ጥቅምት 11 የሚጀምር ሳምንት
ጥቅምት 11 የሚጀምር ሳምንት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 1 ዜና መዋዕል 5-7
ቁ. 1፦ 1 ዜና መዋዕል 6:31-47
ቁ. 2፦ የይሖዋ ምሥክሮች ኑፋቄ ወይም አዲስ የመጣ አክራሪ ሃይማኖት ናቸው? ሃይማኖታቸው ከተቋቋመስ ምን ያህል ጊዜ ሆኖታል? (rs ገጽ 202 አን. 5 እስከ ገጽ 204 አን. 1)
ቁ. 3፦ ፍጽምና የሚጎድላቸው ሰዎች ቅዱስ ሊሆኑ የሚችሉት እንዴት ነው? (1 ጴጥ. 1:16)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
5 ደቂቃ፦ ማስታወቂያዎች።
10 ደቂቃ፦ መልስ መስጠት ያለብህ እንዴት ነው? በአገልግሎት ትምህርት ቤት መጽሐፍ ገጽ 69 ከአንቀጽ 1 እስከ 5 ላይ ተመሥርቶ ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። አንድ አቅኚ፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቱ የግል ውሳኔን የሚጠይቅ ጉዳይ አንስቶ ላቀረበለት ጥያቄ መልስ ሲሰጥ የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪው “አንተ በእኔ ቦታ ብትሆን ኖሮ ምን ታደርግ ነበር?” ብሎ ይጠይቀዋል።
10 ደቂቃ፦ አካላዊ ንጽሕና አምላክን ያስከብራል። የተደራጀ ሕዝብ በተባለው መጽሐፍ ገጽ 137 አንቀጽ 1 እስከ ገጽ 138 አንቀጽ 2 ባለው ሐሳብ ላይ ተመሥርቶ የሚቀርብ ንግግር። የይሖዋ ምሥክሮች ንጹሖች አልፎ ተርፎም በአለባበስና በአጋጌጥ ልከኞች መሆናቸው፣ እውነትን እንዲቀበሉ የረዳቸው እንዴት እንደሆነ እንዲናገሩ አድማጮችን ጋብዝ።
10 ደቂቃ፦ “አትፍሩ።” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ።