የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w26 ሐምሌ ገጽ 31
  • ለችግሩ ቶሎ እልባት ስጠው!

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ለችግሩ ቶሎ እልባት ስጠው!
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2026
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ጓደኛዬ የጎዳኝ ለምንድን ነው?
    ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎችና ተግባራዊ መሆን የሚችሉ መልሶች፣ ጥራዝ 2
  • ከይሖዋ ጋር ያለህ ተራ ትውውቅ ነው ወይስ ወዳጅነት?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
  • ጓደኞቼ የሚተዉኝ ለምንድን ነው?
    ንቁ!—1997
  • “ወዳጆች ብዬ ጠርቻችኋለሁ”
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2020
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2026
w26 ሐምሌ ገጽ 31
አንዲት እህት ከሌላ እህት ጋር ቤት ውስጥ ተቀምጣ ከልቧ ይቅርታ ስትጠይቃት።

ለችግሩ ቶሎ እልባት ስጠው!

ከአንድ ወንድም ጋር በተፈጠረ ቅሬታ ምክንያት ጓደኝነታችሁ አደጋ ላይ ወድቋል? ከሆነ ለችግሩ እልባት ለመስጠትና ጓደኝነታችሁን ለማዳን በትክክለኛው ዓላማ ተነሳስተህ አፋጣኝ እርምጃ መውሰድ ይኖርብሃል።a

ሁኔታውን በምሳሌ ለማስረዳት ያህል፣ የተሰበረ አጥንት በአግባቡ ከታከመ በጊዜ ሂደት ሙሉ በሙሉ ይድናል። ቶሎ ካልታከመ ግን ሥቃዩ አይቆምም። ይባስ ብሎም፣ አጥንቱ በትክክል ስለማይገጥም ዘላቂ ጉዳት ሊያስከትል ይችላል።

በተመሳሳይም ከአንድ የእምነት አጋራችን ጋር ያለን ወዳጅነት ከሻከረ ለችግሩ ቶሎ እልባት ልንሰጠው ይገባል። አለዚያ የስሜት ቁስላችን አይሽርም። በመካከላችን ቂም ይፈጠር ይሆናል፤ ይባስ ብሎም ጓደኝነታችን ሙሉ በሙሉ ሊበላሽ ይችላል። ኢየሱስ “ፈጥነህ ታረቅ” የሚል ምክር ሰጥቷል። (ማቴ. 5:25) ስለዚህ ወደ ጓደኛህ ቀርበህ በደግነት ሆኖም በግልጽ አነጋግረው። እንዲህ ማድረግ ከባድ ሊሆን የሚችለው ለምንድን ነው? ሁለት ምክንያቶችን እስቲ እንመልከት።

አንደኛ፣ ጉዳዩን አንስቶ መነጋገር ስለከበደህ ብቻ ችግሩ ባይፈታም እንኳ እንዲሁ አዳፍነህ ለማለፍ ትፈተን ይሆናል።b የኤዎድያንንና የሲንጤኪን ምሳሌ እንመልከት። እነዚህ እህቶች በመካከላቸው የተፈጠረውን አለመግባባት መፍታት ከብዷቸው ነበር። እነሱ ካሉበት አካባቢ ርቃ በምትገኘው በሮም የነበረው ሐዋርያው ጳውሎስ እንኳ ጉዳዩን መስማቱ ችግሩ ረዘም ላለ ጊዜ እንደቆየ ይጠቁማል። ጳውሎስ እነዚህ እህቶች ሰላም ለመፍጠር የቻሉትን ሁሉ እንዲያደርጉ አበረታቷቸዋል። (ፊልጵ. 4:2) ትሑት ከሆኑ፣ ስሜታቸውን በግልጽ ከተነጋገሩ እንዲሁም ከልባቸው ይቅር ከተባባሉ ጓደኝነታቸውን መልሰው ማደስ ይችላሉ።

ሁለተኛ፣ ሌላኛው ወገን ጥፋቱን አምኖ እንዲቀበል ትጠብቅ ይሆናል። ሆኖም ዓላማህ ጓደኝነታችሁን ማዳን ነው እንጂ ‘ጥፋተኛው ማን ነው’ የሚለውን መለየት እንዳልሆነ አስታውስ። የተሰበረ አጥንት የሚያክም ሐኪም፣ አጥንቱ እንዲሰበር ያደረገው ምንድን ነው የሚለውን በማጣራት ብዙ ጊዜ አያጠፋም። ከዚህ ይልቅ አጥንቱን በማከም ላይ ያተኩራል። አንተም ጓደኛህን ስታነጋግረው ‘ጥፋተኛው ማን ነው’ በሚለው ላይ ሳይሆን ‘ወዳጅነታችንን ማደስ የምንችለው እንዴት ነው’ በሚለው ላይ አተኩር።

ከወንድምህ ጋር የነበረህን ወዳጅነት የማደስ ግብ ይዘህ ለምን ዛሬውኑ አታነጋግረውም? ‘ተቆጥተህ እያለ ፀሐይ አይጥለቅብህ።’ (ኤፌ. 4:26) ለችግሩ ቶሎ እልባት ለመስጠት እርምጃ መውሰድህ ‘አንድ ላይ የሚያስተሳስረው የሰላም ማሰሪያ’ እንዳይበጠስ ያደርጋል።—ኤፌ. 4:1-3

a ትናንሽ ቅሬታዎች በግል በመነጋገርና በነፃ ይቅር በመባባል መፈታት አለባቸው። (ማቴ. 5:23, 24) ከባድ በደል ከተፈጸመ ግን የሽማግሌዎችን እርዳታ መጠየቅ ሊያስፈልግ ይችላል። (ማቴ. 18:17) አንድ ክርስቲያን የሽማግሌዎችን እርዳታ የሚጠይቀው በማቴዎስ 18:15, 16 ላይ የተጠቀሱትን እርምጃዎች ከወሰደ በኋላ ብቻ ነው።

b አንድ የእምነት አጋራችን ቅር ቢያሰኘንም ችግሩ ጓደኝነታችንን አደጋ ላይ የሚጥል ዓይነት ካልሆነ ጉዳዩን ችላ ብለን ለማለፍ ልንመርጥ እንችላለን።—ምሳሌ 26:20

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2026)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2026 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ