ከነሐሴ 10-16
ዘፀአት 15–16
መዝሙር 149 እና ጸሎት
የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)
ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት
“ይሖዋን በመዝሙር አወድሱት”፦ (10 ደቂቃ)
ዘፀ 15:1, 2—ሙሴና የእስራኤል ወንዶች ይሖዋን በመዝሙር አወድሰውታል (w95 10/15 11 አን. 11)
ዘፀ 15:11, 18—ይሖዋ ውዳሴ ይገባዋል (w95 10/15 11-12 አን. 15-16)
ዘፀ 15:20, 21—ሚርያምና የእስራኤል ሴቶች ይሖዋን በመዝሙር አወድሰውታል (it-2 454 አን. 1፤ 698)
መንፈሳዊ ዕንቁዎችን በምርምር ማግኘት፦ (10 ደቂቃ)
ዘፀ 16:13—ይሖዋ እስራኤላውያን በምድረ በዳ በነበሩበት ጊዜ እነሱን ለመመገብ ድርጭቶችን የመረጠው ለምን ሊሆን ይችላል? (w11 9/1 14)
ዘፀ 16:32-34—የመናው ማሰሮ የሚቀመጠው የት ነበር? (w06 1/15 31)
ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ይሖዋን፣ የመስክ አገልግሎትን ወይም ሌሎች ነገሮችን በተመለከተ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) ዘፀ 16:1-18 (th ጥናት 10)
በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር
መመሥከር—ቪዲዮ፦ (4 ደቂቃ) በውይይት የሚቀርብ። ቪዲዮውን አጫውት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠይቅ፦ ሊዲያ ጥያቄዎችን ጥሩ አድርጋ የተጠቀመችው እንዴት ነው? የጥቅሱን ዓላማ ግልጽ ያደረገችው እንዴት ነው?
መመሥከር፦ (3 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) በውይይት ናሙናው ጀምር። ከዚያም በማስተማሪያ መሣሪያዎቻችን ውስጥ ከሚገኙት ጽሑፎች አንዱን አበርክት። (th ጥናት 3)
መመሥከር፦ (5 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) በውይይት ናሙናው ጀምር። ከዚያም መጽሐፍ ቅዱስን የምናስጠናው እንዴት ነው? የተባለውን ቪዲዮ አስተዋውቅና ተወያዩበት። (ክፍሉ ላይ ቪዲዮውን ማጫወት አያስፈልግህም።) (th ጥናት 9)
ክርስቲያናዊ ሕይወት
“አቅኚ በመሆን ይሖዋን አወድሱት”፦ (15 ደቂቃ) በውይይት የሚቀርብ። በሞንጎሊያ የሚገኙ ሦስት እህትማማቾች የተባለውን ቪዲዮ አጫውት። በአሁኑ ወቅት በአቅኚነት እያገለገለ ላለ ወይም ቀደም ሲል በአቅኚነት ላገለገለ ወንድም (እህትም ልትሆን ትችላለች) ቃለ መጠይቅ አድርግ። የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠይቅ፦ ምን ተፈታታኝ ሁኔታ አጋጥሞሃል? ምን በረከቶች አግኝተሃል?
የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦ (30 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) jy ምዕ. 118
የመደምደሚያ ሐሳብ (3 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
መዝሙር 109 እና ጸሎት