የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 4/99 ገጽ 7
  • ማስታወቂያዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ማስታወቂያዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1999
የመንግሥት አገልግሎታችን—1999
km 4/99 ገጽ 7

ማስታወቂያዎች

◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች ሚያዝያና ግንቦት፦ የመጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! ነጠላ ቅጂዎችና ኮንትራት። ፍላጎት ላላቸው ሰዎች ለማበርከት እንድትችሉ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው የተባለው ብሮሹር ይኑራችሁ። የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናትም ለማስጀመር ጥረት አድርጉ። ሰኔ፦ ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎችና ተግባራዊ መሆን የሚችሉ መልሶች። ሐምሌና ነሐሴ፦ ቀጥሎ ከተዘረዘሩት ባለ 32 ገጽ ብሮሹሮች ማንኛውንም ማበርከት ይቻላል:- አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባልን?፣ በምድር ላይ ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ በሥላሴ ማመን ይገባሃልን?፣ ለዘላለም ጸንቶ የሚኖረው መለኮታዊው ስም፣ የአምላክ መንግሥት ገነትን ታመጣለች፣ ስንሞት ምን እንሆናለን?፣ የሕይወት ዓላማ ምንድን ነው? እንዴትስ ልታገኘው ትችላለህ?፣ የምትወዱት ሰው ሲሞት፣ እና የሙታን መናፍስት—ሊረዱህ ወይም ሊጎዱህ ይችላሉን? ደግሞስ በእርግጥ አሉን?

◼ አስፋፊዎች ለማንኛውም ጉባኤ ያልተመደበ ወይም በተደጋጋሚ ያልተሸፈነ የአገልግሎት ክልል ሲሸፍኑ እውቀት መጽሐፍ ወይም አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ብሮሹር የተባለውን ሊያበረክቱ ይችላሉ። የትኛውንም ሌላ ጽሑፍ በተለይ ደግሞ ለዘላለም መኖር መጽሐፍና የቆዩ መጽሔቶችን ማበርከትም ይቻላል። ሁሉም ቤት ላልተገኙ ወይም ጽሑፍ ላልወሰዱ ሰዎች የሚያበረክቷቸው የተለያዩ ዓይነት ትራክቶች መያዝ አለባቸው። ፍላጎት ያሳዩ ሰዎችን ተከታትሎ ለመርዳት ጥረት መደረግ አለበት።

◼ የ1999 የአውራጃ ስብሰባ ደረት ላይ የሚለጠፍ ካርድ ከሚላኩላችሁ ጽሑፎች ጋር ከነሐሴ ጀምሮ ስለሚላክ ማዘዝ አያስፈልግም። የሚላከው ካርድ ብዛት እንደየጉባኤው ስፋት ይሆናል። ጉባኤዎች ተጨማሪ ካርድ ካስፈለጋቸው በጽሑፍ ማዘዣ ቅጽ (S-14-AM) ማዘዝ ይኖርባቸዋል። ጉባኤ ውስጥ ደረት ላይ የሚለጠፈውን ካርድ መያዣ ፕላስቲክ ማግኘት የሚፈልጉ ካሉ ማዘዝ ይቻላል።

◼ የጉባኤ ጸሐፊዎች የሚከተሉት የአቅኚነት ቅጾች በበቂ መጠን መኖሩን ማረጋገጥ ያስፈልጋቸዋል:- የዘወትር አቅኚነት አገልግሎት ማመልከቻ (S-205)፣ የረዳት አቅኚነት አገልግሎት ማመልከቻ ቅጽ (S-205b) እና የዘወትር አቅኚነት አገልግሎትን ያቋረጡ ሰዎች ማሳወቂያ (S-206)። እነዚህን ቅጾች በጽሑፍ ማዘዣ ቅጽ (S-14-AM) ማዘዝ ይቻላል። ቢያንስ ለአንድ ዓመት ያህል የሚበቃ ቅጽ ይኑራችሁ። የዘወትር አቅኚነት ማመልከቻ ቅጹ በትክክል መሞላቱን ለማረጋገጥ ቅጹን እንደገና ተመልከቱ። አመልካቾች የተጠመቁበትን ትክክለኛ ቀን ማስታወስ ካልቻሉ ቀኑን በመገመት መዝግበው መያዝ ይኖርባቸዋል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2026)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2026 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ