ተገቢ እንደሆነና እንዳልሆነ እስቲ እናንተው ፍረዱ። እኛ ግን ስላየነውና ስለሰማነው ነገር ከመናገር ወደኋላ ማለት አንችልም።” እኛም እንዲህ ዓይነት ቁርጥ አቋም ይኑረን።—ሥራ 4:19, 20፤ w19.07 12-13 አን. 18-20
ዓርብ፣ ሚያዝያ 16
በሰው ልብ ውስጥ ያለ ሐሳብ እንደ ጥልቅ ውኃ ነው፤ አስተዋይ ሰው ግን ቀድቶ ያወጣዋል።—ምሳሌ 20:5
በምንሰብክበት ወቅት በምናነጋግራቸው ሰዎች አመለካከት ላይ ተጽዕኖ ያሳደሩትን ነገሮች ለመረዳት መሞከር ይኖርብናል። ሐዋርያው ጳውሎስ ያደገው በአይሁዳውያን መካከል ነው። በመሆኑም ለአሕዛብ ሲሰብክ፣ የሚሰብክበትን መንገድ ማስተካከል አስፈልጎት እንደሚሆን ጥርጥር የለውም፤ ምክንያቱም እነዚህ ሰዎች ስለ ይሖዋም ሆነ ስለ ቅዱሳን መጻሕፍት ቢያውቁ እንኳ እውቀታቸው በጣም ውስን ነው። እኛም በክልላችን ውስጥ ያሉትን ሰዎች አመለካከትና ስሜት መረዳት እንድንችል ምርምር ማድረግ አሊያም በጉባኤያችን የሚገኙ ተሞክሮ ያላቸው ክርስቲያኖችን ማማከር ያስፈልገን ይሆናል። (1 ቆሮ. 9:20-23) ዓላማችን “መልእክቱን መስማት የሚገባውን ሰው” ማግኘት ነው። (ማቴ. 10:11) በዚህ ረገድ ውጤታማ ለመሆን፣ ሰዎች አመለካከታቸውን እንዲገልጹ መጠየቅ ከዚያም በጥሞና ማዳመጥ ይኖርብናል። በእንግሊዝ የሚኖር አንድ ወንድም ሰዎችን በሚያነጋግርበት ጊዜ የትዳር ሕይወትን አስደሳች ማድረግ፣ ጨዋ ልጆች ማሳደግ አሊያም ደግሞ ግፍ ሲፈጸምብን መቋቋም የሚቻለው እንዴት እንደሆነ አመለካከታቸውን ይጠይቃቸዋል። የሚሰጡትን ሐሳብ ካዳመጠ በኋላ “ከዛሬ 2,000 ዓመት ገደማ በፊት የተጻፈ ምክር ባሳይህ ደስ ይለኛል” ይላቸዋል። ከዚያም ከመጽሐፍ ቅዱስ እየጠቀሰ እንደሆነ ሳይናገር፣ አስቀድሞ የተዘጋጃቸውን ጥቅሶች ከስልኩ ላይ ያሳያቸዋል። w19.07 21-22 አን. 7-8
ቅዳሜ፣ ሚያዝያ 17
አምላክ ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ እንዲሞትልን በማድረግ ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር አሳይቷል።—ሮም 5:8
አምላክን ምን ያህል ልንወደው ይገባል? ኢየሱስ ለአንድ ፈሪሳዊ “አምላክህን ይሖዋን በሙሉ ልብህ፣ በሙሉ ነፍስህና በሙሉ አእምሮህ ውደድ” ብሎታል። (ማቴ. 22:36, 37) አምላክን የምንወደው በተከፈለ ልብ መሆን የለበትም። ከዚህ ይልቅ ለእሱ ያለን ፍቅር በየቀኑ እየጨመረ እንዲሄድ እንፈልጋለን። አምላክን ለመውደድ እሱን ማወቅ ያስፈልገናል። መጽሐፍ ቅዱስ “ፍቅር የማያሳይ አምላክን አያውቅም፤ ምክንያቱም አምላክ ፍቅር ነው” ይላል። (1 ዮሐ. 4:8) ሐዋርያው ጳውሎስ ስለ አምላክ “ትክክለኛ እውቀትና ጥልቅ ግንዛቤ” ባገኘን መጠን ለእሱ ያለን ፍቅር ይበልጥ እያደገ እንደሚሄድ ተናግሯል። (ፊልጵ. 1:9) መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናት በጀመርንበት ወቅት ስለ አምላክ ግሩም ባሕርያት ያገኘነው ውስን እውቀት እሱን እንድንወደው አድርጎናል። ስለ ይሖዋ ይበልጥ እየተማርን ስንሄድ ደግሞ ለእሱ ያለን ፍቅር ይበልጥ እየጨመረ መጥቷል። ከዚህ አንጻር፣ ዘወትር መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናትና በአምላክ ቃል ላይ ማሰላሰል በሕይወታችን ውስጥ ትልቅ ቦታ የምንሰጠው ነገር መሆኑ የሚያስገርም አይደለም!—ፊልጵ. 2:16፤ w19.08 9 አን. 4-5
እሁድ፣ ሚያዝያ 18
አንድ ከመሆን ሁለት መሆን ይሻላል።—መክ. 4:9
በአዲስ ምድብ ላይ እያገለገላችሁ ከሆነ ወዳጆች ያስፈልጓችኋል። ጓደኛ ማግኘት ከፈለጋችሁ እናንተ ራሳችሁ ለሌሎች ጥሩ ጓደኛ መሆን እንዳለባችሁ አስታውሱ። በይሖዋ አገልግሎት ስላሳለፋችሁት አስደሳች ሕይወት በመናገር ሌሎች ደስታችሁን እንዲያዩ አድርጉ። በአገልግሎት ምድባችሁ ላይ መቀጠል ያልቻላችሁት፣ የትዳር ጓደኛህ የጤና እክል ስለገጠማት ከሆነ ባለቤትህን አትውቀሳት። የጤና እክል ያጋጠመህ አንተ ከሆንክ ደግሞ ለትዳር ጓደኛህ እንቅፋት እንደሆንክባት በማሰብ ራስህን አትውቀስ። “አንድ ሥጋ” እንደሆናችሁና ምንም ዓይነት ነገር ቢያጋጥማችሁ አንዳችሁ ሌላውን ለመንከባከብ በይሖዋ ፊት ቃል እንደገባችሁ አትዘንጉ። (ማቴ. 19:5, 6) አገልግሎታችሁን ያቆማችሁት ባልታቀደ እርግዝና ምክንያት ከሆነ ደግሞ ልጃችሁን ከአገልግሎት ምድባችሁ ይበልጥ ከፍ አድርጋችሁ እንደምትመለከቱት አረጋግጡለት። ከይሖዋ እንዳገኛችሁት “ስጦታ” አድርጋችሁ እንደምታዩት ለልጃችሁ ንገሩት። (መዝ. 127:3-5) በሌላ በኩል ደግሞ በአገልግሎት ምድባችሁ ላይ ያገኛችኋቸውን አስደሳች ተሞክሮዎች አካፍሉት። ይህን ማድረጋችሁ ልጃችሁም ልክ እንደ እናንተ ሕይወቱን ይሖዋን ለማገልገል እንዲጠቀምበት ሊያነሳሳው ይችላል። w19.08 22 አን. 10-11
ሰኞ፣ ሚያዝያ 19
በታላቂቱ አመንዝራ ላይ የተበየነውን ፍርድ አሳይሃለሁ።—ራእይ 17:1
በዓለም ላይ ያሉትን የሐሰት ሃይማኖቶች በሙሉ የምትወክለው ታላቂቱ ባቢሎን በአምላክ ስም ላይ ብዙ ነቀፋ አምጥታለች። ስለ አምላክ በርካታ ውሸቶችን አስተምራለች። ከምድር ገዢዎች ጋር ኅብረት በመፍጠር መንፈሳዊ ምንዝር ፈጽማለች። ሥልጣኗንና ተሰሚነቷን በመጠቀም መንጎቿን በዝብዛለች። እንዲሁም የአምላክን አገልጋዮች ጨምሮ የብዙ ሰዎችን ደም አፍስሳለች። (ራእይ 18:24፤ 19:2) ይሖዋ ‘በደማቁ ቀይ አውሬ ላይ ባሉት አሥር ቀንዶች’ አማካኝነት ‘ታላቂቱን አመንዝራ’ ያጠፋታል። ይህ ምሳሌያዊ አውሬ የተባበሩት መንግሥታትን ያመለክታል። አሥሩ ቀንዶች በአሁኑ ጊዜ ይህን ድርጅት እየደገፉ ያሉትን የፖለቲካ ኃይሎች ያመለክታሉ። አምላክ የወሰነው ጊዜ ሲደርስ እነዚህ የፖለቲካ ኃይሎች በታላቂቱ ባቢሎን ላይ ይነሳሉ። ሀብቷን በመዝረፍና ክፋቷን በማጋለጥ “ይበዘብዟታል፤ ራቁቷንም ያስቀሯታል።” (ራእይ 17:3, 16) በአንድ ቀን ውስጥ የተከናወነ ያህል በአፋጣኝ የሚመጣባት ይህ ጥፋት፣ ደጋፊዎቿን በእጅጉ ያስደነግጣቸዋል፤ ምክንያቱም ይህች አመንዝራ “ሐዘንም ፈጽሞ አይደርስብኝም” እያለች ትኩራራ ነበር።—ራእይ 18:7, 8፤ w19.09 10 አን. 10-11
ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 20
ቀንበሬን ተሸከሙ፤ ከእኔም ተማሩ።—ማቴ. 11:29
ይህ ግብዣ ለሁሉም ክፍት ነው። ኢየሱስ ከልቡ አምላክን ማገልገል የሚፈልግን ማንኛውንም ሰው ከመቀበል ወደኋላ አይልም። (ዮሐ. 6:37, 38) ሁሉም የክርስቶስ ተከታዮች ይሖዋ ለኢየሱስ በሰጠው ሥራ የመካፈል መብት ተሰጥቷቸዋል። ይህን ሥራ ስናከናውን ኢየሱስ ሁሌም ከጎናችን ሆኖ እንደሚረዳን መተማመን እንችላለን። (ማቴ. 28:18-20) ትሑት የሆኑ ሰዎች ወደ ኢየሱስ መቅረብ ይቀላቸው ነበር። (ማቴ. 19:13, 14፤ ሉቃስ 7:37, 38) ለምን? በኢየሱስና በፈሪሳውያን መካከል ያለውን ልዩነት እስቲ እንመልከት። የሃይማኖት መሪዎች የነበሩት ፈሪሳውያን ጨካኝና ኩሩ ነበሩ። (ማቴ. 12:9-14) ኢየሱስ ግን አፍቃሪና ትሑት ነበር። ፈሪሳውያን ከሌሎች ልቀው ለመታየት ይጣጣሩ የነበረ ከመሆኑም ሌላ በማኅበረሰቡ ውስጥ በነበራቸው ከፍተኛ ቦታ ይኩራሩ ነበር። ኢየሱስ ግን ከሌሎች ልቆ ለመታየት የመፈለግ ዝንባሌን ያወገዘ ሲሆን ደቀ መዛሙርቱ ራሳቸውን እንደ ተራ አገልጋይ እንዲቆጥሩ አስተምሯል። (ማቴ. 23:2, 6-11) ፈሪሳውያን ሕዝቡን በማስፈራራትና በማሸማቀቅ እንዲገዛላቸው ያደርጉ ነበር። (ዮሐ. 9:13, 22) ኢየሱስ ግን ፍቅርና ደግነት የሚንጸባረቅባቸው ቃላት በመናገር ለሌሎች የእረፍት ምንጭ ሆኗል። እናንተስ በዚህ ረገድ የኢየሱስን ምሳሌ ለመከተል ጥረት ታደርጋላችሁ? w19.09 20 አን. 1፤ 21 አን. 7-8፤ 23 አን. 9
ረቡዕ፣ ሚያዝያ 21
ወደ አምላክ ቅረቡ፤ እሱም ወደ እናንተ ይቀርባል።—ያዕ. 4:8
ስብሰባዎች ወደ ይሖዋ ይበልጥ እንድንቀርብ ይረዱናል። በአሁኑ ጊዜ በስብሰባዎች ላይ ስለ መገኘት ያለን አመለካከት፣ ወደፊት ስደት ቢመጣ ምን ያህል እንደምንጸና ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። (ዕብ. 10:24, 25) እንዲህ የምንለው ለምንድን ነው? አሁን በትንሽ በትልቁ ስብሰባ የምንቀር ከሆነ ወደፊት ከእምነት ባልንጀሮቻችን ጋር ለመሰብሰብ ስንል ራሳችንን ለአደጋ ማጋለጥ የሚጠይቅ ሁኔታ ቢገጥመን ምን እናደርጋለን? በሌላ በኩል ግን በስብሰባዎች ላይ ለመገኘት ቁርጥ ውሳኔ ካደረግን ተቃዋሚዎች እንዳንሰበሰብ ለማድረግ በሚሞክሩበት ጊዜ አቋማችንን አናላላም። ለስብሰባዎቻችን ፍቅር ማዳበር ያለብን አሁን ነው። ስብሰባዎቻችንን የምንወዳቸው ከሆነ ተቃውሞም ሆነ መንግሥታት የሚጥሉት እገዳ ከሰው ይልቅ አምላክን እንደ ገዢያችን አድርገን እንዳንታዘዝ እንቅፋት አይሆኑብንም። (ሥራ 5:29) የምትወዷቸውን ጥቅሶች በቃላችሁ ለመያዝ ጥረት አድርጉ። (ማቴ. 13:52) በእርግጥ በቃላችሁ ያጠናችሁትን ሁሉ ታስታውሳላችሁ ማለት አይደለም፤ ያም ቢሆን ይሖዋ ኃያል በሆነው ቅዱስ መንፈሱ ተጠቅሞ እነዚህን ጥቅሶች እንድታስታውሱ ይረዳችኋል። (ዮሐ. 14:26) እነዚህ ጥቅሶች ከይሖዋ ጋር ያላችሁን ዝምድና ጠብቃችሁ መቀጠል እንድትችሉና በታማኝነት እንድትጸኑ ይረዷችኋል። w19.07 3 አን. 5፤ 4 አን. 8-9
ሐሙስ፣ ሚያዝያ 22
በመጨረሻዎቹ ቀናት ለመቋቋም የሚያስቸግር በዓይነቱ ልዩ የሆነ ዘመን እንደሚመጣ ይህን እወቅ።—2 ጢሞ. 3:1
የተወለድከው ከ1914 ወዲህ ነው? ከሆነ ሕይወትህን ሙሉ የኖርከው በዚህ ሥርዓት ‘የመጨረሻዎቹ ቀናት’ ውስጥ ነው። ሁላችንም፣ ኢየሱስ ይህን ዘመን አስመልክቶ በትንቢት የተናገራቸው ክንውኖች እየተፈጸሙ እንዳለ እየሰማን ነው። ከእነዚህ ክንውኖች መካከል ጦርነት፣ የምግብ እጥረት፣ የምድር ነውጥ፣ ቸነፈር፣ ክፋት እየበዛ መሄዱ እና በይሖዋ ሕዝቦች ላይ የሚደርስ ስደት ይገኙበታል። (ማቴ. 24:3, 7-9, 12፤ ሉቃስ 21:10-12) በተጨማሪም ሐዋርያው ጳውሎስ ሰዎች ስለሚኖራቸው ባሕርይ የተናገረው ትንቢት ሲፈጸም ተመልክተናል። በመሆኑም እኛ የይሖዋ አገልጋዮች፣ የምንኖረው “በዘመኑ መጨረሻ” እንደሆነ እርግጠኞች ነን። (ሚክ. 4:1) ከ1914 ወዲህ በርካታ ዓመታት ስላለፉ አሁን የምንኖረው “በመጨረሻዎቹ ቀናት” መጨረሻ ላይ መሆን አለበት። የዚህ ሥርዓት ፍጻሜ በጣም ከመቅረቡ አንጻር የሚከተሉትን ወሳኝ ጥያቄዎች መልስ ማወቃችን አስፈላጊ ነው፦ “በመጨረሻዎቹ ቀናት” ማብቂያ ላይ የትኞቹ ክንውኖች ይፈጸማሉ? እነዚህን ክንውኖች እየተጠባበቅን ባለንበት በዛሬው ጊዜ ይሖዋ ምን እንድናደርግ ይጠብቅብናል? w19.10 8 አን. 1-2
ዓርብ፣ ሚያዝያ 23
እስከ መጨረሻው የሚጸና ግን ይድናል።—ማቴ. 24:13 ግርጌ
መጽናታችን የተመካው ባለንበት ሁኔታ ላይ እንዳልሆነ ተምረናል። ከዚህ ይልቅ ጽናትን ይበልጥ ማዳበር የምንችለው በይሖዋ በመታመን ነው። (ሮም 12:12) ኢየሱስ በዛሬው የዕለት ጥቅስ ላይ የሰጠው ተስፋ፣ ምንም ዓይነት ፈታኝ ሁኔታ ቢያጋጥመን በታማኝነት መጽናት እንዳለብን ይጠቁመናል። በዛሬው ጊዜ የሚያጋጥመንን እያንዳንዱን ፈተና በጽናት ከተወጣን ለታላቁ መከራ የሚያስፈልገንን ጥንካሬ ከአሁኑ እናዳብራለን። እንደ ጽናት ሁሉ፣ እውነተኛ ድፍረትም የሚገኘው በይሖዋ በመታመን ነው። በይሖዋ ይበልጥ ለመታመን ምን ማድረግ እንችላለን? ቃሉን በየዕለቱ ማንበባችንና በጥንት ጊዜ ይሖዋ ሕዝቡን እንዴት እንዳዳነ ማሰላሰላችን በዚህ ረገድ ይረዳናል። (መዝ. 68:20፤ 2 ጴጥ. 2:9) በታላቁ መከራ ወቅት መንግሥታት በእኛ ላይ ጥቃት ሲሰነዝሩ ደፋሮች መሆንና ከመቼውም ጊዜ ይበልጥ በይሖዋ መታመን ይኖርብናል። (መዝ. 112:7, 8፤ ዕብ. 13:6) በአሁኑ ወቅት በይሖዋ የምንታመን ከሆነ የጎግን ጥቃት ለመቋቋም የሚያስችል ድፍረት ማዳበር እንችላለን። ይሖዋ ፍቅራዊ ጥበቃ ስለሚያደርግልን ምንጊዜም ደህንነታችን እንደሚጠበቅ እርግጠኞች ነን።—1 ቆሮ. 13:8፤ w19.10 17-18 አን. 15-16
ቅዳሜ፣ ሚያዝያ 24
መላው ዓለም . . . በክፉው ቁጥጥር ሥር ነው።—1 ዮሐ. 5:19
ይህን ሥርዓት የሚቆጣጠረው ዲያብሎስ ነው፤ በመሆኑም ይህን ሥርዓት በመጠቀም፣ ተፈጥሯዊ ለሆኑ ፍላጎቶቻችን ከልክ ያለፈ ቦታ እንድንሰጥ እንዲሁም በድክመቶቻችን እንድንሸነፍ ለማድረግ ይሞክራል። (ኤፌ. 2:1-3) ዓላማው ለሌሎች ነገሮች ያለን ፍቅር፣ ለይሖዋ ብቻ ልናቀርብ የሚገባውን አምልኮ እንዲሻማብን ማድረግ ነው። ሐዋርያው ጴጥሮስ በደብዳቤው ላይ ስለ ሰይጣን ዓለም ጥፋትና ስለ መጪው አዲስ ዓለም ከገለጸ በኋላ “የተወደዳችሁ ወንድሞች፣ እነዚህን ነገሮች እየተጠባበቃችሁ ስለሆነ በመጨረሻ በእሱ ፊት ቆሻሻና እድፍ ሳይኖርባችሁ በሰላም እንድትገኙ የተቻላችሁን ጥረት አድርጉ” ብሏል። (2 ጴጥ. 3:14) ይህን ምክር በመከተል ሥነ ምግባራዊና መንፈሳዊ ንጽሕናችንን ለመጠበቅ የምንችለውን ሁሉ የምናደርግ ከሆነ ይሖዋን ብቻ እንደምናመልክ እናሳያለን። ሰይጣንና የእሱ ሥርዓት፣ ቅድሚያ መስጠት ላለብን ነገሮች ቅድሚያ እንዳንሰጥ እኛን መፈተናቸውን ይቀጥላሉ። (ሉቃስ 4:13) ሆኖም የሚያጋጥመን ተፈታታኝ ሁኔታ ምንም ይሁን ምን፣ ይሖዋ በልባችን ውስጥ ሊኖረው የሚገባውን ቦታ ለማንኛውም አካል ወይም ነገር አንሰጥም። ለይሖዋ ብቻ የሚገባውን ነገር ለእሱ ለመስጠት ይኸውም እሱን ብቻ ለማምለክ ቁርጥ ውሳኔ አድርገናል! w19.10 27 አን. 4፤ 31 አን. 18-19
እሁድ፣ ሚያዝያ 25
ኃጢአቴም አስጨንቆኝ ነበር።—መዝ. 38:18
ስለ አንዳንድ ጉዳዮች መጨነቅ ተገቢ ነው። ለምሳሌ ያህል፣ ይሖዋን እና ኢየሱስን ስለ ማስደሰት ልንጨነቅ ይገባል። (1 ቆሮ. 7:32) ከባድ ኃጢአት ሠርተን ከሆነ ደግሞ ከአምላክ ጋር ያለንን ወዳጅነት የማደሱ ጉዳይ ሊያስጨንቀን ይገባል። ከዚህም ሌላ የትዳር ጓደኛችንን ስለ ማስደሰት ወይም የቤተሰባችንን አባላትና የእምነት ባልንጀሮቻችንን ስለ መንከባከብ መጨነቃችን ተገቢ ነው። (1 ቆሮ. 7:33፤ 2 ቆሮ. 11:28) በሌላ በኩል ግን በቂ ምግብና ልብስ የማግኘታችን ጉዳይ ነጋ ጠባ ያስጨንቀን ይሆናል። (ማቴ. 6:31, 32) እንዲህ ያለው ጭንቀት ደግሞ ቁሳዊ ነገሮችን በማካበት ላይ እንድናተኩር ሊያደርገን ይችላል። ይህ ከሆነ ደግሞ በይሖዋ ላይ ያለን እምነት መዳከሙና መንፈሳዊነታችን መጎዳቱ አይቀርም። (ማር. 4:19፤ 1 ጢሞ. 6:10) ከልክ ባለፈ ጭንቀት ልንዋጥ የምንችልበት ሌላ አቅጣጫ ደግሞ በሌሎች ዘንድ ተቀባይነት ስለ ማግኘት መጨነቅ ነው። እንዲህ ያለው ጭንቀት ይሖዋን ከማሳዘን የበለጠ ከሰዎች የሚሰነዘርብንን ፌዝ ወይም ስደትን እንድንፈራ ሊያደርገን ይችላል። እንዲህ ባለው ወጥመድ ውስጥ እንዳንወድቅ፣ ፈተናውን ለመቋቋም የሚያስችል እምነትና ድፍረት እንዲሰጠን ይሖዋን መለመን ይኖርብናል።—ምሳሌ 29:25፤ ሉቃስ 17:5፤ w19.11 15 አን. 6-7
ሰኞ፣ ሚያዝያ 26
ከእናንተ መካከል ጥበብ የጎደለው ሰው ካለ አምላክን ያለማሰለስ ይለምን፤ አምላክ . . . ለሁሉም በልግስና ይሰጣልና።—ያዕ. 1:5
ትልቅ ቦታ የሚሰጣቸው አንዳንድ ውሳኔዎችን ፈጽሞ መቀየር አንችልም። ለምሳሌ ያህል፣ ይሖዋን ለማገልገል ባደረግነው ውሳኔ እስከ መጨረሻው መጽናት ይኖርብናል፤ ለትዳር ጓደኛችን ታማኝ ለመሆን የገባነውን ቃልም መጠበቅ አለብን። (ማቴ. 16:24፤ 19:6) ሌሎች ውሳኔዎቻችንን ግን ማስተካከል ያስፈልገን ይሆናል። ለምን? ሁኔታዎች ስለሚለዋወጡ ነው። ታዲያ ከሁሉ የተሻለ ውሳኔ ለማድረግ የሚረዱን አንዳንድ እርምጃዎች የትኞቹ ናቸው? ጥበብ ለማግኘት ጸልይ። ሁኔታው ይለያይ እንጂ ሁላችንም ‘ጥበብ የሚጎድለን’ ጊዜ አለ። በመሆኑም ውሳኔ ስታደርግም ሆነ ያደረግከውን ውሳኔ ስትገመግም የይሖዋን እርዳታ ለማግኘት ሞክር። ይሖዋም ጥበብ የተንጸባረቀባቸው ውሳኔዎች እንድታደርግ ይረዳሃል። የተሟላ መረጃ ለማግኘት ጥረት አድርግ። የአምላክ ቃል ስለ ጉዳዩ የሚሰጠውን ምክር ተመልከት፤ የይሖዋ ድርጅት ያዘጋጃቸውን ጽሑፎች አንብብ፤ እንዲሁም እምነት የምትጥልባቸውን ሰዎች አማክር። (ምሳሌ 20:18) በዚህ መንገድ መረጃ ለማግኘት ጥረት ማድረግህ ሥራ ከመቀየር፣ ወደ ሌላ አካባቢ ከመዛወር ወይም ራስህን እያስተዳደርክ ይሖዋን ማገልገል እንድትችል ምን ዓይነት ትምህርት መምረጥ እንዳለብህ ከመወሰን ጋር በተያያዘ ጥሩ ውሳኔ ለማድረግ ይረዳሃል። w19.11 27 አን. 6-8
ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 27
እኔ ምንኛ ጎስቋላ ሰው ነኝ! እንዲህ ወዳለው ሞት ከሚመራኝ ሰውነት ማን ይታደገኛል?—ሮም 7:24
ደስ የሚለው ነገር አምላክ ከኃጢአት ነፃ የምንወጣበት ዝግጅት አድርጎልናል። ይህን ነፃነት እንድናገኝ ቁልፍ ሚና የሚጫወተው ኢየሱስ ነው። በስምንተኛው መቶ ዘመን ዓ.ዓ. ነቢዩ ኢሳይያስ ወደፊት ስለሚኖር ታላቅ ነፃነት አስቀድሞ ተናግሮ ነበር፤ ይህ ታላቅ ነፃነት የእስራኤላውያን የኢዮቤልዩ ዓመት ከሚያስገኘው ነፃነት እጅግ የላቀ ነው። ኢሳይያስ እንዲህ ሲል ጽፏል፦ “የሉዓላዊው ጌታ የይሖዋ መንፈስ በእኔ ላይ ነው፤ ምክንያቱም ይሖዋ የዋህ ለሆኑ ሰዎች ምሥራች እንድናገር ቀብቶኛል። ልባቸው የተሰበረውን እንድጠግን፣ ለተማረኩት ነፃነትን እንዳውጅ . . . ልኮኛል።” (ኢሳ. 61:1) ይህ ትንቢት የሚናገረው ስለ ማን ነው? ስለ ነፃነት የሚናገረው ይህ አስፈላጊ ትንቢት ፍጻሜውን ማግኘት የጀመረው ኢየሱስ አገልግሎቱን ከጀመረ በኋላ ነው። ኢየሱስ ባደገበት በናዝሬት ከተማ ወደሚገኝ አንድ ምኩራብ በገባበት ወቅት በዚያ ለተሰበሰቡት አይሁዳውያን ይህን የኢሳይያስ ትንቢት ካነበበ በኋላ ትንቢቱ በእሱ ላይ ፍጻሜውን እንዳገኘ ገልጿል።—ሉቃስ 4:16-19፤ w19.12 9-10 አን. 6-8
ረቡዕ፣ ሚያዝያ 28
ከባድ ተቃውሞ እያለም የአምላክን ምሥራች ለእናንተ ለመንገር በአምላካችን እርዳታ እንደ ምንም ብለን ድፍረት አገኘን።—1 ተሰ. 2:2
ስደትን በጽናት ለመቋቋም ድፍረት ያስፈልጋችኋል። ይህን ባሕርይ ይበልጥ ማዳበር እንደሚያስፈልጋችሁ ከተሰማችሁ ምን ማድረግ ትችላላችሁ? እውነተኛ ድፍረት፣ ግዙፍ ወይም ጠንካራ በመሆናችን አሊያም በችሎታችን ላይ የተመካ እንዳልሆነ እናስታውስ። ወጣቱ ዳዊት፣ ጎልያድን በተጋፈጠበት ወቅት የነበረውን ሁኔታ እንደ ምሳሌ እንመልከት። ዳዊት ከዚያ ግዙፍ ሰው በአቋምም ሆነ በጥንካሬ የሚያንስ ከመሆኑም ሌላ በቂ የጦር ትጥቅ አልነበረውም። ሌላው ቀርቶ ሰይፍ እንኳ አልያዘም። ያም ቢሆን በጣም ደፋር ነበር። ዳዊት እብሪተኛ ከሆነው ከዚያ ግዙፍ ሰው ጋር ለመዋጋት በድፍረት እየሮጠ ወደ እሱ ሄዷል። ዳዊት ይህን ያህል ደፋር እንዲሆን የረዳው ምንድን ነው? ይሖዋ ከእሱ ጋር እንደሆነ ጠንካራ እምነት ነበረው። (1 ሳሙ. 17:37, 45-47) ዳዊት፣ ጎልያድ ከእሱ አንጻር ሲታይ ምን ያህል ግዙፍ እንደሆነ አላሰበም። ከዚህ ይልቅ ትኩረት ያደረገው ጎልያድ ከይሖዋ አንጻር ሲታይ በጣም ኢምንት በመሆኑ ላይ ነው። ከዚህ ዘገባ ምን ትምህርት እናገኛለን? ይሖዋ ከእኛ ጋር እንደሆነ ከተማመንንና ተቃዋሚዎቻችን ሁሉን ቻይ ከሆነው አምላክ አንጻር ሲታዩ ከቁጥር የማይገቡ እንደሆኑ ካስታወስን የበለጠ ድፍረት ይኖረናል።—2 ዜና 20:15፤ መዝ. 16:8፤ w19.07 5 አን. 11-13
ሐሙስ፣ ሚያዝያ 29
አብረውኝ የሚሠሩት . . . የብርታት ምንጭ ሆነውልኛል።—ቆላ. 4:11
ቲኪቆስ እምነት የሚጣልበት የሐዋርያው ጳውሎስ ክርስቲያን አጋር ነበር። (ሥራ 20:4) በ55 ዓ.ም. ገደማ ጳውሎስ በይሁዳ ላሉት ክርስቲያኖች እርዳታ እንዲዋጣ ዝግጅት አድርጎ ነበር፤ ጳውሎስ ከዚህ አስፈላጊ ሥራ ጋር በተያያዘ እገዛ እንዲያበረክት የመደበው ቲኪቆስን ሳይሆን አይቀርም። (2 ቆሮ. 8:18-20) ከጊዜ በኋላም ጳውሎስ በሮም ለመጀመሪያ ጊዜ በታሰረበት ወቅት ቲኪቆስ መልእክተኛው ሆኖ አገልግሎታል። ቲኪቆስ፣ ጳውሎስ የጻፋቸውን ደብዳቤዎችና ማበረታቻ የያዙ መልእክቶች በእስያ ለሚገኙ ጉባኤዎች አድርሷል። (ቆላ. 4:7-9) ከጊዜ በኋላም ቲኪቆስ እምነት የሚጣልበት የጳውሎስ ወዳጅ ሆኖ ቀጥሏል። (ቲቶ 3:12) በዚያ ወቅት እንደ ቲኪቆስ እምነት የሚጣልባቸው ሁሉም ክርስቲያኖች አልነበሩም። በ65 ዓ.ም. ገደማ ጳውሎስ ለሁለተኛ ጊዜ ታስሮ በነበረበት ወቅት፣ በእስያ ግዛት የሚገኙ በርካታ ወንድሞች ከእሱ ጋር መተባበራቸውን እንዳቆሙ ጽፏል፤ እነዚህ ወንድሞች ይህን ያደረጉት ተቃዋሚዎችን ፈርተው ሊሆን ይችላል። (2 ጢሞ. 1:15) በሌላ በኩል ግን ቲኪቆስ እምነት የሚጣልበት ሰው ስለነበር ጳውሎስ ተጨማሪ ኃላፊነት ሰጥቶታል። (2 ጢሞ. 4:12) ጳውሎስ እንደ ቲኪቆስ ያለ ጥሩ ወዳጅ በማግኘቱ አመስጋኝ እንደነበረ ጥያቄ የለውም። w20.01 10 አን. 7-8
ዓርብ፣ ሚያዝያ 30
አምላክ እነዚህን ነገሮች በመንፈሱ አማካኝነት የገለጠው ለእኛ [ነው]።—1 ቆሮ. 2:10
ምናልባት አንተም ‘በመንፈስ ቅዱስ ተቀብቼ ይሆን?’ የሚል ጥያቄ ተፈጥሮብህ ይሆናል። ከሆነ ልታስብባቸው የሚገቡ አንዳንድ ጥያቄዎች ከዚህ ቀጥሎ ቀርበዋል፦ ‘የይሖዋን ፈቃድ የማድረግ ከፍተኛ ፍላጎት አለህ? በስብከቱ ሥራ የተለየ ቅንዓት እንዳለህ ይሰማሃል? “የአምላክን ጥልቅ ነገሮች” መቆፈር የሚያስደስትህ ትጉ የአምላክ ቃል ተማሪ ነህ? ይሖዋ በስብከቱ ሥራ ግሩም ውጤት እንድታገኝ እንደረዳህ ይሰማሃል? ሌሎችን በመንፈሳዊ የመርዳት ኃላፊነት እንዳለብህ ከልብህ ይሰማሃል? ይሖዋ በሕይወትህ ውስጥ በተለያዩ መንገዶች እንደረዳህ የሚያረጋግጥ ማስረጃ ተመልክተሃል?’ ታዲያ ለእነዚህ ጥያቄዎች በልበ ሙሉነት “አዎ” የሚል መልስ የምትሰጥ ከሆነ ሰማያዊ ጥሪ አለህ ማለት ነው? አይደለም። ለምን? ምክንያቱም ሁሉም የአምላክ አገልጋዮች እንዲህ ያለ ስሜት ሊሰማቸው ይችላል። እንዲያውም በመንፈስ ቅዱስ ስለ መቀባትህ ጥያቄ የሚፈጠርብህ ከሆነ ይህ በራሱ እንዲህ ዓይነት ጥሪ እንዳላገኘህ ያሳያል። ይሖዋ የጠራቸው ሰዎች ስለ መቀባታቸው ጥርጣሬ አይገባቸውም! ጥሪውን ማግኘታቸውን በእርግጠኝነት ያውቃሉ! w20.01 23 አን. 14