የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 5/94 ገጽ 2
  • የግንቦት የአገልግሎት ስብሰባዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የግንቦት የአገልግሎት ስብሰባዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1994
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ግንቦት 2 የሚጀምር ሳምንት
  • ግንቦት 9 የሚጀምር ሳምንት
  • ግንቦት 16 የሚጀምር ሳምንት
  • ግንቦት 23 የሚጀምር ሳምንት
  • ግንቦት 30 የሚጀምር ሳምንት
የመንግሥት አገልግሎታችን—1994
km 5/94 ገጽ 2

የግንቦት የአገልግሎት ስብሰባዎች

ግንቦት 2 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 155

5 ደቂቃ፦ የጉባኤው ማስታወቂያዎችና ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። የመስክ አገልግሎትን ለማስፋት ከመንገድ ወደ መንገድ ወይም ከሰዓት በኋላ ባሉት ጊዜያት ምሥክርነት ለመስጠት የተደረጉ ዝግጅቶች ካሉ ይህን በተመለከተ ደግመህ አሳስብ።

15 ደቂቃ፦ “መደበኛ ባልሆነ መንገድ ምሥክርነት በመስጠቱ ሥራ ትካፈላለህን?” በርዕሱ ውስጥ ያሉትን ነጥቦች አብራራ። ትዕይንትም አቅርብ። ሁልጊዜ የይሖዋ ምሥክሮች የመሆናችንን ሐቅ ጠበቅ አድርገህ ግለጽ። ስለዚህ ምሥክርነት መስጠት የምንችልባቸውን አጋጣሚዎች እንፈልጋለን። መደበኛ ያልሆነ ምሥክርነት በመስጠት ጥሩ ውጤት ያገኙ አስፋፊዎች አስቀድሞ ዝግጅት ያደረጉባቸውን አጠር ያሉ ሁለት ተሞክሮዎች እንዲናገሩ ወይም የአጋጣሚ ምሥክርነት ተሰጥቶት ወደ እውነት የመጣ ሰው ካለ ተሞክሮውን እንዲናገር አድርግ።

10 ደቂቃ፦ “አቀራረቤን በየጊዜው መለወጥ አለብኝን?” በሁለት ሽማግሌዎች መካከል በውይይት የሚቀርብ። አዘውትሮ በመስክ አገልግሎት መካፈል የሚያስገኛቸውን ጥቅሞች አጉላ።

15 ደቂቃ፦ “እውነትን ለሌሎች ለማካፈል በመጽሔቶች ተጠቀም።” ከአድማጮች ጋር ተወያይበት። መጽሔቶቻችን የተለዩ የሆኑበትን ምክንያትና ይህም በእያንዳንዱ አጋጣሚ መጽሔቶቹን ለማበርከት ሊገፋፋን የሚገባው ለምን እንደሆነ አብራራ። አጠር ያሉ ሁለት ትዕይንቶችን አቅርብ።

መዝሙር 172 እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ግንቦት 9 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 34

10 ደቂቃ፦ የጉባኤው ማስታወቂያዎች። የመጽሔት ኮንትራት የሚገቡ ሰዎችን ለማግኘት አጋጣሚዎችን ነቅተን መከታተል ይኖርብናል። ባለፉት ጊዜያት አዘውትረው መጽሔቶቹን የወሰዱ ሰዎችን ኮንትራት እንዲገቡ ጥያቄ ልናቀርብላቸው እንችላለን። የኮንትራት ማስገቢያ ቅጹን በሦስት ቅጂዎች መሙላት እንዴት እንደሚቻል አስረዳ።

20 ደቂቃ፦ “የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎችን ለአገልግሎት አዘጋጃቸው” በጥያቄና መልስ የሚሸፈን። አንቀጽ 4 እና 5⁠ን በምታብራራበት ጊዜ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪው ከቤት ወደ ቤት ለመመሥከር ሲዘጋጅ እንዴት መርዳት እንደሚቻል የሚያሳይ አጠር ያለ ትዕይንት አቅርብ። ተማሪው መዝሙር 37:11⁠ን በመጠቀም ቀለል ባለ መግቢያ ይጀምራል። የመጽሐፍ ቅዱስ አስተማሪው “የራሴ ሃይማኖት አለኝ” በማለት ያቋርጠዋል። ተማሪው ምን ብሎ መልስ እንደሚሰጥ እርግጠኛ አይደለም። ሁለቱም ምክንያቱን ማስረዳት በተባለው መጽሐፍ ላይ ገጽ 18, 19⁠ን በማውጣት የቀረቡትን አንዳንድ ሐሳቦች አብረው ይመለከታሉ። ተማሪው ይስማማኛል ያለውን አንድ መልስ ይመርጣል። ተማሪው ንግግሩን እንደገና ይጀምራል፤ ለተሰነዘረው መቃወሚያ ሐሳብ ጥሩ መልስ ይሰጣል፤ በውጤቶቹ ይበረታታል።

15 ደቂቃ፦ አዲሱን የዓመት መጽሐፍ በቤተሰብ ተጠቀሙበት። የቤተሰቡ ራስ በ1994 የዓመት መጽሐፍ ውስጥ በመጀመሪያዎቹ 10 ገጾች ላይ ያሉትን የሚያነቃቁ የመግቢያ ሐሳቦች በመከለስ ቤተሰቡን ይመራል። ቤተሰቡ በእያንዳንዱ ሳምንት ከዓመት መጽሐፉ ጥቂት ገጾችን ለማንበብ እቅድ በማውጣት ይደመድማል። ጉባኤው አዲሱ የዓመት መጽሐፍ ገና ካልደረሰው ይህ ክፍል ለጉባኤው የሚያስፈልጉት ጉዳዮች ሊቀርብበት ይችላል።

መዝሙር 215 እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ግንቦት 16 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 191

10 ደቂቃ፦ የጉባኤው ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርትና ማኅበሩ የተላከለት መዋጮ የደረሰው መሆኑን ገልጾ ከሆነ ጨምረህ አቅርብ። የትኞቹን ብሮሹሮች ማበርከት እንደሚችልና ጥቂት መነጋገሪያ ነጥቦችን ግለጽ።

17 ደቂቃ፦ “ፍላጎት ያሳዩ ሰዎች ስታገኝ ተመልሰህ ጠይቃቸው።” ጥያቄና መልስ። በቀረቡት ሐሳቦች ላይ አንድ ወይም ሁለት ትዕይንቶችን አቅርብ።

18 ደቂቃ፦ “ከቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ሙሉ በሙሉ ጥቅም ማግኘት” የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች በንግግርና ከአድማጮች ጋር በመወያየት ያቀርበዋል። ሁሉም ክፍል እንዲወስዱና በደንብ እንዲያቀርቡ አበረታታ። የሳምንቱን የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ የመከታተልን አስፈላጊነት አጉልተህ ግለጽ። መላው ጉባኤ ክፍል ላቀረቡት ተማሪዎች ከሚሰጠው ምክር ምን ያህል እንደሚጠቀም አብራራ።

መዝሙር 53 እና የመደምደሚያ ጸሎት

ግንቦት 23 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 113

15 ደቂቃ፦ የጉባኤው ማስታወቂያዎች።

15 ደቂቃ፦ “ምክር በምትሰጥበት ጊዜ ሌሎችን ታከብራለህን?” በየካቲት 1, 1994 መጠበቂያ ግንብ ገጽ ከ25–9 በቀረበው ትምህርት ላይ የተመሠረተ በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር። የቤተሰብ ራሶች በቤተሰብ ክልል ውስጥ ምክር ሲሰጡ መሠረታዊ ሥርዓቶቹን እንዴት እንደሚጠቀሙባቸው ግለጽ።

15 ደቂቃ፦ ከ1994 የዓመት መጽሐፍ የሚገኘው ጥቅም። አንድ ሽማግሌና አንድ ዲያቆን በ1994 የዓመት መጽሐፍ ገጽ 10–18 አውጥተው ለቲኦክራሲያዊ ድርጅት ያላቸውን አድናቆት ለመገንባት የሚጠቅሙ አበረታች ነጥቦችን ይወያያሉ። አሁን ካለው ድርቅ ጋር የተያያዙ ችግሮችንና የመንግሥት አዳራሽ የግንባታ ፕሮጀክቶችን በተመለከተ በአካባቢያችሁ ያሉ ወንድሞችን ሕይወት የነኩ ጉዳዮችን ጥቀስ። ጉባኤው አዲሱ የዓመት መጽሐፍ ገና ካልደረሰው ይህን ክፍል በቅርቡ የሚደረገውን የክልል ስብሰባ ወይም የልዩ ቀን ስብሰባ ፕሮግራም በተመለከተ ዋና ዋና ነጥቦቸን ለመከለስ ሊውል ይችላል።

መዝሙር 19 እና የመደምደሚያ ጸሎት

ግንቦት 30 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 13

12 ደቂቃ፦ የጉባኤው ማስታወቂያዎች። በቅርቡ ከወጡት መጽሔቶች ውስጥ ዋና ዋና ርዕሶችን ከልስ። አጠር ያሉ አንድ ወይም ሁለት አቀራረቦችን አሳይ።

15 ደቂቃ፦ በሰኔ ወር ስለሚበረከቱ ጽሑፎች ተግባራዊ ሐሳቦችን አቅርብ።

18 ደቂቃ፦ በመጪዎቹ ወራት ረዳት አቅኚ ሆነህ ታገለግላለህን? ባለፉት ዓመታት በእነዚህ ወራት ረዳት አቅኚ ሆነው ካገለገሉት መካከል ለአንዳንዶች ቃለ ምልልስ አድርግላቸው። ወጣቶችንና የእረፍት ጊዜያቸውን ከሁሉ የተሻለውን ጥቅም በሚያስገኝ መንገድ ለመጠቀም ሁኔታው የሚፈቅድላቸውን ሁሉ አበረታታ። አንዳንዶች እምብዛም ያልተሠራባቸውን ወይም ገለልተኛ ክልሎችን በመሸፈን ሊረዱ ይችሉ ይሆናል።

መዝሙር 212 እና የመደምደሚያ ጸሎት

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2026)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2026 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ