መጣላታቸውን እንዲያቆሙ ረዳቸው
ካሊፎርኒያ፣ ዩ ኤስ ኤ የሚኖር አንድ የ11 ዓመት ልጅ ብሩክሊን፣ ኒው ዮርክ ወደሚገኘው የይሖዋ ምሥክሮች ቢሮ የሚከተለውን ጽፏል:-
“መጽሐፎቻችሁን በተለይ ደግሞ ለቤተሰብ ደስታ ቁልፉ ምንድን ነው? የተባለውን መጽሐፍ ማንበብ በጣም ያስደስተኛል። ይህን መጽሐፍ አግኝተን ከማንበባችን በፊት እኔና እህቴ ሁልጊዜ እንጣላ ነበር። አንድ ቀን ይህን መጽሐፍ ለማጥናት ወሰንን። መጽሐፉን ካነበብን በኋላ ግን የምናደርገውን ነገር አምላክ እንደማይወደው ተገነዘብን።
“መጽሐፉ በጣም ጠቅሞናል። መጽሐፉን በማግኘቴ አመስጋኝ ነኝ። ግሩም መጽሐፍ በመሆኑ ሌሎች ቤተሰቦችም እንዲያነቡት አበረታታቸዋለሁ። በቤታችንም ውስጥ ሰላምና ደስታ እንዲሰፍን በማድረጉ ቤተሰቦቼን ረድቷቸዋል።”
ለቤተሰብ ደስታ ቁልፉ ምንድን ነው? የተባለው ይህ መጽሐፍ 192 ገጽ ያለው ሲሆን “ቤተሰባችሁን ጎጂ ከሆኑ ተጽዕኖዎች ጠብቁ፣” “በቤተሰባችሁ ውስጥ ሰላም እንዲሰፍን አድርጉ፣” “ቤተሰብን የሚያናጉ ችግሮችን መቋቋም ትችላላችሁ” የሚሉና ሌሎች ጠቃሚ ርዕሶችን በውስጡ አካቶ ይዟል።
አንድ የይሖዋ ምሥክር መጥቶ እንዲያነጋግርዎትና መጽሐፍ ቅዱስን በነፃ እንዲያስተምርዎ የሚፈልጉ ከሆነ የይሖዋ ምሥክሮች፣ ፖ.ሣ.ቁ. 5522፣ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ ወይም በገጽ 5 ላይ ከተዘረዘሩት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው ይጻፉ።