ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች:- ሚያዝያና ግንቦት፦ የመጠበቂያ ግንብ ኮንትራት ማስገባት። ሰኔ፦ ሕይወት እንዴት ተገኘ በዝግመተ ለውጥ ወይስ በፍጥረት? ከሐምሌ እስከ መስከረም፦ በጉባኤ ወይም በግል የሚገኙ ቀለሙ እየደበዘዘ ወይም እየለቀቀ በሚሄድ ወረቀት የታተሙ የቆዩ መጻሕፍት እንደ ታላቁ አስተማሪ እንዲሁም በእንግሊዝኛ ቋንቋ ዘላለማዊ ዓለማ፣ ሕይወት ይህ ብቻ ነውን?፣ መንፈስ ቅዱስ፣ የሰው ልጅ መዳንና የሺህ ዓመት ግዛት የሚሉትን መጻሕፍት በ1 ብር ማበርከት ይቻላል። የየጉባኤዎቹ ጸሐፊዎች በአስፋፊዎች ወይም በአቅኚዎች ለተወሰዱት መጻሕፍት በቅጽ S-20-AM ላይ የዋጋው ልዩነት እንዲቀነስላቸው መጠየቁን መዘንጋት የለባቸውም። በተጨማሪም አረንጓዴ ቀለም ያለው የአዲሲቱ ዓለም የቅዱሳን ጽሑፎች ትርጉም በ5 ብር ሊበረከት ይችላል። ማሳሰቢያ:- ከላይ የተጠቀሱት የዘመቻ ጽሑፎች የሚያስፈልጓቸው ጉባኤዎች በሚቀጥለው ጊዜ በሚልኩት ወርኃዊ የጽሑፍ መጠየቂያ ቅጽ (S-14-AM) ላይ ማዘዝ ይችላሉ።
◼ ባለፈው ጊዜ ይመጣሉ ተብለው ማስታወቂያ የተነገረላቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ድራማዎችና የመዝሙር ካሴቶች ገና ባለመድረሳቸው እናዝናለን። በሚቀጥለው የመንግሥት አገልግሎታችን ላይ አዲስ ማስታወቂያ ከተነገረ በኋላ እንደገና እዘዙ።
◼ በዚህ ዓመት ከሐምሌ እስከ መስከረም በሚደረገው የገለልተኛ የአገልግሎት ክልሎች ዘመቻ ጊዜያዊ ልዩ አቅኚ በመሆን ለማገልገል የሚፈልጉ የዘወትር አቅኚዎች በጉባኤያቸው የሽማግሌዎች አካል (ወይም የአገልግሎት ኮሚቴ) በኩል ሊያመለክቱ ይችላሉ። የአገልግሎት ኮሚቴዎች ግለሰቡ ወይም ግለሰቧ ጊዜያዊ ልዩ አቅኚ መሆናቸውን ለምን እንደሚደግፉ፤ እንዲሁም አቅኚው ወይም አቅኚዋ ነጠላ ወይም ባለትዳር፣ ወንድ ወይም ሴት መሆናቸውን (ልጆች ካሏቸው ብዛታቸውን) እና አመልካቾቹ ለየትኛውም ጉባኤ ባልተመደበ የአገልግሎት ክልል ውስጥ ለሦስት ወራት ያህል ቢመደብ ወይም ብትመደብ ለመሄድ የሚችሉ መሆናቸውን እንዲጠቅሱ ይጠየቃሉ። የአገልግሎት ኮሚቴዎች እነዚህን ነጥቦች በግልጽ በማስቀመጥና አስተያየታቸውን አክለው የግለሰቡን ማመልከቻ ግፋ ቢል እስከ ሚያዝያ 15, 1994 ድረስ ለማኅበሩ መላክ አለባቸው።
◼ በሃይማኖታዊ አቋማቸው ምክንያት ልጆችን የማሳደግና የመጠየቅን መብት በተመለከተ የፍርድ ቤት ሙግት ያለባቸውን አስፋፊዎች ለመርዳት አስፈላጊ መረጃዎችን የያዘ በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ጽሑፍ ይገኛል። አስፋፊዋ ልጆቿን ለማሳደግ አትችልም የሚል የፍርድ ቤት ክስ የሚነሣው በሃይማኖቷ ምክንያት በሚሆንበት ጊዜ ብቻ የሽማግሌዎች አካል ይህ ጽሑፍ እንዲላክላቸው መጠየቅ ይችላሉ። ልጅን ማሳደግ ወይም መጠየቅን በተመለከተ የፍርድ ክስ ላለባቸው አስፋፊዎች ጠቃሚ መረጃዎችን ከጥቅምት 22, 1988 ንቁ! ገጽ 2–14 እና ከሚያዝያ 22, 1991 ንቁ! በገጽ 9 ላይ ከሚገኘው ሰንጠረዥ ማግኘት ይቻላል።
የልዩ ስብሰባ ቀናት ፕሮግራም:-
ግንቦት 8, 1994፤ ባሕር ዳር
ግንቦት 14, (ቅዳሜ) 1994፤ አዲስ አበባ (ክልል 2)፣ ሶዶ
ግንቦት 15, 1994 አለታ ወንዶ፣ አዲስ አበባ (ክልል 2)፣ ሻሸመኔ
ግንቦት 21, (ቅዳሜ) 1994፤ አዲስ አበባ (ክልል3)
ግንቦት 22, 1994፤ አዲስ አበባ (ክልል 3)፣ ጅማ
ግንቦት 29 1994፤ አዲስ አበባ (ክልል 3)፣ ናዝሬት፣ ነቀምት
ሰኔ 5 1994፤ ደሴ፣ ድሬዳዋ