የቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ
ታኅሣሥ 28, 2015 በሚጀምር ሳምንት በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ላይ መልስ የሚሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው። እያንዳንዱ ነጥብ ውይይት የሚደረግበት መቼ እንደሆነ የሚጠቁም ቀን በጥያቄዎቹ ላይ የተካተተው በየሳምንቱ ለትምህርት ቤቱ ዝግጅት በምናደርግበት ወቅት ምርምር እንድናደርግ ታስቦ ነው።
ይሖዋ የዘላለም ንጉሥ ሆኖ ሳለ በ1 ዜና መዋዕል 16:31 ላይ “ይሖዋ ነገሠ” የተባለው ለምንድን ነው? [ኅዳር 2, w14 1/15 ገጽ 11 አን. 14]
ዳዊት የለጋስነት መንፈስ እንዲያሳይ ያነሳሳው ምንድን ነው? እኛስ እንዲሁ እንድናደርግ ምን ሊረዳን ይችላል? (1 ዜና 22:5) [ኅዳር 9, w05 10/1 ገጽ 11 አን. 7]
ዳዊት “የአባትህን አምላክ እወቅ” በማለት ለሰለሞን የተናገረው ሐሳብ ምን ትርጉም አለው? (1 ዜና 28:9) [ኅዳር 16, w10 11/1 ገጽ 30 አን. 3, 7]
በ2 ዜና መዋዕል 1:10 ላይ የሚገኘው ሰለሞን ያቀረበው ልመና ስለ እሱ ምን ይጠቁማል? እኛስ ለይሖዋ የምናቀርበውን ጸሎት ይዘት በመመርመር ምን ማወቅ እንችላለን? (2 ዜና 1:11, 12) [ኅዳር 23, w05 12/1 ገጽ 19 አን. 6]
ሁለተኛ ዜና መዋዕል 6:29, 30 እንደሚገልጸው ይሖዋ ምን ልዩ ችሎታ አለው? በጸሎት አማካኝነት የልባችንን ግልጥልጥ አድርገን መናገር ያለብን ለምንድን ነው? (መዝ. 55:22) [ኅዳር 30, w10 12/1 ገጽ 11 አን. 7]
አሳ እጅግ ግዙፍ የሆነውን ሠራዊት ማሸነፍ እንዲችል ለመጸለይ ያነሳሳው ምንድን ነው? እኛስ ከምናደርገው መንፈሳዊ ውጊያ ጋር በተያያዘ ስለ ምን ነገር እርግጠኛ መሆን እንችላለን? (2 ዜና 14:11) [ታኅ. 7, w12 8/15 ገጽ 8 አን. 6 እስከ ገጽ 9 አን. 1]
ንጉሥ ኢዮሳፍጥ ጥፋት በሠራበት ወቅት ይሖዋ ጉዳዩን የያዘበት መንገድ አምላክ ለእኛ ያለውን ፍቅር የሚያረጋግጠው እንዴት ነው? ይህስ እኛ ለሌሎች ያለንን አመለካከት የሚነካው እንዴት ነው? (2 ዜና 19:3) [ታኅ. 14, w03 7/1 ገጽ 17 አን. 13፤ cl ገጽ 244-245 አን. 12]
በዘመናችን ‘ቦታ ቦታችንን ይዘን ዝም ብለን የምንቆመው’ ለምንና እንዴት ነው? (2 ዜና 20:17) [ታኅ. 21, w05 12/1 ገጽ 21 አን. 3፤ w03 6/1 ገጽ 21 አን. 15-16]
ከኢዮራም ሞት ጋር በተያያዘ በ2 ዜና መዋዕል 21:20 ላይ ምን ኃይለኛ ማሳሰቢያ እናገኛለን? [ታኅ. 21, w98 11/15 ገጽ 32 አን. 4]
በ2 ዜና መዋዕል 26:5 ላይ የሚገኘው ዘገባ እንደሚናገረው በወጣቱ ዖዝያ ላይ በጎ ተጽዕኖ ያሳደረው ማን ነው? በአሁኑ ጊዜ ያሉ ወጣቶች በጉባኤው ውስጥ ካሉ የጎለመሱ ክርስቲያኖች ጥቅም ማግኘት የሚችሉት እንዴት ነው? [ታኅ. 28, w07 12/15 ገጽ 10 አን. 2, 4]