አምላክን ማስደሰት ትፈልጋለህ?
መንፈሳዊ ነገር ማግኘትህ ለሕይወትህ አስፈላጊ እንደሆነ ይሰማሃል? ለቁሳዊ ነገሮች ብቻ ከፍተኛ ቦታ በሚሰጥበት ዓለም ውስጥ አንድ የጎደለ ነገር እንዳለ ሆኖ ይሰማሃልን? አምላክን ለማወቅና ከእርሱም ጋር የተቀራረበ ዝምድና ለመመሥረት ትፈልጋለህ?
‘አዎን፣ ግን ይህን ላደርግ የምችለው እንዴት ነው? መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብና መረዳት አስቸጋሪ ነገር አይደለም?’ ብለህ ትጠይቅ ይሆናል። አንዳንድ ሰዎች በጣም አስቸጋሪ በሆነ የኢኮኖሚ ሁኔታ ሥር በማደጋቸው ምክንያት ሊሆን ይችላል በትምህርት ቤት ያሳለፉት ጊዜ በጣም ውስን በመሆኑ የማንበብ ችግር ይኖርባቸው ይሆናል። ታዲያ እነዚህ ሰዎች አምላክንና እርሱ የዘላለም ሕይወት ማግኘት ለሚፈልጉ ያወጣቸውን ብቃቶች እንዲያውቁ እንዴት መርዳት ይቻላል?
የመጠበቂያ ግንብ ማኅበር በ1996 አንድ ጽሑፍ አውጥቶ ነበር። ይህ ጽሑፍ በአሁኑ ጊዜ በ211 ቋንቋዎች የሚገኝ ሲሆን አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው? የሚል ርዕስ አለው። ይህ ባለ ሙሉ ቀለም 32 ገጽ ብሮሹር የያዛቸው 16 ክፍሎች ለሚከተሉት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥያቄዎች ቀላል መልስ ይሰጣሉ:- አምላክ ማን ነው? ኢየሱስ ክርስቶስ ማን ነው? አምላክ ለምድር ያለው ዓላማ ምንድን ነው? እውነተኛውን ሃይማኖት እንዴት ማግኘት ትችላለህ? በተጨማሪም ብሮሹሩ በጸሎት አማካኝነት ወደ አምላክ እንዴት መቅረብ እንደምንችልና አምላክን የሚያስደስት ቤተሰብ እንዴት መገንባት እንደምንችል ይነግረናል።
የዚህን ብሮሹር አንድ ቅጂ ማግኘት የሚፈልጉ ከሆነ በዚህ ገጽ ላይ ያለውን ኩፖን ይላኩ።
□ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው? የተባለውን ብሮሹር አንድ ቅጂ ላኩልኝ
□ መጽሐፍ ቅዱስን ያለ ክፍያ የሚያስጠናኝ ሰው እፈልጋለሁ።