ከይሖዋ ወዳጆች ተማሩ
ኤልያስ
ይህን መልመጃ ተጠቅማችሁ የይሖዋ ወዳጅ ከሆነው ከኤልያስ ተማሩ።
ወላጆች፣ 1 ነገሥት 19:9, 10, 18, 19ን ከልጆቻችሁ ጋር አንብባችሁ ተወያዩበት።
ይህን መልመጃ አውርዱና አትሙት።
በመጀመሪያው ገጽ ላይ ያሉትን ሥዕሎች ቆርጣችሁ ካወጣችሁ በኋላ በሁለተኛው ገጽ ላይ ያሉትን ምልክቶች ተከትላችሁ ካርዱን አዘጋጁ። አብራችሁ በምትሠሩበት ጊዜ በቪዲዮው ላይ ያሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክሩ። በዚህ ክፍል ውስጥ የሚካተቱ ሌሎች ካርዶች ካሏችሁ ሁሉንም አንድ ላይ በማድረግ መጽሐፍ መሥራት ትችላላችሁ።