የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 7/96 ገጽ 3
  • አጋጣሚዎችን ለመጠቀም ንቁ ሁን

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • አጋጣሚዎችን ለመጠቀም ንቁ ሁን
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1996
የመንግሥት አገልግሎታችን—1996
km 7/96 ገጽ 3

አጋጣሚዎችን ለመጠቀም ንቁ ሁን

1 ለምናገኛቸው አጋጣሚዎች ንቁ ከሆንን በጥሩ መንገድ ልንጠቀምባቸው የምንችላቸው በአገልግሎታችን የምናገኛቸው ብዙ አመቺ ሁኔታዎች አሉ። (ቆላ. 4:5) ለምሳሌ ያህል አንድ ሰው “እነዚህን መጽሔቶች እወዳቸዋለሁ” ሊል ይችላል። ይህ ኮንትራት እንዲገባ ወይም የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እንዲጀምር ለመጠየቅ ጥሩ አጋጣሚ ነው! ሌላ ሰው ደግሞ “ይህ ጽሑፍ ጥሩ ይመስላል። ይሁን እንጂ ገንዘብ የለኝም” ሊል ይችላል። በዚህ ጊዜ ሌላ ቀን ተመልሰህ ጽሑፉን አንድ ላይ ሆናችሁ እንድታነቡ ወይም ገንዘብ በሚያገኝበት ጊዜ ለመምጣት እንደምትችል ልትገልጽለት ትችላለህ።

2 አንዳንድ ጊዜ ፍላጎት ያሳየ ሰው የምናገኘው በሌላ ሰው ቤት ወይም በመንገድ ላይ ሊሆን ይችላል። ታዲያ አድራሻውን ለመቀበል ንቁዎች ነን? ቤቱ ቅርብ ከሆነ ሊያሳይህ ይችል እንደሆነ ጠይቀው። ብዙዉን ጊዜ ሰዎች የወዳጅነት ስሜት ቢኖራቸውም ጊዜ እንደሌላቸው ይናገራሉ። ይህ መጽሔት ወይም ቢያንስ ቢያንስ ትራክት በማበርከት መልእክታችንን በአጭሩ በአንድ አረፍተ ነገር ማቅረብ የምንችልበት አጋጣሚ ሊሆን ይችላል። በአገልግሎት ጊዜ የምትጠቀምበትን አጭር መግቢያ ቀደም ብለህ ለመለማመድ ለምን አትሞክርም?

3 ብዙ አስፋፊዎች የቤቱ ባለቤት በሩ ጋር ሲደርስ ጭንቅ ጥብብ ይላቸዋል። ይሁን እንጂ ሳትጨነቅ አንድ መግቢያ ከተናገርክ ብዙ አጋጣሚዎች ልትከፍት ትችላለህ። እንዲህ ለማለት ትችላለህ:- “ከዚህ በፊት የማያውቋቸውን ሰዎች በማየትዎ የተደናገጡ ይመስላሉ። እርግጥ ችግርዎ ይገባናል፤ በአሁኑ ጊዜ አንድ ሰው ከዚህ በፊት ከማያውቀው ሰው ጋር ሲገናኝ ጥንቃቄ ማድረግ አለበት። ይሁን እንጂ ቀደም ሲል ይተዋወቁ ያልነበሩ ሰዎች እርስ በርሳቸው እንደ ጓደኛ ወይም እንደ ወንድማማች የሚተያዩበት ጊዜ በቅርቡ እንደሚመጣ ብዙ ሰዎች አያውቁም። ይህን ያምናሉ?”

4 በተመሳሳይ መንገድ ከቤት ወደ ቤት በሚደረገው አገልግሎት ከሚያጋጥሙት የተለመዱ ሁኔታዎች መካከል ጥቂቶቹ ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል። አንዲት ሴት ልብስ እያጠበች ይሆናል። እያከናወነች ላለችው ሥራ አድናቆትህን ከገለጽክ በኋላ ለአምስት ደቂቃ ያህል ሥራዋን አቋርጣ አንድ አስደሳች የሆነ ነገር እንድትሰማ ሐሳብ አቅርብላት። አንድ ወላጅ ከልጁ ጋር ሆኖ ታገኘው ይሆናል። የልጁን እድሜ ጠይቅና ይህ ልጅ ትልቅ በሚሆንበት ጊዜ ዓለማችን ምን ሊመስል እንደሚችል ጥያቄ አቅርብ። ወይም አንድ ወጣት በሩን ይከፍት ይሆናል። እድሜው ስንት እንደሆነ ወይም ስለ ትምህርቱ ሁኔታ፣ በሕይወቱ ውስጥ ስላለው ዓላማ ጠይቅና በዚህ ዘመን አንድ ወጣት በቀላሉ ደስታ ማግኘት ስለ መቻሉ ወይም ደስታ ማግኘት ቀላል ስለ መሆኑ ጠይቀው። እረፍት ላይ ያለ አንድ በእድሜ የገፋ ሰው ይኖር ይሆናል። በዛሬው ጊዜ አእምሮአችን ስለ ተለያዩ ችግሮች ማውጠንጠን እንደሚቀናው ከገለጽክለት በኋላ አንተ ግን የሄድከው አእምሮ በአስደሳች ሐሳቦች ላይ እንዲያተኩር ለማድረግ እንደሆነ ልትጠቅስ ትችላለህ።

5 አጋጣሚዎች እንዲያመልጡህ አትፍቀድ። የቤቱን ባለቤት ማግኘት ባትችልም ልታነጋግረው የምትችል ሌላ እንግዳ እቤት ይኖር ይሆናል። አንዳንድ እንግዳዎች ምሥራቹ ካልተዳረሰበት ክልል የመጡ ናቸው! ወይም አንድ ሰው ስታነጋግር ሁለተኛ ሰው መጥቶ ሊሰማ ይችላል። ሁለቱንም አነጋግርና የቤቱ ባለቤት ማን እንደሆነ ጠይቅ። አጋጣሚዎችን ለመጠቀም ንቁ እንድትሆን ይሖዋ እንዲረዳህ ጠይቀው። አዎንታዊ አመለካከት ይኑርህ! እንዲህ ካደረግህ የጥረትህን ዋጋ ታገኛለህ!

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2026)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2026 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ