መዝሙር 163
ዓይኖቻችሁ ደስተኞች ናቸው
በወረቀት የሚታተመው
1.ጨለማው ዘመን ተሸኘ፤
የደስታ መንገድ ተገኘ፤
ከኢየሱስ ዘንድ ከተራራው ናኘ።
ልበ ትሑት ነው ይቅር ባይ፤
ለሰው ሁሉ ደግ ሳይለያይ፤
ወርዶ አሳየን አባቱን ከሰማይ።
(አዝማች)
ባምላኬ በራ ’ይኔ፤
ሐሴት ነው ዘመኔ።
ባምላኬ አዩ ዓይኖቼ፤
በደስታ መንገድ ተገኝቼ።
2. ቢሰጋም ልቤ ተጨንቆ፣
ይረጋል ተስፋን ሰንቆ፤
የዛሬን እንጂ የነገን ማን አውቆ?
የሰማይዋን ወፍ መግቦ፣
የሜዳ ’በባን ሞሽሮ፣
እንዴት አይረዳኝ እንባዎቼን ቆጥሮ?
(አዝማች)
ባምላኬ በራ ’ይኔ፤
ሐሴት ነው ዘመኔ።
ባምላኬ አዩ ዓይኖቼ፤
በደስታ መንገድ ተገኝቼ።
3. ባሸዋ ሳይሆን ባ’ለቱ፣
ታንጿል ሥሩ በብርቱ፤
በወጀብ፣ ጎርፉ አይወሰድ ቤቱ።
ቀጭን ቢሆንም መንገዱ፣
መግቢያ በራችን ጠባቡ፤
ያበቃል ለድል፣ ያደርሳል ከግቡ።
(አዝማች)
ባምላኬ በራ ’ይኔ፤
ሐሴት ነው ዘመኔ።
ባምላኬ አዩ ዓይኖቼ፤
በደስታ መንገድ ተገኝቼ።
(በተጨማሪም ማቴ. 7:24ን ተመልከት።)