የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 3/03 ገጽ 2
  • የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2003
  • ንዑስ ርዕሶች
  • መጋቢት 10 የሚጀምር ሳምንት
  • መጋቢት 17 የሚጀምር ሳምንት
  • መጋቢት 24 የሚጀምር ሳምንት
  • መጋቢት 31 የሚጀምር ሳምንት
  • ሚያዝያ 7 የሚጀምር ሳምንት
የመንግሥት አገልግሎታችን—2003
km 3/03 ገጽ 2

የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም

መጋቢት 10 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 35 (79)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። በገጽ 8 ላይ ያሉትን ሐሳቦች በመጠቀም የየካቲት 1 መጠበቂያ ግንብ እና የየካቲት 2003 ንቁ! ሲበረከት የሚያሳዩ ሁለት ሠርቶ ማሳያዎች አቅርብ። በሁለቱም ሠርቶ ማሳያዎች ላይ አስፋፊው አንደኛውን መጽሔት ብቻ ያስተዋውቅና ሌላኛውንም መጽሔት አያይዞ ያበረክታል።

15 ደቂቃ:- ከይሖዋ ምሥክሮች የዓመት መጽሐፍ ጥቅም ማግኘት። በንግግርና ከአድማጮች ጋር በውይይት የሚቀርብ። በ2003 የዓመት መጽሐፍ በገጽ 3-5 ላይ “ከአስተዳደር አካል የተላከ ደብዳቤ” ከሚለው ርዕስ ውስጥ ጎላ ያሉ ሐሳቦችን አቅርብ። (ይህ ደብዳቤ በዚህ የመንግሥት አገልግሎታችን እትም ገጽ 6 ላይ ይገኛል።) ባለፈው ዓመት ከወጣው የዓመት መጽሐፍ ውስጥ የሚያበረታቱና እምነት የሚያጠነክሩ ሆነው ያገኟቸውን ሪፖርቶችና ተሞክሮዎች የሚናገሩ ጥቂት አስፋፊዎች አስቀድመህ አዘጋጅ። ከዓለም አቀፉ ሪፖርት ላይ ጎላ ብለው የሚታዩትን ክንውኖች ተናገር። (የጥር 1, 2003 መጠበቂያ ግንብ ተመልከት።) ቤተሰቦች ቀስ በቀስ ሙሉውን መጽሐፍ በዓመቱ ውስጥ አንብበው እንዲጨርሱ አበረታታቸው። አዲሶች ወደ ይሖዋ ድርጅት እንዲመጡ ለማድረግና በስብሰባዎች ላይ እንዲገኙ ለማበረታታት መጽሐፉን መጠቀም የምንችልባቸውን አንዳንድ መንገዶች ተናገር።

20 ደቂቃ:- “መልካም ለማድረግ የምትቀኑ ሁኑ!” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። (አንቀጽ 1-10) በአንቀጽ 6 ላይ ከተወያያችሁ በኋላ አንድ አስፋፊ የመጋበዣ ወረቀት በመጠቀም ዘመዱን፣ ጎረቤቱን፣ የትምህርት ቤት ጓደኛውን ወይም የሥራ ባልደረባውን ወደ መታሰቢያው በዓል ሲጋብዘው የሚያሳይ አጭር ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። የመጋበዣ ወረቀቱ እስካሁን ለአስፋፊዎች ካልታደለ ከስብሰባው በኋላ መከፋፈል አለበት።

መዝሙር 7 (19) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

መጋቢት 17 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 14 (34)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት።

15 ደቂቃ:- በጓደኛ ምርጫችሁ ረገድ ጥበበኛ ሁኑ። በየካቲት 22, 1997 (እንግሊዝኛ) ንቁ! ገጽ 13 ላይ እና በማመራመር መጽሐፍ ገጽ 189 ላይ “መጥፎ ጓደኝነት” በሚለው ርዕስ ሥር ባለው ሐሳብ ላይ ተመሥርቶ በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር። መሠረታዊ ሥርዓቱ ለወጣቶችም ሆነ ለአዋቂዎች የሚሠራው እንዴት እንደሆነ አሳይ። ይሖዋን ከሚወዱና የሥነ ምግባር ደረጃዎቹን ለመጠበቅ ከሚጥሩ ሰዎች ጋር ወዳጅነት መመሥረቱ ያለውን ጥቅም ጎላ አድርገህ አሳይ።

20 ደቂቃ:- “መልካም ለማድረግ የምትቀኑ ሁኑ!” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። (አንቀጽ 11-​24) በሰብሳቢ የበላይ ተመልካቹ የሚቀርብ። አንቀጽ 12ን ስትወያዩ አንድ የጉባኤ ሽማግሌ አንድን አቅመ ደካማ የሆኑ ወንድም ቤታቸው ሄዶ በመጠየቅ በመታሰቢያው በዓል ሰሞን በሚደረገው ሰፊ የአገልግሎት እንቅስቃሴ እንዴት ተሳትፎ ማድረግ እንደሚችሉ በደግነት ሲገልጽላቸው የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ አቅርብ።

መዝሙር 25 (53) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

መጋቢት 24 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 33 (72)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። በገጽ 8 ላይ ያሉትን ሐሳቦች በመጠቀም የየካቲት 15 መጠበቂያ ግንብ እና የየካቲት 22 ንቁ! (እንግሊዝኛ) መጽሔቶች ሲበረከቱ የሚያሳዩ ሁለት ሠርቶ ማሳያዎች አቅርብ።

15 ደቂቃ:- ከጥቅምት 1993 ንቁ! መጽሔት ላይ “በሚልዮን የሚቆጠሩ ሰዎች እየተሠቃዩ ነው​—⁠እርዳታ ማግኘት ይችሉ ይሆን?” የሚለውን ርዕስ ተወያዩበት።

20 ደቂቃ:- የይሖዋ ምሥክሮች​—⁠ለኅብረተሰቡ ጠቃሚ አስተዋጽኦ ያበረክታሉ። በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። አንዳንድ ጊዜ አገልግሎታችንና መልካም አርአያችን ኅብረተሰቡን እንዴት እንደሚጠቅም የምንገልጽበት አጋጣሚ እናገኛለን። አድማጮች በሚከተሉት ነጥቦች ላይ ሐሳብ እንዲሰጡ ጋብዝ:- (1) ሰዎች ከመጽሐፍ ቅዱስ የሥነ ምግባር ደረጃዎች ጋር ተስማምተው እንዲኖሩ እናስተምራለን። (2) ሐቀኝነትንና ለሥልጣን አክብሮት ማሳየትን እናስተምራለን። (3) የተለያየ ዘር፣ ብሔርና ማሕበራዊ ደረጃ ያላቸው ሰዎች አንድ ላይ ተስማምተው እንዲኖሩ እናስተምራለን። (4) ሰዎች የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶችን በሥራ ላይ በማዋል የቤተሰባቸውን ሕይወት እንዲያሻሽሉ እንረዳቸዋለን። (5) በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ማንበብና መጻፍ አስተምረናል። (6) አደጋዎች በሚያጋጥሙበት ጊዜ ሌሎችን ለመርዳት ጥረት እናደርጋለን። (7) ሁሉም ሰው ተጠቃሚ የሆነበትን ሃይማኖታዊ ነፃነት በማስከበር ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ አበርክተናል።​—⁠አዋጅ ነጋሪዎች የተባለውን መጽሐፍ ገጽ 699 ተመልከት።

መዝሙር 91 (207) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

መጋቢት 31 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 53 (130)

12 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ሁሉም የመጋቢት የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲመልሱ አስታውሳቸው። በሚያዝያ ወር የሚበረከተውን ጽሑፍና በልዩ የአገልግሎት ክልል ዘመቻው የሚሸፈኑ ምን ያህል ክልሎች እንደቀሩ ተናገር። “መጽሐፍ ቅዱስ ለማስጠናት የአምልኮ አንድነት በተባለው መጽሐፍ ተጠቀሙ” የሚለውን ርዕስ ከልስ። “የመታሰቢያውን በዓል የሚመለከቱ ማሳሰቢያዎች” ከሚለው ርዕስ ዋና ዋና ሐሳቦችን ተናገር።

13 ደቂቃ:- ከጉባኤው የተገኙ ተሞክሮዎች። በመጋቢት ወር በተደረገው የላቀ የአገልግሎት እንቅስቃሴ የተገኙትን ተሞክሮዎች እንዲናገሩ ጋብዝ። ለጥረታቸው አመስግናቸው እንዲሁም ሁኔታቸው በፈቀደላቸው መጠን ሁሉም በሚያዝያ ወር የተሟላ ተሳትፎ እንዲያደርጉ አበረታታቸው።

20 ደቂቃ:- “ይሖዋ ሊወደስ የሚገባው አምላክ ነው።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። የመታሰቢያው በዓል ትልቅ ቦታ የሚሰጠው መሆኑን ጎላ አድርገህ ግለጽ። ሌሎች ሰዎች በበዓሉ ላይ እንዲገኙ በመርዳት ረገድ ሁሉም አስተዋጽኦ ማድረግ የሚችሉበትን መንገድ ተናገር። አገልግሎት ያቆሙ አስፋፊዎችን በማነጋገር ቅንዓታቸውን ለማነሳሳት ምን ማድረግ እንደሚቻል ግለጽ። አድማጮች ባለፈው ዓመት በተከበረው የመታሰቢያው በዓል ወቅት ያገኟቸውን የሚያበረታቱ ተሞክሮዎች እንዲናገሩ ጋብዝ።

መዝሙር 88 (200) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ሚያዝያ 7 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 85 (191)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች።

15 ደቂቃ:- ከቅዱሳን ጽሑፎች እየጠቀሱ አሳማኝ ምክንያት ማቅረብ። ከአድማጮች ጋር በውይይት የሚቀርብ። በአገልግሎት ለምናገኛቸው ሰዎች አሳማኝ ምክንያት የማቅረብ ችሎ​ታችንን ማዳበር የምንችለው እንዴት ነው? (1) ቋሚ የግል ጥናት በማድረግና በስብሰባዎች ላይ አዘውትረህ በመገኘት ጥሩ የቅዱሳን ጽሑፎች እውቀት አግኝ። (2) የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶችን ከተለያዩ አቅጣጫዎች በመመርመር በተማርከው ላይ አሰላስል። (3) ለጥቅሶቹ የሚሰጡትን ማብራሪያዎች ብቻ ሳይሆን ማብራሪያዎቹ የተመሠረቱባቸውን ቅዱስ ጽሑፋዊ ማስረጃዎችም መርምር። (4) ጥቅሶችን ለተለያዩ ዓይነት ሰዎች እንዴት አድርገህ እንደምታብራራ አስብ። (5) አንዳንድ ነጥቦችን እንዴት በምሳሌ ማስረዳት እንደምትችል አስብ።

20 ደቂቃ:- “እውነት ነፃ የሚያወጣን እንዴት ነው?” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። በጥቅምት 1, 1998 መጠበቂያ ግንብ በገጽ 6 ላይ ካለው ሣጥን አንዳንድ ሐሳቦችን ተናገር። የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት በምን መንገድ ነፃነት እንዳስገኘላቸው አድማጮች እንዲናገሩ ጋብዝ።

መዝሙር 97 (217) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2026)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2026 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ