ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች ሰኔ:- ለቤተሰብ ደስታ፤ ሐምሌና ነሐሴ:- ብሮሹሮች፤ መስከረም:- ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው?
◼ ሰብሳቢ የበላይ ተመልካቹ አሊያም እርሱ የወከለው ሌላ ወንድም የመጋቢትን፣ የሚያዝያንና የግንቦትን የጉባኤ ሒሳብ መመርመር ይኖርበታል። የሒሳብ ምርመራው ውጤት የሚቀጥለው የሒሳብ ሪፖርት ከቀረበ በኋላ ለጉባኤው መነበብ አለበት።—ስለ ጉባኤ ሒሳብ አያያዝ የተሰጡ መመሪያዎች (S-27) የሚለውን ተመልከት።
◼ አዲስ የደረሰን ጽሑፍ:- ፈረንሳይኛ:- የ2007 የዓመት መጽሐፍ።
◼ በድጋሚ የደረሱን ጽሑፎች:- አማርኛ:- ማመራመር፣ የወጣቶች ጥያቄ፣ የውዳሴ መዝሙር፤ እንግሊዝኛ:- ኖኅና ዳዊት የተባለው ዲቪዲ፣ የመንግሥቱ ጣዕመ ዜማዎች ቁ. 4፣ የአገልግሎት ክልል መያዣ ፕላስቲክ፣ የባጅ መያዣ ፕላስቲክ፤ ፈረንሳይኛ:- የወጣቶች ጥያቄ፤ ትግርኛ:- ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!