እስከ የካቲት 2026 ባለን መረጃ መሠረት በዓለም ዙሪያ ከ259 በላይ የይሖዋ ምሥክሮች በእምነታቸው ምክንያት ታስረዋል።
በዓለም አቀፍ የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ስምምነት ላይ አንቀጽ 18 የማሰብ፣ የሕሊና እና የሃይማኖት ነፃነትን ይደነግጋል። ይሁንና በአንዳንድ አገሮች ውስጥ የይሖዋ ምሥክሮች ይህን መብት ተነፍገዋል፤ በሃይማኖታዊ እንቅስቃሴዎች በመሳተፋቸው ወይም በሕሊናቸው ምክንያት ወታደራዊ አገልግሎት ለመስጠት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው የተነሳ ያለአግባብ እየታሰሩና እንግልት እየደረሰባቸው ነው።
“በእስር ላይ ያሉትን ከእነሱ ጋር ታስራችሁ እንዳላችሁ አድርጋችሁ በማሰብ ሁልጊዜ አስታውሷቸው።”—ዕብራውያን 13:3