ማስታወቂያዎች
◼ ታኅሣሥ፦ ትራክቶች ወይም ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? ጥር እና የካቲት፦ ከአምላክ የተላከ ምሥራች! ወይም አምላክን ስማ ወይም አምላክን ስማ የዘላለም ሕይወት ታገኛለህ። (አምላክን ስማ የሚለውን ብሮሹር፣ ማንበብ የማይችል ወይም የማንበብ ችሎታው ውስን የሆነ ሰውን ለማወያየት መጠቀም እንችላለን። ይህም ልጆችን ያጠቃልላል።) መጋቢት፦ መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች።
◼ በ2016 የመታሰቢያው በዓል የሚከበረው ረቡዕ፣ መጋቢት 23 ቀን 2016 ይሆናል።
◼ ከጥር 1 ቀን 2015 አንስቶ ጉባኤዎች በወሩ የመጀመሪያ ቅዳሜ ላይ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እንዲያስጀምሩ ተደርጎ የነበረው ዝግጅት ይቋረጣል። ከዚህ ይልቅ አስፋፊዎች በሌሎች ቅዳሜዎች እንደሚያደርጉት መጽሔቶች ማበርከት ይችላሉ። በወሩ ውስጥ በማንኛውም ጊዜ መጽሔቶችንም ሆነ ሌሎች ማስጠኛ ጽሑፎችን ተጠቅመን ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን እንዲያጠኑ መጋበዝ እንችላለን።
◼ ለበርካታ ዓመታት ነጠላ ወንድሞችን በአገልጋዮች ማሠልጠኛ ትምህርት ቤት እንዲሠለጥሉ ወደ ኬንያ ስንልክ ቆይተን ነበር። ይህም በኢትዮጵያ የመንግሥቱን ሥራ ለማስፋፋት ትልቅ ሚና ተጫውቷል። ይሁንና ብቃቱን የሚያሟሉ በርካታ ወንድሞች ቋንቋ ስለሚገድባቸው ለሥልጠና ወደ ኬንያ መሄድ አልቻሉም። አሁን ግን የመንግሥቱ ወንጌላውያን ትምህርት ቤት (መወትቤ) በአዲስ አበባ እንዲቋቋም የበላይ አካሉ ፈቃድ መስጠቱን ስናሳውቃችሁ ደስ ይለናል። ትምህርቱ የሚሰጠው በአማርኛ ነው። ትምህርት ቤቱ የሚገነባው በቅርንጫፍ ቢሮው ቅጥር ግቢ ውስጥ ሲሆን በያዝነው የአገልግሎት ዓመት መጨረሻ ላይ ሥራ እንደሚጀምር ተስፋ እናደርጋለን።