የቲኦክራሲያዊ አገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ
ነሐሴ 25, 2008 በሚጀምር ሳምንት በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ላይ መልስ የሚሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ከሐምሌ 7 እስከ ነሐሴ 25, 2008 ድረስ ባሉት ሳምንታት ውስጥ በቀረቡት ክፍሎች ላይ የተመሠረተ የ30 ደቂቃ ክለሳ ይመራል።
የንግግር ባሕርይ
1. እውነትን ለሌሎች ስናካፍል ምክንያታዊ መሆናችንን ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው? (ፊልጵ. 4:5 NW) [be ገጽ 251 አን. 3]
2. በመጽሐፍ ቅዱስ ለማያምኑ ሰዎች ስንመሠክር፣ ጳውሎስ በአርዮስፋጎስ ከግሪካውያን ጋር ሲወያይ የተጠቀመበት ዘዴ እንዴት ሊረዳን ይችላል? (ሥራ 17:22, 23) [be ገጽ 252 አን. 1-2]
3. የምናነጋግረው ሰው እንደተሳሳተ እርግጠኛ ብንሆንም እንኳ ከግለሰቡ ጋር በምናደርገው ውይይት ምክንያታዊ መሆናችንን ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው? [be ገጽ 253 አን. 1-2]
4. ንግግራችን አሳማኝ እንዲሆን ለማድረግ ምን ነገር ማስታወስ ይኖርብናል? [be ገጽ 255 አን. 3፣ ሣጥኑ]
5. የአድማጫችንን ልብ ለመንካት የማስተዋል ችሎታችንን መጠቀም የምንችለው እንዴት ነው? (ምሳሌ 20:5) [be ገጽ 258 አን. 1-5]
ክፍል ቁጥር 1
6. እህቶች መቼታቸውን ሲዘጋጁ ምን ነገር ማስታወስ ይገባቸዋል? [be ገጽ 44 አን. 5-6]
7. ወንድሞች የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ጎላ ያሉ ነጥቦችን ሲያቀርቡ ዓላማቸው ምን መሆን ይኖርበታል? (ነህ. 8:8) [be ገጽ 47 አን. 2-3]
8. አንድ ወንድም በአገልግሎት ስብሰባ ላይ ሠርቶ ማሳያ ወይም ቃለ ምልልስ ያለው ክፍል ሲሰጠው ምን ማድረግ ይኖርበታል? [be ገጽ 49 አን. 5]
9. የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ፣ ምሥክርነቱ ስለሚሰጥበት መንገድና ስለሚኖረው ስፋት ጎላ አድርጎ የሚገልጸው እንዴት ነው? (ሥራ 20:20, 21፤ 28:23 NW ) [bsi08-1 ገጽ 16 አን. 35]
10. አንድ የሕዝብ ተናጋሪ ንግግሩ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረተ እንዲሆን ምን ማድረግ ይኖርበታል? (ሥራ 17:2, 3) [be ገጽ 52 አን. 6 እስከ ገጽ 53 አን. 2]
ሳምንታዊው የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ
11. የፊልጵስዩስ ከተማ ነዋሪ የሆነው የወህኒ ቤት ጠባቂ “ራሱን ለመግደል” የፈለገው ለምን ነበር? (ሥራ 16:25-27) [w90 5/15 (w-AM 10-111) ገጽ 25 ላይ የሚገኘው ሣጥን]
12. አርስጥሮኮስና ጋይዮስ ለደረሰባቸው ስደት ምላሽ የሰጡት እንዴት ነበር? (ሥራ 19:29፤ 20:4, 5) [w08 2/15 ገጽ 10 አን. 16-17]
13. ሳውል ‘መውጊያውን ይጋፋ’ ነበር ሲባል ምን ማለት ነው? (ሥራ 26:14) [w03 10/1 ገጽ 32]
14. ኃጢአት፣ አምላክ ለእስራኤል የሰጠው ‘ትእዛዝ ባስገኘው ዕድል ሊጠቀም’ የቻለው እንዴት ነው? (ሮሜ 7:8, 11) [w08 6/15 “የይሖዋ ቃል ሕያው ነው — የሮሜ መጽሐፍ ጎላ ያሉ ነጥቦች”]
15. በጠላታችን ራስ ላይ ‘የእሳት ፍም የምንከምረው’ እንዴት ነው? (ሮሜ 12:20) [w08 6/15 “የይሖዋ ቃል ሕያው ነው—የሮሜ መጽሐፍ ጎላ ያሉ ነጥቦች”]