ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች:- ሐምሌ እና ነሐሴ:- ብሮሹሮች፤ መስከረም:- ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው?፤ ጥቅምት:- መጽሔቶች እና ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ይበልጥ ማወቅ ትፈልጋለህ? (ትራክት ቁጥር 26)
◼ ጥናት ለማስጀመርም ሆነ ለመምራት አምላክ ከእኛ የሚፈልገው የሚለውን ብሮሹር ከመጠቀም ይልቅ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የተባለውን መጽሐፍ መጠቀም ይኖርብናል። ይሁንና በእጃችን ላይ ያለው እስኪያልቅ ድረስ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው የተባለውን ብሮሹር ማበርከታችንን እንቀጥላለን።
◼ የነሐሴ ወር አምስት ቅዳሜና እሁዶች ስላሉት ረዳት አቅኚ ለመሆን አመቺ ነው።
◼ ከመስከረም ጀምሮ የወረዳ የበላይ ተመ ልካቾች የሚሰጡት የሕዝብ ንግግር “በን ጹሕ አቋም መመላለስ” የሚል ርዕስ ያለው ይሆናል።
◼ ወላጆች፣ መስከረም ወር ላይ ለሚጀምረው አዲስ የትምህርት ዘመን ልጆቻችሁን ለማዘጋጀት ትምህርት ቤትና የይሖዋ ምሥክሮች ከሚለው ብሮሹር ተስማሚ የሆኑ ክፍሎችን በመምረጥ ከልጆቻችሁ ጋር ውይይት እንድታደርጉ እናበረታታችኋለን። ይህ ብሮሹር በእጃችን የሚገኝ በመሆኑ ማዘዝ ትችላላችሁ።
◼ አዲስ የደረሱን ጽሑፎች:- ቀለል ባለ ቻይንኛ:- ክርኤሽን፤ እንግሊዝኛ:- በዲቪዲ:- ጄሆቫስ ዊትነስስ...ኦርጋናይዝድ ቱ ሼር ዘ ጉድ ኒውስ ኤንድ አወር አሶሲየሽን ኦቭ ብራዘርስ (dvjwa)፤ በሲዲ:- የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት፣ ወደ ይሖዋ ቅረብ፣ የቤተሰብ ደስታ፣ ታላቅ ሰው፣ የምትወዱት ሰው ሲሞት፤ በኤምፒ3:- የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት፣ የቤተሰብ ደስታ፣ ከታላቁ አስተማሪ ተማሩ፣ ታላቅ ሰው፣ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው፣ የመንግሥቱ ጣዕመ ዜማዎች፣ አዲስ ዓለም ትርጉም፣ ሳቲስፋይንግ ላይፍ።
◼ በድጋሚ የደረሱን ጽሑፎች:- አማርኛ:- የውዳሴ መዝሙር፤ እንግሊዝኛ:- ማመራመር፣ ጠለቅ ብሎ ማስተዋል፣ የመጠበቂያ ግንብ ማኅበር ጽሑፎች ማውጫ 2001-2005፤ ፈረንሳይኛ:- የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ፤ ኦሮምኛ:- አምላክ ከእኛ የሚፈልገው።