የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w26 ሚያዝያ ገጽ 32
  • የመጽሐፍ ቅዱስን ዘይቤያዊ አገላለጾች መረዳት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የመጽሐፍ ቅዱስን ዘይቤያዊ አገላለጾች መረዳት
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2026
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2026
w26 ሚያዝያ ገጽ 32

ለጥናት የሚረዱ ሐሳቦች

የመጽሐፍ ቅዱስን ዘይቤያዊ አገላለጾች መረዳት

መጽሐፍ ቅዱስ በመቶዎች የሚቆጠሩ ዘይቤያዊ አገላለጾችን ይዟል። ብዙ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን ሲያነቡ እነዚህን ዘይቤያዊ አገላለጾች ለመረዳት ይቸገራሉ። (ማቴ. 13:13) ታዲያ ትርጉማቸውን ለመረዳት ምን ያግዘናል?

  • ርዕሰ ጉዳዩን እና ምሳሌውን ለይ። ዘይቤያዊ አገላለጾች አንድን ርዕሰ ጉዳይ ከአንድ ምሳሌ ጋር ያወዳድራሉ። ለምሳሌ ያህል፣ ራእይ 3:3 የኢየሱስን መምጣት (ርዕሰ ጉዳይ) ከሌባ አመጣጥ (ምሳሌ) ጋር ያመሳስለዋል።

  • ርዕሰ ጉዳዩ ከምሳሌው ጋር የሚመሳሰለው እንዴት እንደሆነ አስተውል። ሁለቱ ነገሮች ለምን እንደተወዳደሩና የሚመሳሰሉት በየትኞቹ አቅጣጫዎች እንደሆነ ለማሰብ ሞክር።

  • ትክክለኛው መደምደሚያ ላይ መድረስህን አረጋግጥ። አንዳንዴ ርዕሰ ጉዳዩን ከምሳሌው ጋር ባልተፈለገ መንገድ ካመሳሰልነው የተሳሳተ መደምደሚያ ላይ ልንደርስ እንችላለን። ለአብነት ያህል፣ ከላይ በተጠቀሰው ምሳሌ ላይ የኢየሱስ መምጣት ከሌባ ጋር የተወዳደረው አመጣጡ ያልተጠበቀና ድንገተኛ እንደሚሆን ለማጉላት እንጂ ኢየሱስ የሆነ ነገር እንደሚሰርቅ ለመጠቆም አይደለም።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2026)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2026 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ