ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች:- ከጥቅምት እስከ ታኅሣሥ፦ በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ በ3.00 ብር።
◼ የ1998 “የአምላክ የሕይወት መንገድ” የተሰኘው የአውራጃ ስብሰባ የሚደረግባቸው ቀናት እንደሚከተለው ተስተካክለዋል:-
ድሬዳዋ፦
September 25-27, 1998
መስከረም 15–17, 1991 (እኢአ)
ደሴ፦
October 2-4, 1998
መስከረም 22–24, 1991 (እኢአ)
ሻሸመኔ፦
October 9-11, 1998
መስከረም 29 እስከ ጥቅምት 1, 1991 (እኢአ)
አዲስ አበባ፦
October 16-18, 1998
ጥቅምት 6–8, 1991 (እኢአ)
ጅማ፦
October 23-25, 1998
ጥቅምት 13–15, 1991 (እኢአ)
◼ ከዚህ የመንግሥት አገልግሎታችን አባሪዎች መካከል መኖር የነበረበት “የ1999 ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ፕሮግራም” በቅርቡ የሚደርሳችሁ ሲሆን ዓመቱን በሙሉ ልንጠቀምበት እንድንችል በጥሩ ሁኔታ ልንይዘው ይገባል።
◼ የጉባኤያችሁ የስብሰባ ሰዓት ከጥር 1 ጀምሮ የሚቀየር ከሆነ አዲሱን የስብሰባ ሰዓት የያዘ የስብሰባ መጋበዣ ወረቀቶች ማዘዝ ያስፈልጋችሁ ይሆናል።
◼ ጉባኤዎች በጥቅምት ወር በሚልኩት የጽሑፍ ማዘዣ ቅጽ ላይ ቅዱሳን ጽሑፎችን በየዕለቱ መመርመር-1999 ማዘዝ መጀመር ይኖርባቸዋል። ቡክሌቱ በአማርኛ፣ በእንግሊዝኛና በትግርኛ ቋንቋ ይገኛል። እነዚህ ቡክሌቶች እንደደረሱን እንልክላችኋለን። ቅዱሳን ጽሑፎችን መመርመር የተባለው ቡክሌት በልዩ ትእዛዝ የሚገኝ ነው።
◼ በድጋሚ የደረሱን፦ አማርኛ፦ ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ እውቀት፣ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው?፣ አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባልን?፤ ጣሊያንኛ፦ ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ እውቀት፣ የቤተሰብ ደስታ የሚገኝበት ቁልፍ፣ አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባልን?፣ ትራክት ቁጥር 14 ጥና 15።
◼ በድጋሚ ይመጣሉ ብለን የምንጠብቃቸው፦ እንግሊዝኛ፦ ቅዱስ ጽሑፉ ሁሉ በአምላክ መንፈስ አነሳሽነት የተጻፈና ጠቃሚ ነው፣ ኮንኮርዳንስ፣ የአዲሲቱ ዓለም የቅዱሳን ጽሑፎች ትርጉም (Bi12)፣ የቴፕ ክሮች:- ታላቅ ሰው (csgt)፣ የአገልግሎት ክልል ካርድ መያዣ ፕላስቲክ።
◼ በቅርቡ ይመጣሉ ብለን የምንጠብቃቸው፦ እንግሊዝኛ፦ ማውጫ 1997፤ የቴፕ ክሮች:- የቤተሰብ ደስታ (csfy)።