የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 11/03 ገጽ 2
  • የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2003
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ኅዳር 10 የሚጀምር ሳምንት
  • ኅዳር 17 የሚጀምር ሳምንት
  • ኅዳር 24 የሚጀምር ሳምንት
  • ታኅሣሥ 1 የሚጀምር ሳምንት
የመንግሥት አገልግሎታችን—2003
km 11/03 ገጽ 2

የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም

ኅዳር 10 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 94 (212)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። በገጽ 4 ላይ ያሉትን ሐሳቦች በመጠቀም የመስከረም 1 መጠበቂያ ግንብ እና የመስከረም 2003 ንቁ! መጽሔቶችን በጉባኤው የአገልግሎት ክልል ውስጥ እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳዩ ሁለት ሕያው ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ። በሁለቱም ሠርቶ ማሳያዎች ላይ አስፋፊው አንደኛውን መጽሔት ብቻ ያስተዋውቅና ሌላኛውን መጽሔት አያይዞ ያበረክታል። በአንደኛው ሠርቶ ማሳያ ላይ ለዓለም አቀፉ የስብከት ሥራ ማካሄጃ ገንዘብ እንዴት እንደሚገኝ ተናገር።—መጠበቂያ ግንብ ገጽ 2 ላይ ወይም ንቁ! ገጽ 5 ላይ ተመልከት።

15 ደቂቃ:- “ተዘጋጅታችሁ ኑሩ።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። በዚህ ሥርዓት ውስጥ የሚያጋጥሟቸው የኑሮ ጭንቀቶችና ጊዜ የሚያባክኑ ነገሮች መንፈሳዊ ጉዳዮችን ለማከናወን የሚያስችላቸውን ጊዜ እንዳይሻሙባቸው ለማድረግ ምን እንደረዳቸው እንዲናገሩ አድማጮችን ጋብዝ።

20 ደቂቃ:- ጓደኞቻችሁን የምትመርጡት እንዴት ነው? የአምልኮ አንድነት በተባለው መጽሐፍ ገጽ 44-5 ላይ ተመሥርቶ ከአድማጮች ጋር በውይይት የሚቀርብ። አድማጮች በአንቀጽ 13 ላይ የሚገኙትን ጥያቄዎችና ጥቅሶች ተጠቅመው በጓደኛ ምርጫ ረገድ መመሪያ የሚሆኑንን የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶች እንዲናገሩ ጋብዝ።

መዝሙር 51 (127) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ኅዳር 17 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 14 (34)

12 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። በወሩ ውስጥ የሚበረከተውን ጽሑፍ ተጠቅመው ጥሩ ተሞክሮ ላገኙ ወይም የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ላስጀመሩ ሁለት ወይም ሦስት አስፋፊዎች ቃለ ምልልስ አድርግ።

15 ደቂቃ:- የልግስና መንፈስ አዳብሩ። በኅዳር 1, 2003 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 27-30 ላይ ተመሥርቶ በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር።

18 ደቂቃ:- “ምስጋና መንፈስ ያድሳል።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። የቤተሰብ ደስታ ከተባለው መጽሐፍ ገጽ 49-50 አንቀጽ 21 ላይ አንዳንድ ሐሳቦችን ጨምረህ ተናገር። ከሌሎች ያገኙት ምስጋና የብርታት ምንጭ የሆነላቸው ግለሰቦች አጠር ያሉ ሐሳቦችን እንዲናገሩ ጋብዝ።

መዝሙር 28 (58) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ኅዳር 24 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 95 (213)

12 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት። በገጽ 4 ላይ ያሉትን ሐሳቦች በመጠቀም የመስከረም 15 መጠበቂያ ግንብ እና የመስከረም 22, 2003 ንቁ! (እንግሊዝኛ) መጽሔቶችን እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳዩ ሁለት ሕያው ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ። በገጽ 4 ላይ ከተጠቆመው የተለየ ጥቅስ መጠቀም ይቻላል። በሁለቱም ሠርቶ ማሳያዎች ላይ አስፋፊው አንደኛውን መጽሔት ብቻ ያስተዋውቅና ሌላኛውን መጽሔት አያይዞ ያበረክታል። አንደኛው ሠርቶ ማሳያ በሕዝብ ማጓጓዣ ወይም ለጉባኤው ክልል ተስማሚ በሆነ ሌላ መቼት መደበኛ ባልሆነ መንገድ መጽሔት ሲበረከት የሚያሳይ ይሁን።

10 ደቂቃ:- የጥያቄ ሣጥን። በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር።

23 ደቂቃ:- “ከይሖዋ ጋር የጠበቀ ወዳጅነት ማዳበር።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። ለአንቀጾቹ የቀረቡትን ጥያቄዎች ተጠቀም። አድማጮች ጥቅሶቹ ከሐሳቡ ጋር እንዴት እንደሚያያዙ ሐሳብ እንዲሰጡ አድርግ። አንድ ወይም ሁለት አስፋፊዎች የግል የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናታቸውን ጥራት እንዲያሻሽሉ ምን እንደረዳቸው እንዲናገሩ አስቀድመህ ዝግጅት አድርግ።

መዝሙር 91 (207) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ታኅሣሥ 1 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 58 (138)

5 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች።

40 ደቂቃ:- “የአውራጃ ስብሰባው ለአምላክ ክብር እንድንሰጥ አነሳስቶናል!” በሽማግሌ የሚቀርብ። አንድ ደቂቃ ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ የአውራጃ ስብሰባውን ፕሮግራም ለመከለስ በቀረቡት ጥያቄዎች ተጠቅመህ በውይይት አቅርበው። ሁሉንም ጥያቄዎች መሸፈን እንድትችል ለአንዳንድ ጥያቄዎች አንድ መልስ ብቻ በመፍቀድ ጊዜውን አመጣጥን። በተመደበው ጊዜ ውስጥ ምዕራፍና ቁጥራቸው ብቻ የተሰጡትን ጥቅሶች በሙሉ ማንበብ ያስቸግራል። ጥቅሶቹ የገቡት መልሶቹን በቀላሉ ለማግኘት እንዲቻል ነው። የሚሰጡት መልሶች የተማርናቸውን ነገሮች ተግባራዊ ማድረግ በሚያስገኛቸው ጥቅሞች ላይ ያተኮሩ መሆን ይኖርባቸዋል።

መዝሙር 32 (70) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2026)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2026 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ