መስከረም 3 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
መስከረም 3 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 6 እና ጸሎት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
fy ምዕ. 14 ከአን. 10-16 (30 ደቂቃ)
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ሕዝቅኤል 39-41 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ ሕዝቅኤል 40:17-31 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ ዓይናችን ሊያስተን የሚችለው በየትኞቹ መንገዶች ነው?—ዘፍ. 3:2-6 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ ክርስቲያኖች ገለልተኞች ናቸው ሲባል ለሰዎች ደኅንነት ደንታ ቢሶች ናቸው ማለት ነው?—rs ገጽ 275 አን. 2 (5 ደቂቃ)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
10 ደቂቃ፦ ለምናነጋግረው ሰው ነጥቡን ማስረዳት የምንችልበት መንገድ—ክፍል 2። በአገልግሎት ትምህርት ቤት መጽሐፍ ከገጽ 253 አንቀጽ 3 እስከ ገጽ 254 መጨረሻ ድረስ ባለው ሐሳብ ላይ ተመሥርቶ በውይይት የሚቀርብ። የቀረቡትን ነጥቦች በመጠቀም አንድ ወይም ሁለት አጠር ያሉ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ።
10 ደቂቃ፦ ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።
10 ደቂቃ፦ በመስከረም ወር መጽሔቶችን ለማበርከት የሚረዱ ሐሳቦች። በውይይት የሚቀርብ። መጽሔቶቹ በክልላችሁ ውስጥ ያሉ ሰዎችን ትኩረት ሊስቡ የሚችሉበትን ምክንያት ከ30 እስከ 60 ሴኮንድ ባለው ጊዜ ውስጥ ተናገር። ከዚያም በመጠበቂያ ግንብ መጽሔት የሽፋን ርዕስ ዙሪያ የሰዎችን የማወቅ ፍላጎት ለመቀስቀስ ምን ጥያቄ ማንሳት እንዲሁም የትኞቹን ጥቅሶች ማንበብ እንዳሰቡ አድማጮችን ጠይቅ። በንቁ! መጽሔት የሽፋን ርዕስ ዙሪያም ተመሳሳይ ጥያቄዎችን አቅርብ፤ ጊዜ ካለህ ከመጠበቂያ ግንብ ወይም ከንቁ! መጽሔት አንድ ተጨማሪ ርዕስ ማከል ትችላለህ። እያንዳንዱን መጽሔት እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
መዝሙር 34 እና ጸሎት