ነሐሴ 3 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 97 (217)
❑ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
❑ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘኍልቍ 4-6
ቁ. 1፦ ዘኍልቍ 4:1-16
ቁ. 2፦ ማንን መታዘዝ እንዳለብን ማወቅ የምንችለው እንዴት ነው? (lr ምዕ. 28)
ቁ. 3፦ አንድ ሰው እውነተኛ ደስታ ያለበት ሕይወት እንዲያገኝ የግድ ወደ ሰማይ መሄድ ይኖርበታል? (rs ገጽ 163 አን. 4-6)
❑ የአገልግሎት ስብሰባ፦
መዝሙር 73 (166)
5 ደቂቃ፦ ማስታወቂያዎች።
10 ደቂቃ፦ የመንግሥቱ ሰባኪዎች ይበልጥ ወደሚያስፈልጉበት ወይም ብዙም ወዳልተሠራባቸው አካባቢዎች ሄደው ላገለገሉ ሁለት ወይም ሦስት አስፋፊዎች ቃለ ምልልስ አድርግ። ወደዚያ ከመሄዳቸው በፊት ምን ፍርሃት ነበራቸው? ፍርሃታቸውን ያሸነፉትስ እንዴት ነው? ይሖዋ ጥረታቸውን የባረከላቸው እንዴት ነው? በመስክ አገልግሎት ሲካፈሉ ያገኟቸውን አንድ ወይም ሁለት ተሞክሮዎች እንዲናገሩ ወይም በአጭሩ በሠርቶ ማሳያ እንዲያሳዩ አድርግ።
10 ደቂቃ፦ ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።
10 ደቂቃ፦ የማስተማር ችሎታችሁን ለማሻሻል ጥረት ስታደርጉ በይሖዋ ታመኑ። በአገልግሎት ትምህርት ቤት መጽሐፍ ከገጽ 56 አንቀጽ 1 እስከ ገጽ 57 አንቀጽ 2 ባለው ሐሳብ ላይ ተመሥርቶ ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ።
መዝሙር 75 (169)