“እንደ ማገዶ እሳት”
በዩ ኤስ ኤ ካሊፎርንያ ኦክላንድ ውስጥ የምትኖር ጄኒፈር የተባለች አንዲት የ16 ዓመት ልጅ መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶችን የገለጸቻቸው በዚህ መንገድ ነበር። “እነዚህን መጽሔቶች አዘውትሬ ማንበቤ ቅንዓቴ እንዲቀጣጠል ረድቶኛል” ስትል ገልጻለች። “የአጻጻፍ ስልታቸው ጽሑፎቹ የሚጻፉት በጨለማ ውስጥ ያሉ ሰዎች እውነታዎቹ ቁልጭ ብለው እንዲታዩአቸው ለማድረግ እንደሆነ በግልጽ ያሳያል።”
በተጨማሪም ጄኒፈር “የመጽሐፍ ቅዱስን ትክክለኛነት ለማስረዳት ለሚቀርቡት መረጃዎች በሙሉ” ያላትን ምስጋና ገልጻለች። እንዲህ ስትል ጽፋለች:- “የማነጋግረው ሰው ሁሉ ማለት ይቻላል፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ እምነት ይጎድለዋል። መጽሐፍ ቅዱስ ሊመረመር የሚገባው መሆኑን የሚገልጸው ይህ ሁሉ መረጃ ታትሞ መውጣቱ መረጃው የሚያስፈልገው እኔ በምኖርበት አገር ብቻ እንዳልሆነ እንድገነዘብ አድርጎኛል።”
ይህ ትክክለኛ አባባል ነው። የመጽሐፍ ቅዱስን ጥቅም ጎላ አድርጎ የሚያሳይ መረጃ የሚያስፈልገው በዓለም አቀፍ ደረጃ እንደሆነ የታወቀ ነው። ለሰው ሁሉ የሚሆን መጽሐፍ የተሰኘው ብሮሹርም የተዘጋጀው በዚህ ምክንያት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ እምነት ሊጣልበት የሚችል ነውን? ከሳይንስ ጋር ይስማማልን? ለዘመናዊው ኑሮ ተግባራዊ ጥቅም የሚሰጥ መጽሐፍ ነውን? ለሚሉትና ለሌሎችም ጥያቄዎች መልስ ይሰጣል።
ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ አለዚያም ደግሞ በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው በመላክ ይህን ባለ 32 ገጽ ብሮሹር ማግኘት ይችላሉ።
□ ለሰው ሁሉ የሚሆን መጽሐፍ የተባለውን ብሮሹር አንድ ቅጂ ላኩልኝ
□ መጽሐፍ ቅዱስን ያለ ክፍያ የሚያስጠናኝ ሰው እፈልጋለሁ።