ይህን ቡክሌት መጠቀም የሚቻልበት መንገድ
በዚህ ቡክሌት ላይ ለእያንዳንዱ ቀን የተሰጠውን ጥቅስና ጥቅሱን የሚያብራራ ሐሳብ ታገኛለህ። የዕለቱን ጥቅስም ሆነ ሐሳቡን በቀኑ ውስጥ በማንኛውም ሰዓት ላይ ማንበብ ቢቻልም ብዙዎች ጠዋት ላይ ማንበቡን ጠቃሚ ሆኖ አግኝተውታል። እንዲህ ማድረጋቸው ባነበቡት ሐሳብ ላይ ቀኑን ሙሉ ለማሰላሰል አስችሏቸዋል። የዕለቱን ጥቅስ በቤተሰብ ሆኖ መወያየትም በጣም ጠቃሚ ነው። በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የቤቴል ቤተሰቦች በቁርስ ሰዓት እንዲህ የማድረግ ልማድ አላቸው።
በእያንዳንዱ ሐሳብ መጨረሻ ላይ የተጠቀሰው ፊደልና አኃዝ ሐሳቡ ከምን ላይ እንደተወሰደ የሚጠቁም ነው። ለምሳሌ “w24.04 2 አን. 1, 3” የሚለው መግለጫ ከታች ባለው ሣጥን ላይ በተገለጸው መሠረት ሐሳቡ የተወሰደበትን ቦታ ያመለክታል። ስለ ጉዳዩ ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት የጥናት ርዕሱን መመልከት ይቻላል።
w24 |
የመጠበቂያ ግንቡ ዓመት (2024) |
04 |
የመጠበቂያ ግንቡ ወር (ሚያዝያ) |
2 |
ሐሳቡ የሚገኝበት ገጽ (ገጾች) |
አን. 1, 3 |
ሐሳቡ የሚገኝበት አንቀጽ (አንቀጾች) |