የቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ
ታኅሣሥ 30, 2013 በሚጀምር ሳምንት በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ላይ መልስ የሚሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው። እያንዳንዱ ነጥብ ውይይት የሚደረግበት መቼ እንደሆነ የሚጠቁም ቀን በጥያቄዎቹ ላይ የተካተተው በየሳምንቱ ለትምህርት ቤቱ ዝግጅት በምናደርግበት ወቅት ምርምር እንድናደርግ ታስቦ ነው።
1. ከመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር በሚኖረን ግንኙነት ገርነትን ወይም የዋህነትን ለማሳየት ምን ሊረዳን ይችላል? (ቲቶ 3:2) [ኅዳር 4, w03 4/1 ገጽ 25 አን. 18-19]
2. በፊልሞና 4, 5 እና 7 ላይ ከሚገኘው ጳውሎስ ለፊልሞና ከተናገረው ሐሳብ ምን ትምህርት እናገኛለን? [ኅዳር 4, w08 10/15 ገጽ 31 አን. 1, 2፤ w92 4/15 ገጽ 25 አን. 2]
3. ወደ አምላክ እረፍት መግባት የምንችለው እንዴት ነው? (ዕብ. 4:9-11) [ኅዳር 11, w11 7/15 ገጽ 27-28 አን. 16, 17]
4. “ጽድቅ እንዲፈጸም የሚያደርግ ተግባር” ከፈጸሙት ከሳሙኤል እንዲሁም ታማኝ ከሆኑት መሳፍንትና ነቢያት ምን እንማራለን? (ዕብ. 11:32, 33) [ኅዳር 18, w11 1/1 ገጽ 25 አን. 5, 6]
5. ያዕቆብ ‘ከላይ የሆነው ጥበብ በመጀመሪያ ንጹሕ ከዚያም ሰላማዊ’ እንደሆነ የተናገረው ለምንድን ነው? (ያዕ. 3:17) [ኅዳር 25, w11 8/15 ገጽ 30-31 አን. 15]
6. ‘ምሥራቹ የተሰበከላቸው ሙታን’ እነማን ናቸው? (1 ጴጥ. 4:6) [ታኅ. 2, w08 11/15 ገጽ 21 አን. 7]
7. በአንደኛ ዮሐንስ 2:7, 8 ላይ ዮሐንስ “የቆየ” እና “አዲስ” ትእዛዝ በማለት የጠራው የትኛውን ትእዛዝ ነው? [ታኅ. 9, w08 12/15 ገጽ 27 አን. 6]
8. “አልፋና ኦሜጋ” እንዲሁም “የመጀመሪያውና የመጨረሻው” የሚሉት መጠሪያዎች የሚያመለክቱት ማንን ነው? (ራእይ 1:8, 17) [ታኅ. 16, w09 1/15 ገጽ 30 አን. 6]
9. ቅቡዓን ክርስቲያኖች “ማኅተም” የተደረገባቸው በየትኞቹ ሁለት መንገዶች ነው? (ራእይ 7:3) [ታኅ. 23, w07 1/1 ገጽ 31 አን. 2]
10. አስቀድሞ የተነገሩት በረከቶች በመንግሥቱ አገዛዝ ሥር እውን እንደሚሆኑ እርግጠኛ መሆን የምንችለው ለምንድን ነው? ይህን ማወቃችንስ ምን እንድናደርግ ሊያነሳሳን ይገባል? (ራእይ 21:5, 6) [ታኅ. 30, re ገጽ 303-304 አን. 9]