የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb25 ሐምሌ ገጽ 4-5
  • ከሐምሌ 14-20

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ከሐምሌ 14-20
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2025
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2025
mwb25 ሐምሌ ገጽ 4-5

ከሐምሌ 14-20

ምሳሌ 22

መዝሙር 79 እና ጸሎት | የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

1. ልጆችን ለማሳደግ የሚረዱ ጠቃሚ መሠረታዊ ሥርዓቶች

(10 ደቂቃ)

ልጆቻችሁን ለሕይወት ውጣ ውረድ አዘጋጇቸው (ምሳሌ 22:3፤ w20.10 27 አን. 7)

ከተወለዱበት ጊዜ አንስቶ አሠልጥኗቸው (ምሳሌ 22:6፤ w19.12 26 አን. 17-19)

ፍቅራዊ ተግሣጽ ስጧቸው (ምሳሌ 22:15፤ w06 4/1 9 አን. 4)

አንድ አባት መጽሐፍ ቅዱስን ተጠቅሞ ልጁን በደግነት ሲያስረዳት። ታብሌቷ ላይ የዝግመተ ለውጥን የተለያዩ ደረጃዎች የሚያሳዩ ሥዕሎች አሉ።

2. መንፈሳዊ ዕንቁዎች

(10 ደቂቃ)

  • ምሳሌ 22:29—ይህን ጥቅስ ከጉባኤ እንቅስቃሴዎች ጋር በተያያዘ በሥራ ላይ ማዋል የምንችለው እንዴት ነው? ይህስ ምን ጥቅም ያስገኛል? (w21.08 22 አን. 11)

  • ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?

3. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ

(4 ደቂቃ) ምሳሌ 22:1-19 (th ጥናት 10)

በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር

4. ውይይት መጀመር

(3 ደቂቃ) ከቤት ወደ ቤት። (lmd ምዕራፍ 5 ነጥብ 4)

5. ውይይት መጀመር

(4 ደቂቃ) መደበኛ ያልሆነ ምሥክርነት። ግለሰቡ ለወላጆች የሚጠቅም መረጃ ከ​jw.org ላይ ማግኘት የሚችለው እንዴት እንደሆነ አሳየው። (lmd ምዕራፍ 1 ነጥብ 4)

6. ንግግር

(5 ደቂቃ) ijwyp ርዕስ 100—ጭብጥ፦ የወላጆቼን ሕግ ጥሻለሁ—ምን ባደርግ ይሻላል? (th ጥናት 20)

ክርስቲያናዊ ሕይወት

መዝሙር 134

7. ታጋሽ ሁኑ፤ ሆኖም ልል አትሁኑ

(15 ደቂቃ) ውይይት።

ልጆችን ማሳደግ ከፍተኛ ትዕግሥት ይጠይቃል። ወላጆች ለልጆቻቸው ያልተከፋፈለ ትኩረትና ሰፊ ጊዜ ሊሰጧቸው ይገባል። (ዘዳ 6:6, 7) ወላጆች በልጆቻቸው ልብ ውስጥ ያለውን ነገር ለማወቅ ጥያቄዎችን በመጠቀም የልባቸውን ቀድተው ማውጣትና ሐሳባቸውን ሲገልጹ በጥሞና ማዳመጥ ይኖርባቸዋል። (ምሳሌ 20:5) በተጨማሪም ወላጆች ልጆቻቸው አንድን መመሪያ መረዳትና በሥራ ላይ ማዋል እንዲችሉ መመሪያውን በተደጋጋሚ መናገር ሊያስፈልጋቸው ይችላል።

ይሁንና ታጋሽ የሆኑ ወላጆች ልል አይደሉም። ይሖዋ ለልጆቻቸው ገደብ የማውጣት እንዲሁም ልጆቻቸው ሲያጠፉ የመገሠጽ ሥልጣን ሰጥቷቸዋል።—ምሳሌ 6:20፤ 23:13

ኤፌሶን 4:31ን አንብብ። ከዚያም እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦

  • ወላጆች ተቆጥተው ሳለ ለልጆቻቸው ተግሣጽ መስጠት የሌለባቸው ለምንድን ነው?

ገላትያ 6:7ን አንብብ። ከዚያም እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦

  • ወላጆች፣ ልጆቻቸው ለሠሩት ነገር መዘዙን እንደሚያጭዱ ማስተማራቸው አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

“‘በትዕግሥት እርስ በርሳችሁ በፍቅር ተቻቻሉ’—ልጆቻችሁን” ከተባለው ቪዲዮ ላይ የተወሰደ ሥዕል። ማክስ ልጁን ሱን በትዕግሥት ሲያዳምጣት።

‘በትዕግሥት እርስ በርሳችሁ በፍቅር ተቻቻሉ’—ልጆቻችሁን የተባለውን አጭር ድራማ አጫውት። ከዚያም እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦

  • ከቪዲዮው ምን ትምህርት አግኝታችኋል?

8. የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

(30 ደቂቃ) lfb “የበላይ አካሉ መልእክት፣” የክፍል 1 ማስተዋወቂያ እና ትምህርት 1

የመደምደሚያ ሐሳብ (3 ደቂቃ) | መዝሙር 6 እና ጸሎት

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2026)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2026 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ