የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g98 9/8 ገጽ 32
  • “አንደኛ ደረጃ የሚሰጠው መጽሔት”

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • “አንደኛ ደረጃ የሚሰጠው መጽሔት”
  • ንቁ!—1998
ንቁ!—1998
g98 9/8 ገጽ 32

“አንደኛ ደረጃ የሚሰጠው መጽሔት”

ከዚህ በፊት ንቁ! መጽሔት አንብበው ያውቃሉ? በእጅዎ ያለውን ይህን መጽሔት ካነበቡ በኋላ እንዴት ሆኖ አገኙት? ርዕሶቹን ትምህርት ሰጪ፣ ጥሩ ምርምር የተደረገባቸውና ማራኪ በሆኑ ሥዕላዊ መግለ ጫዎች የቀረቡ ሆነው አገኙዋቸው?

በአፍሪካ ናይጄሪያ የሚገኝ አንድ በግሉ የሚንቀሳቀስ ጋዜጠኛ የሚከተለውን ጽፏል:- “የይሖዋ ምሥክር ባልሆንም እንኳ ንቁ! መጽሔትን ዘወትር አነባለሁ። ንቁ! አንደኛ ደረጃ የሚሰጠው መጽሔት ነው። ሁልጊዜ አዳዲስ እውቀቶች የማገኝበት መጽሔት ሆኖ አግኝቸዋለሁ። የመጽሔቱ ሽፋኖች ለዓይን የሚማርኩ ከመሆናቸውም በላይ ጭፍን ጥላቻ የሌለው አንባቢ ገጾቹን ገልጦ እንዲያነብ ከፍተኛ ግፊት ያሳድሩበታል። እያንዳንዱ እትም አስደናቂ የፈጠራ ውጤቶችን የሚያንጸባርቅ ሲሆን እያንዳንዱ ገጽ ደግሞ የተዋጣለት የአጻጻፍ ዘይቤ ያንጸባርቃል። ወቅታዊና የተዋጣላቸው ርዕሶች ይዞ የሚወጣው እያንዳንዱ እትም ጠቃሚና በዋጋ ሊተመን የማይችል ትምህርት ያቀርባል።”

በዚህ የንቁ! መጽሔት ቅጂ ላይ የወጡትን ርዕሶች እንዲመረምሩ እናበረታታዎታለን። ሌላ ቅጂ ማግኘት የሚፈልጉ ከሆነ የይሖዋ ምሥክሮች፣ ፖ.ሣ.ቁ. 5522፣ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ ወይም በገጽ 5 ላይ ከተዘረዘሩት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው ይጻፉ። ሌላ ቅጂ ልንልክልዎ ወይም ስለ ጊዜያችን ትርጉም ማብራሪያ ማግኘት የሚፈልጉ ከሆነም አንድ ሰው እንዲያነጋግርዎ ማድረግ እንችላለን።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2026)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2026 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ