የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g99 10/8 ገጽ 11
  • ውጫዊውን ሁኔታ ብቻ አይተህ ትፈርዳለህን?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ውጫዊውን ሁኔታ ብቻ አይተህ ትፈርዳለህን?
  • ንቁ!—1999
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ‘ይሖዋ ልብን ያያል’
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2010
  • ተስፋ የሚያስቆርጡ ነገሮች ቢኖሩም ጸንቷል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
  • ሳሙኤል እውነተኛውን አምልኮ አስፋፍቷል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2007
  • ሐር—ተወዳዳሪ የሌለው ምርጥ ክር
    ንቁ!—2006
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—1999
g99 10/8 ገጽ 11

ውጫዊውን ሁኔታ ብቻ አይተህ ትፈርዳለህን?

ሽፋኑን በማየት ብቻ ስለ አንድ መጽሐፍ የሆነ ድምዳሜ ላይ ትደርሳለህ? እንዲህ ካደረግህ ልትታለል ትችላለህ። ይህ እንዳይሆን መጀመሪያ ይዘቱን መርምር። በቱርክ በሚነገር አንድ ተረት ላይ የተጠቀሰው የዝነኛው ገጸ ባሕርይ የናዝሬዲን ሆዣ ገጠመኝ ይህን ያሳያል። (ሆዣ የሚለው የቱርክ ቃል “መምህር” ማለት ነው።) ናዝሬዲን “ብልህና ገራገር፣ ጥበበኛና ሞኝ ሰው ነው ... ለእምነቱ ያደረ ቢሆንም ሰብዓዊ ድክመቶች አሉት።” “በሕይወት ውስጥ ለሚያጋጥሙ እንግዳ የሆኑ ነገሮች እጅ የማይሰጥ ሰው” ነው።—በጆን ኑናን የተዘጋጀው ቴልስ ኦቭ ዘ ሆዣ፣ አራምኮ ዎርልድ፣ መስከረም-ጥቅምት 1997

አንድን የኦቶማን ባለሥልጣን ለመጠየቅና ከእርሱ ጋር እራት ለመብላት ስላደረገው ጉዞ የሚነገር አንድ ተረት አለ። “[ናዝሬዲን] ተጀንኖ ከፈረስ ላይ ወረደና ከፊት ለፊት ያለውን ግዙፍ በር አንኳኳ። በሩ ሲከፈት ድግሱ እየተካሄደ መሆኑን ተገነዘበ። ሆኖም ራሱን ከማስተዋወቁ በፊት ጋባዡ በጉዞ የመነቸከውን ልብሱን ተመልክቶ በንቀት ለማኞች አለመጋበዛቸውን ነገረው።”

ናዝሬዲን ኮርቻው ላይ ወደታሠረው ከረጢቱ ተመልሶ በመሄድ “ምርጥ የሆነ የክት ልብሱን ይኸውም ዙሪያውን ፀጉር ያለው ከሐር የተሠራ የሚያምር ካባውንና ሰፊ የሐር ጥምጣሙን አደረገ። በዚህ መልኩ ሽክ ብሎ ወደ ፊተኛው በር ተመለሰና በድጋሚ አንኳኳ።

“በዚህ ጊዜ ጋባዡ ሞቅ ያለ አቀባበል አደረገለት ... አገልጋዮቹ ጣፋጭ ምግቦች አቀረቡለት። ናዝሬዲን ሆዣ በሳህን የቀረበውን ሾርባ አንስቶ በካባው ኪስ ውስጥ አፈሰሰው። ሌሎቹ ታዳሚዎች በመገረም እያዩት የተጠበሱ ሥጋዎችን አንስቶ ጥምጥሙ ውስጥ ከተታቸው። ከዚያም በድንጋጤ በተዋጠው ጋባዡ ፊት ባለ ፀጉር ካባውን ሳህን ላይ ወደቀረበው ሩዝ አስጠግቶ ‘ብላ፣ አንተ ፀጉር ብላ!’ ይል ጀመር።

“ጋባዡ ‘ምን ማድረግህ ነው?’ ሲል ጠየቀው።

“‘ጌታዬ፣ ልብሶቼን እየመገብኳቸው ነው’ ሲል ሆዣ መለሰ። ‘ከግማሽ ሰዓት በፊት ባደረጉልኝ አቀባበል መሠረት እርሶ እንግድነት የተቀበሉት እኔን ሳይሆን ልብሶቼን እንደሆነ በግልጽ ማየት ችያለሁ!’”

እኛም ብዙ ጊዜ ውጫዊ ሁኔታን ብቻ በመመልከት አሉታዊ ወይም አዎንታዊ ፍርድ ሰጥተን ሊሆን እንደሚችል የታወቀ ነው! ነቢዩ ሳሙኤል፣ ይሖዋ ቀጥሎ የሚመርጠው የእስራኤል ንጉሥ የዳዊት ወንድም ኤልያብ መሆን አለበት ብሎ ባሰበ ጊዜ ይሖዋ እንዲህ ብሎታል:- “ፊቱን የቁመቱንም ዘለግታ አትይ፤ ሰው እንዲያይ እግዚአብሔር አያይምና ናቅሁት፤ ሰው ፊትን ያያል፣ እግዚአብሔር ግን ልብን ያያል።” (1 ሳሙኤል 16:7) አዎን፣ ይሖዋ የሚፈርደው ውጫዊ ገጽታን በመመልከት ሳይሆን የልብ ሁኔታን በማየት ነው። አንተስ የምትፈርደው እንዴት ነው?

[በገጽ 11 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

ሳሙኤል ውጫዊ ሁኔታን በመመልከት እንዳይታለል ይሖዋ አስጠንቅቆታል

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2026)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2026 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ