የርዕስ ገጽ/የአዘጋጆች ገጽ
በሕይወት ተርፎ ወደ አዲስ ምድር መግባት
ከጥፋት በሕይወት መትረፍ በጊዜያችን በጣም አሳሳቢ ጉዳይ ሆኗል። ይሁን እንጂ በሰው ልጆች ፊት የተደቀነው ጥፋት በኑክሌር ፍንዳታ ከሚመጣ እልቂት የበለጠ ነገር ነው። አምላክ ራሱ ከሰዎች ጋር ይፋረዳል። ከዚህ ጥፋት በሕይወት የሚተርፉ ሰዎች እንደሚኖሩና እዚችው ምድር ላይ አስደናቂ ሁኔታዎች አግኝተው እንደሚኖሩ የሚገልጹ አስገራሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች አሉ። ይህ መጽሐፍ የተዘጋጀው እርስዎ ከእነዚህ ሰዎች አንዱ እንዲሆኑ ለመርዳት ነው።
— የመጽሐፉ አሳታሚዎች